የሽብርተኝነት ክስ የተመሠረተባቸው እነ አቡበከር መሐመድ ከሁለት ዓመት በላይ ጊዜ ከወሰደ ክርክር በኋላ በዛሬው ዕለት ጥፋተኛ ተባሉ፡፡

በፌዴራል ዓቃቤ ሕግ ክስ ተመሥርቶባቸው በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አራተኛ ወንጀል ችሎት ከጥቅምት 15 ቀን 2005 ዓ.ም. ጀምሮ በተካሄደ ክርክር፣ ዓቃቤ ሕግ ያቀረበባቸውን የሰውም ሆነ የሰነድ ማስረጃዎች ማስተባበል አልቻሉም የተባሉት

አቡበከር መሐመድ፣ አህመዲን ጀበል፣ ያሲን ኑሩ፣ ከሚል ሸምሱ፣ በድሩ ሁሴን፣ ሼክ መከተ ሙሔ፣ ሳቢር ይርጉ፣ መሐመድ አባተ፣ አህመድ ሙስጠፋ፣ ካሊድ ሽኩር፣ አቡበከር ዓለሙ፣ ጉሩ ቱርኪ፣ ሼክ ባህሩ ኡመር፣ ሙኒር ሁሴን፣ ሼክ ሰኢድ፣ ጋዜጠኛ የሱፍ ጌታቸው፣ ሙባረክ አደም፣ እንዲሁም ካሊድ አብርሃም በዛሬው  ዕለት ጥፋተኛ ተብለዋል፡፡

ተከሳሾቹ የተሰጠባቸውን የፍርድ ውሳኔ ከመቀመጫቸው በመነሳት በተደጋጋሚ  ተቃውመዋል፡፡ የቅጣት ውሳኔ ለመስጠት ፍርድ ቤቱ ለሐምሌ 27 ቀን 2007 ዓ.ም. ተለዋጭ ቀጠሮ የሰጠ ሲሆን፣ ዓቃቤ ሕግ የቅጣት ማክበጃውን ተከሳሾች ደግሞ የቅጣት ማቅለያቸውን እስከ ሐምሌ 10 ቀን 2007 ዓ.ም. ድረስ በጽሕፈት ቤት በኩል እንዲያስገቡ ትዕዛዝ ሰጥቷል፡፡

Leave a Reply