July 12th, 2015 

ወያኔ ጭንቅ ውስጥ ሲገባ አጣብቂኙ አላላውስ ሲለው ከሚወስዳቸው እርምጃዎች አንዱ እስረኞችን መፍታት ነው::በዛሬው እለትም የተደረገው ይህ ነው:: የውጪ ሃይሎች ጫና የኦባማ ወደ አፍሪካ ሕብረት መምጣት እና ተመሳሳይ የሆኑ ጉዳዮች እንዲሁም በአራቱም አቅጣጫ የተስፈነጠረው የባሩድ ሽታ ጦርነት ለመጀመር ሕዝብን ማማከር የሚሉ አባዜ ተደማምረው ዛሬ ቂሊንጦ ወያኔን አውልውታል::

ሁለት እና ሶስት እስረኛ አሊያም አስር እና ሃያ እስረኛ በመፍታት የሕዝብን ልብ ለመግዛት መሞከር አሊያም አቅጣጫ ለማስቀየር መፍጠን ብሎም ከገቡበት አጣብቂኝ ለመውጣት መሞከር አይቻልም::በሃግሪቱ ባሉት እስር ቤቶች እየተሰቃዩ ያሉትን የፖለቲካ እስረኞች ጋዜጠኞች ጦማርያን እንዲሁም በአጠቃላይ የሕሊና እስረኞች መፍታት የማያጠያይቅ ግዴታ ነው::በአስተሳሰባቸው እና በፖለቲካ እምነታቸው ሃሳባቸውን በነጻነት በመግለጻቸው የሃይማኖት ነጻነት በመጠየቃቸው እና የመብት ጥያቄዎቻቸውን በማቅረባቸው በሃሰት የፈጠራ ክስ እና ካለክስ በወህኒ ቤቶች ታስረው የሚገኙ ንጹሃን ኢትዮጵያውያንን ቤት ይቁጠረው::እነዚህ ሁሉ መፈታት አለባቸው::ይህ ህዝባዊ ጥያቄ ነው::

የፖለቲካ ጫና የኑሮ ውድነት እና ማህበራዊ ዝቅጠት አንገፍግፎት ወደ ትግል የገባውን ኢትዮጵያዊ ለማታለል ከሆነ እንደማይቻል 100% ልንነግራቹ እንወዳለን ትግሉ ይቀጥላል::እኛ ሁለት እና ሶስት እስረአ ተፈቱ ብለን አብረን ከካድሬዎቻቹ ጋር አናጨበጭብም በድጋሚ የለውጥ ትግሉ ይቀጥላል::ሁለት እና ሶስት እስረኛ በመፍታት የሕዝብን ልብ መግዛት አሊያም የትግል አጀንዳ ማፋለስ አይቻልም::በዚህ አጋጣሚ ከቂሊንጦ ወጥታቹ ከሰፊው የዞን ዘጠን እስር ቤት ለተቀላቀላቹ አገሩን ለቃቹ ውጡ እስክትባሉ ድረስ እንኳን ደስ ያላችሁ !!

Leave a Reply