Wednesday, 08 July 2015 14:50

       የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጽ/ቤት ሚኒስትር አቶ ሬድዋን ሁሴን አማካሪ የነበሩት አቶ አንዱዓለም አዱኛ አሞኘ ከሀገር መኮብለላቸው ተሰማ።

አቶ አንዱዓለም ባለፈው ሀገር ዓቀፍ ምርጫ በኢሕአዴግ ጽ/ቤት ለቅስቀሳ የሚሆኑ ሰነዶችን እንዲያዘጋጁ ከመንግስት ኮሚኒኬሽን ጽ/ቤት ተመድበው ይሰሩ ነበር። ሆኖም ምክንያቱ ለጊዜው ባልታወቀ ሁኔታ ከስራገበታቸው በመሰወራቸው፣ በተደረገው ማጣራት ከአሜሪካ ኤምባሲ በተገኘው መረጃ ወደ አሜሪካን ሀገር መግባታቸውን የሰንደቅ ምንጮች አረጋግጠዋል።

አቶ አንዱዓለም ከሀገር ከመኮብለላቸው በፊት ቀደም ብለው ባለቤታቸውንና ልጃቸውን ወደ አሜሪካ ማሻገራቸውም ታውቋል።

      አቶ አንዱዓለም ከሚኒስትሩ በተጨማሪ የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጽ/ቤት ሚኒስትር ዴኤታዎችን ያማክሩም እንደነበር ያገኘነው መረጃ ጠቁሟል። 

Leave a Reply