ህወሓት በጠመንጃና ዱላ ብቻ የተንጠለጠለ ስልጣ ይዛ እንድትቀር፣ በ2007 ዓ/ም ምርጫ ተሸንፎ ቅስሙ እንዲ ሰበር ያደረግነው የተሻለ ኣማራጭ ፓሊሲ፣ የበለጠ ዲሞክራሲያዊ ባህሪ፣ የነጠረ ሃገራዊ ራኢ፣ ህዝባዊነት የተላበሱና ከሂወት መስዋእትነት ጀምረው የኣካል መጉደል፣ የስራ መፈናቀል፣ የቤተሰብ መበተንና ከትዳር መፈናቀል፣ ከማህበራዊ ግንኝነቶች በማሰናከል ያልበገራቹው ጀግኖች ባካሄዱት እልህ ኣስጨራሽ ትግል ነው።
የህወሓት መንግስት ህዝባዊ መሰረት እንደሌለው በጠራራ ፀሓይ ላይ የተጋለጠበት ኣጋጣሚ የፈጠረው ድንጋጤ 100 ፐርሰንት ኣሸንፍያለው ብሎ ራሱን ያዋረደበት ኣጋጣሚ ፈጥሮዋል።
የትግራይ ህዝብ ካሁን በኋላ በስሙ መነገድ እንደማይቻል ኣረጋግጦ ኣልፈዋል። የህወሓት ኣመራሮች
የትግራይ ህዝብ በዓረና መድረክ ቁጥር ኣንድ ተመራጭ ዲሞክራሲያዊ፣ ስለማዊ፣ ሃገራዊ ድርጅት መሆኑ እንደ እሬት እየመረራቸው እንዲቀበሉት እያስገደዳቸው ነው።
የዓረና መድረክ የሃሳብ ልእልና የማይዋጥለት የህወሓት ኣመራር፣ ከፍተኛ ካድሬና የስልጣን ጥመኛ ድርጅቱ ኣሳምኖና ኣስፈቅዶ በህዝብ ፊት ቀርቦ ይከራከር።
ዓረና መድሩክ ኣምባገነኖች በሰከነ ኣካሄድና ሰለማዊ መንገድ ፤ ትግሉ ህዝባዊ መሰረት በማስያዝ ሳይወድ በግድ ከስልጣኑ ማውረድ እንደሚቻል ከማመኑ ባሻገር የበለጠ ኣስተማማኝ ዲሞክራሲያዊ መንግስት ለመገንባት ያስችላል ይላል።
እስቲ ድርጅታቹ ህወሓት ዱላዋን ኣስቀምጣ ሃሳብዋ ይዛ ወደ ህዝብ እድትቀርብ ኣድርጉ።
ነፃነታችን በእጃችን ኑው……!