የህወሓት 12ኛ ድርጅታዊ ጉባኤ ነሓሴ 14 /2007 ዓ/ም ይካሄዳል። የጉባኤው መቃረብ ተንተርሶ በህወሓት ሁለቱ ኣንጃዎች መካከል የስልጣን ፋክክር እየተደረገ ይገኛል።በጉባኤው ኣሸንፎ ለመውጣት የትግራዩ ኣንጃ ከክልል እስከ ቀበሌ በኣመራር ቦታዎች ያሉት ካድሬዎች እና እነሱ የሚቆጣጠሯቸው የኣንድ ለ ኣምስት(1 ለ 5) ኔትወርክ ኣደረጃቶች “…ድርጅታችን እንዳትበተን ኣደራ..” እያሉ እያስማሏቸው ይገኛሉ።የኣዲስ ኣበባው ኣንጃ ደግሞ ..የተማረና ወጣቱ ሃይል ኣሁን በስልጣን ላይ ያለው ኣቅመ ቢስ ኣመራር እንተካዋለን…” የሚል የተደራጀ እንቅስቃሴ እያደረጉ ይገኛሉ።

የትግራዩ ኣንጃ ደጋፊ ናቸው የተባሉ የፖሊስ ኮማንደሮች በማስፈራራትና በማግለል በኣዲስ ወጣት ኮማንደሮች ለመተካት ስብሰባዎች እየተደረጉ ይገኛሉ።

በትግራይ ከተሞች በርካታ ስብሰባዎ እየተካሄዱ የሚገኙ ሲሆኑ ተሰብሳቢዎቹ ከ20 – 30 ሰው ኣንድ ቦታ የሚሰበሰቡ ሲሆኑ ስብሰባው የሚመሩት ደግሞ ኣዳዲስና የማይታወቁ ሰዎች መሆናቸው ታውቀዋል።

ኣንድ ተሰብሳቢ በተለያዩ ሰዎች፣ ከተለያዩ ተሰብሳቢዎች፣ ተመሳሳይ ኣጀንዳ እየቀረበለት እንደ ሆነና በሁኔታው ግራ ገብቶት እንዳለ ታውቋል።

በትግራይ ያለው ድባብ የ93 ግዜ የህወሓት ክፍፍል በእጅጉ የሚመሳሰል ሆኖ የሁለቱ ኣንጃዎች ደጋፊዎች በከፍተኛ ስጋት ተውጠው ይገኛሉ።

በመቐለ በስፋት እየተወራ ያለው ጉዳይ ኣቶ ኣባይ ወልዱ ” ባንተስር ያሉ የድህንነት ሰዎች ኣሳውቀን ? ” የሚል ጥያቄ ከድህንነት ሰዎች እንደቀረበላቸውና ኣልናገርም ኣሻፈረኝ ማለተቸውና ይህን ተከትሎ የትግራዩ ኣንጃ በሃይል ለመቀየር የሚደርግ የኣዲስ ኣበባው ኣንጃ እርምጃ የሃይል ተቃውሞ ሊደርሰው እንደሚችልና ወደ ኣለመረጋጋትና ግጭት ሊደርስ እንደሚችል ተገምቶዋል።

የኣንጃዎቹ ሩጫ በጉባኤው ተሳታፊ የሚሆነው ኣባል ድጋፍ ማግኘት ለስልጣናቸው ወሳኝ ነገር ሁኖ ሳይሆን ለሚወስዱት የሃይል እርምጃ ይሁን ማጭበርበር ህጋዊ ሽፋን ለማላበስ ነው።
በዛሬው 30/11/2007 ዓ/ም በመቐለ ከተማ የክልሉ ልዩ ሃይል ከፍተኛ ጥበቃ እያካሄደ የዋለ ሲሆን ኣንደምታው በህወሓት ኣመራሮች መሃከል ከፍተኛ ኣለመተማመን መፈጠሩና ለድህንነታቸው መስጋታቸውን የሚያሳይ ነው።

በኣዲስ ኣበባ ሲካሄድ የነበረው የማእከላዊ ኮሚቴ ተጠናቅቆ ተሳታፊዎች ወደ መቐለ መምጣት በመጀመራቸው ነው ጥበቃው ያለወትሩ የተጠናከረው።

የኣዲስ ኣበባው ኣንጃ በትግራዩ ኣንጃ ላይ ከፍተኛ የስም ማጥፋት ዘመቻ ተያይዞታል።

በተለይ “…ኣቶ ኣባይ ወልዱ ከትዳራቸው ተለያይተዋል፣ ሙስና ተገኝቶባቹዋል…” የሚሉ በስፋት እያስወሩ ይገኛሉ።

ድምፂ ወያነ ትግራይ ለጉባኤው ከፍተኛ ትኩረት የሰጠች ስትሆን በብዛት ‘የመለስ ራኢ’ የሚሉ መፎክሮች እያሰማች ትገኛለች።

የኣንጃዎቹ ፋክክር ከኢትዮ_ኤርትራ ጦርነት ተከትሎ ያጋጠመው ክፍፍል የከፋ ኣደጋ ሊያጋጥም እንደሚችል የሰጉ ኣባላት ደግሞ ነገሩ በእርቅ እንዲቋጭ እንቅስቃሴ መጀመራቸው ታውቀዋል።

ያው የህወሓት ታሪክ ተመልሰን ስንፈትሽ በትግሉ ኣሸንፎ የወጣው ኣንጃ ለተሸነፈው ኣካል የተለያዩ ጥላሸት መቀባቱ የማይቀር ነው። ስለዚ ኳዂቶ (ኣቃቁማዎች) በብዛት ይገኛሉ ማለት ነው።

የህወሓት ክፍፍል ምን ያሳየን ይሆን……………?

Leave a Reply