ልደታ የሚገኘው 19ኛ ወንጀል ችሎት፤ በዛሬው እለት አምስት የፖለቲካ እስረኞችን በነጻ አሰናብቷውል። ፍፍርድ ቤቱ በነጻ እንዲፈቱ የወሰነላቸው፤ የአረና ህዝብ ግንኙነት ሃላፊ እና ታዋቂ ጦማሪ አቶ አብርሃ ደስታ፣ የሰማያዊ ፓርቲ ምክር ቤት ም/ሰብሳቢ አቶ የሺዋስ አሰፋ፣ የአንድነት ፓርቲ የድርጅት ጉዳይ ም/ሃላፊ አቶ ዳንኤል ሺበሺ እና የአንድነት ፓርቲ የሕዝብ ግንኙነት ክፍል ሃላፊ የነበረው አቶ ሃብታሙ አያሌው  ይገኙበታል።ከአንድ አመት እና አንድ ወር እስር በኋላ የተፈቱት ኢትዮጵያውያን፤ አቃቤ ህግ እንደሸረበው በሽብር ወንጀል ሊፈረድባቸው አልቻለም። ዛሬ የተፈቱት አምስት የህሊና እስረኞች …
1) ሐብታሙ አያሌው
2) ዳንኤል ሺበሺ
3) አብርሃ ደስታ
4) የሽዋስ አሰፋና
5) አብርሃም ሰለሞን ናቸው።

ከእስረኞቹ መካከል አብርሃም ሰለሞን በቤቴል ትምህርት ቤት መምህር የነበረ ነው። የሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ፈጠራ አሸናፊ በመሆኑ፤ መምኅር አብርሃም ሰለሞን ታስሮ በነበረበት ወቅት በአገር አቀፍ ደረጃ አሸናፊ ሆኗል። እሱ በነሃሴ ታስሮ አሸናፊ በተባለበት ወቅት (በጥቅምት ወር) እናቱ እሱን ወክለው፤ ሜዳልያውን ወስደዋል። እናቱ ያሸነፈውን ሜዳልያውን እስር ቤት ይዘው ሲሄዱ፤ ፖሊሶች ሜዳልያውን ማሳየት አይችልሉም ብለው ይዘው እንዳይገቡ ጭምር ከልክለዋቸው ነበር። አብርሃም ሰለሞንን ብዙ ሰውዎች ስለማያውቁት ነው በጥቂቱ ለማስተዋወቅ የሞከርነው።

አብርሃም ሰለሞን

በእውነት ላይ ባልተመሰረተ የሃሰት ክስ የተከሰሱ ወገኖች፤ እንዲህ በነጻ ሲፈቱ እውነተኛ ኢትዮጵያውያን ደስ እንደሚሰኙ ሁሉ፤ የስርአቱ ደጋፊዎች በበኩላቸው ደግሞ ቅር ሊላቸው እንደሚችል ይገመታል። እርስዎ በዚህ መልካም ዜና ከተደሰቱ ለሌሎች፤ መልካሙን ዜና ያካፍሉ።

የኢትዮጵያ ነጻ-ፕሬስ ጋዜጠኞች እና የፖለቲካ እስረኞች ያለአግባብ መታሰራቸው ይይታወቃል። በዚህ አጋጣሚ የህሊና እስረኞች እንዲፈቱ በሰላማዊ ሰልፍ እና በዲፕሎማቲክ መንገድ ጥረት ሲያደርጉ የነበሩ ዜጎችም ሊመሰገኑ ይገባል። “ድካማቹህ ፍሬ አፍርቷል። እንኳን ደስ ያላቹህ።” ልንላቸው እንወዳለን።

Share Button

Leave a Reply