“ኢትዮጵያዉያንን ማከም ሄዴክ ነዉ። መድሃኒት መዉሰድ አይወዱም። ቢጀምሩም አይጨርሱም። የረጅም ጊዜ ክትትል የሚፈልግን ህመም በአግባቡ አይከታተሉም። ደግሞ የ አብዛኛዎቹ ኬዝ የስኳር ህመም ነዉ። ምንድነዉ የምትመገቡት? ብዬ ስጠይቃቸዉ ሁሉም እንጀራ ይሉኛል። እና እንጀራ ከምን እንደሚሰራ ለማወቅ በከተማዉ ከሚገኙ ኢትዮጵያዉያን መደብር ሁሉ ሂጄ አዉቃለሁ።” ይህን ያለዉ ሲያትል አንድ ኔበርሁድ ክሊኒክ ዉስጥ የሚሰራ ከፍተኛ የጤና ባለሙያ ነዉ (ኦፊሻል ያልሆነ)
ለኛ ኢትዮዽያዉያን እንጀራ የምግብ አይነት ብቻ አይደለም፤ከቀን ተቀን እንቅስቃሴያችን፣ ስነ- ልቦናችንና ማንነታችን ጋር ከፍተኛ ቁርኝት ያለዉ እሴት ጭምር እንጂ።ለዚህም ይመስላል ኢትዮጵያዉያን ስደተኞች ስንት የምግብ አማራጭ ባለበት ሃገራት ዉስጥም ሆነዉ ከእንጀራ ጋር ሙጥኝ ያሉት…
እንጀራ ሃገር ቤትና ከ ሃገር ዉጭ(ቢያንስ በሰሜን አሜሪካ)የሚዘጋጅበት መንገድ ፈፅሞ የተለያየ ነዉ። የሃገር ቤት እንጀራ በዋናነት ከጤፍ የሚዘጋጅ ሲሆን፤ ጤፍ ደግሞ ‘ግሉቲን ፍሪ'(Gluten free) ከመሆኑም በተጨማሪ በርካታ ንጥረ ነገር ያሉት በመሆኑ ጠቃሚ የምግብ ግብዕት ነዉ። ኔዘርላንድ ሃገር የሚገኝ የህክምና ተቋም ሲሊያክ ዲዚዝ(celiac disease) ላለባቸዉ ህሙማን ከጤፍ የተዘጋጁ ምግቦችን እንዲመገቡ ‘ሪከመንድ’ እንደሚያደርግም አንብቢያለዉ….
በሰሜን አሜሪካ ጤፍ ዉድ ነዉ። ስለዚህ ነጋዴዎች እንጀራን የሚያዘጋጁት ከሌላ ነገር ነዉ። በትክክል ከምን እንደሚያዘጋጁት ካዘጋጆቹ አፍ ለመስማት ፈልጌ የተወሰኑ መደብር ባለቤቶችን አናግሬ ሊነግሩኝ ፍቃደኛ አልሆኑም። ምናልባት መረጃዉን ከሰራቶኞቻቸዉ ካገኘዉ ብዬም ሞክሬ ነበር፤ አብዛኛዋቹ ሰራተኞችም እንደማያዉቁና ‘ተዋሶዉን'(ingredients) እንደ ኮካ መስሪያ ቅመም ባለቤቶቹና ጥቂት የቅርብ ሰዋቻቸዉ ብቻ እንደሚያውቁ አጫዉተዉኛል። የ አሜሪካም ህግ የምግብ አምራቾች ያመረቱት ምግብ ከምን እንደተሰራ ለሸማቾች እንዲያስውቁ የሚያዝ ቢሆንም ‘ጥቃቅንና አነስተኞችን'(small businesses) አያስገድድም…
እናም ያለኝ ኣማራጭ ጎግል ማድረግና በኮሚኒቲዉ ዉስጥ የሚነገሩ መረጃዎችን ማጠናቀርና መፈተሽ ነበር። ያገኘዉት መረጃ የሚያሳየኝ እንጀራ ጤና ላይ ከፍተኛ ጉዳት ሊያመጡ ከሚችሉ ንጥረ ነገሮች እንደሚዘጋጅ ነዉ። ሰልፍ ራይዚንግ፣ ቤኪንግ ሶዳ፣ ሶዲየም፣ሶዳ ዉሃ ፣ማር፣ስንዴና እጅግ በጣም ጥቂት ጤፍ ወዘተ እንጀራ ለማዘጋጀት የሚዉሉ ግባአቶች ናቸዉ። ርካሽ በመሆኑ ከፍተኛ ተዋፆዉን(share) የሚይዘዉን ሰልፍ ራይዚንግ ብንወስድ በአምራቾቹ ዘንድ እንደ መደበኛ ዲቄት ግልጋሎት ላይ እንዳይዉል የሚመከር ከፍተኛ መጠን ያለዉ ስኳር የያዘ ፍላወር ነዉ። ይህም የዘዉትር ተመጋቢዉን ለ ስኳርና ደም ግፊት ህመም የሚያጋልጥ ብቻ ሳይሆን ፤አስገራሚ ለሆነዉ የአብዛኛዉ ሃበሻ ወንድ የሰዉነት ቅርፅ (አጠር ያለ፣ ቦርጬ ሸሚዙን ገፍቶ የወጣና ቀጭን እግር) ምክንያት ሳይሆን አይቀርም።
የሚገርመዉ ነጋዴዎች አልፎ አልፎ ከጤፍ ብቻ የሚሰራ እንጀራ ከተለመደዉ እንጀራ በጥፍ ዋጋ ማቅረባቸዉ ነዉ። ይህ ማለት ከፈለጉ ገበያዉን ሙሉ በ ሙሉ በጤፍ እንጀራ ማስያዝ ይችላሉ ማለት ነዉ። ተጠቃሚም የጤፍ እንጀራን ብቻ በመግዛት(ወይም ጎጂዉን እንጀራ ባለመግዛት) ሁኔታዉን መቆጣጠር ያለበት ይመስለኛል። ከገፋም ኮሚኒቲዉ መንግስት የእንጀራ ምርት ሂደት ላይ ልዩ ቁጥጥር እንዲያደረግ ግፊት ማድረግ ይኖርበታል። ባለሙያዎችም በዚህ ዙሪያ ምርምር ቢያረጉ ብዬ እመኛለዉ…
አልያ እንጀራ ፍለጋ ሃገር ለቆ የወጣ ወገን በእንጀራ መዘዝ ጤናዉ አደጋ ላይ መዉደቁ የሚቀጥል ይሆናል…