ከነሐሴ 16 ቀን 2007 ዓ.ም. ጀምሮ በመቀሌ የሰማዕታት አዳራሽ ሲካሄድ የከረመው 12ኛው የሕወሓት ጉባዔ አቶ ዓባይ ወልዱ ሊቀመንበር ሆነው እንዲቀጥሉ በድጋሚ መረጣቸው፡፡ ዶ/ር ደብረ ጽዮን ገብረ ሚካኤል ምክትል ሊቀመንበር ሆነው ተመርጠዋል፡፡ከሁለቱ ሊቀ መናብርት በተጨማሪ ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም፣ አቶ በየነ ምክሩ፣ ወ/ሮ አዜብ መስፍን፣ አቶ ዓለም ገብረ ዋህድ፣ አቶ ጌታቸው አሰፋ፣ ዶ/ር አዲስ ዓለም ባሌማና ወ/ሮ ፈትለወርቅ ገብረ እግዚአብሔር (ሞንጀሪኖ) የሕወሓት ሥራ አስፈጻሚ (ፖሊት ቢሮ) አባላት ሆነው ተመርጠዋል፡፡

ሕወሓት ከነባር የፖሊስ ቢሮ አባላት መካከል አቶ ዓባይ ፀሐዬ፣ አቶ አባዲ ዘሞ፣ አቶ ቴድሮስ ሐጎስና አቶ ፀጋይ በረኼ በመተካካት ሸኝቷል፡፡ ወ/ሮ ሮማን ገብረ ሥላሴ፣ አቶ ተወልደ ብርሃን በርኼና አቶ ተክለወይኒ አሰፋ በፈቃዳቸው ከማዕከላዊ ኮሚቴ አባልነት ለቀዋል፡፡

ለማዕከላዊ ኮሚቴ አባልነት 50 አባላት ታጭተው 45 አባላት የተመረጡ ሲሆን፣ የአቶ ዓባይ ወልዱ ባለቤት ወ/ሮ ትርፉ ኪዳነ ማርያምና የመቐለ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ክንደያ ገብረ ሕይወት ሳይመረጡ ከቀሩት አምስት አባላት መካከል ተጠቃሽ ናቸው፡፡

ከሁለት ዓመት ተኩል በፊት በተካሄደው 11ኛው የሕወሓት ጉባዔ የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላት ሆነው ከተመረጡት ውስጥ አቶ ቴዎድሮስ ሐጎስ፣ ወ/ሮ ትርፉ ኪዳነ ማርያምና አቶ ገብረ መስቀል ታረቀ ሳይቀጥሉ ቀርተዋል፡፡ አቶ ጌታቸው አሰፋ፣ ዶ/ር አዲስ ዓለም ባሌማና ወ/ሮ ፈትለወርቅ ገብረ እግዚአብሔር አዳዲስ አባላት ሆነው ገብተዋል፡፡

ለማዕከላዊ ኮሚቴ አባልነት 50 አባላት ታጭተው 45 አባላት የተመረጡ ሲሆን ምርጫ ውጤት ይህንን ይመስላል።
1. ዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል————–1107
2. ኣዜብ መስፍን————————–1089
3. ፈትለወርቅ ገ/ሔር———————-1085
4. ጌታቸው ኣሰፋ————————–1084
5. ኣባይ ነብሶ——————————1082
6. ዶ/ር ቴድሮስ ኣድሓኖም——————1070
7. ኣረጋሽ በየነ—————————–1067
8. ዶ/ር ኣዲሰኣለም ባሌማ——————-1063
9. በየነ ምክሩ——————————1046
10. ኪሮስ ቢተው —————————1043
11. ዶ/ር ኣብርሃም ተኸስተ——————1028
12. ያለም ፀጋይ ————————–1019
13. ኬርያ ኢብራሂም———————–1019
14. ሓዱሽ ዘነበ—————————-1009
15. ተወልደብርሃን ተስፋኣለም—————-1001
16. ሚኪኤለ ኣብርሃ————————997
17. ተወልደ ገ/ፃድቓን———————-982
18. ጎይትኦም ይብራህ———————-975
19. ጎቦዛይ ወ/ኣረጋይ———————–974
20. ኣባይ ወልዱ—————————973
21. ዶ/ር ገ/ሂወት ገ/ሔር——————-968
22. ተስፋኣለም ይሕደጐ——————–966
23. ሓጐስ ጎደፋይ————————–961
24. ኣለም ገ/ዋህድ————————–958
25. እያሱ ተስፋይ————————–953
26. ሃይለ ኣስፍሃ—————————-941
27. ኣፅብሃ ኣረጋዊ————————–936
28. ብርሃነ ፅጋብ—————————-936
29. ሙሉ ካሕሳይ———————-933
30. ብርሃነ ኪ/ማርያም——————926
31. ዲኒኤል ኣሰፋ———————-916
32. ጌታቸው ረዳ———————–909
33. ሃፍቱ ሓዱሽ————————898
34. ገ/መስቀል ታረቀ——————–895
35. ዘነበች ፍስሃ————————-895
36. ኢሳያስ ገ/ጅወርግስ——————-895
37. ኪሮስ ሓጐስ————————-895
38. ሽሻይ መረሳ————————-895
39. ብርሃነ ገ/የሱስ———————–869
40. ኢሳያስ ታደሰ———————–869
41. ነጋ በርሀ—————————-842
42. ማሙ ገ/ሔር———————–811
43. ተኽላይ ገ/መድህን——————–807
44. ቅድሳን ነጋ————————–787
45. ይትባረክ ኣመሃ———————-783

ሳይመረጡ የቀሩት

1. ጥላሁን ታረቀኝ———————777
2. ትርፉ ኪ/ማርያም——————-753
3. ኣልማዝ ገ/ፃዲቕ——————-686
4. ለምለም ሓድጉ———————665
5. ዶ/ር ክንደያ ገ/ሂወት —————661

 

Leave a Reply