በዲላ ዩንቨርስቲ ውስጥ ዛሬ ጠዋት ተማሪዎች የውሃ እጦት እንዲቀረፍላቸው ዛሬ ሐሙስ ጳጉሜ 4 2007 ጠዋት ያቀረቡትን ጥያቄ ተከትሎ በተፈጠረ አለመግባባት አስተዳደሩ ከጠራቸው የልዩ ሃይል ፖሊሶች ጋር መጋጨታቸው ተሰምቷል::በተነሳው ግጭት የተወሰኑ ተማሪዎች የተጎዱ ሲሆን የልዩ ሃይል ፖሊሶች ወደ ግቢው ዘልቀው በመግባት በርካታ ተማሪዎችን እየደበደቡ በማፈስ መውሰዳቸውን የአይን እማኞች ገልጸዋል::
በተለያዩ የሃገሪቱ ዩንቨርስቲዎች የተለያዩ የትምህርት የምግብ እና የውሃ የመኝታ አገልግሎት ጥያቄዎች ቢቀርቡን የወያኔ ጉጅሌ አገዛዝ ፖሊሶችን በመላክ አስከፊ እርምና ተማሪዎች ላይ እየወሰደ ይገኛል::ተማሪው በጋራ ሕብረት ፈጥሮ ለጥያቄዎቹ መልስ እንዳያገኝ የተለያዩ እክሎችን በመፍጠር ተማሪውን በብሄር በመከፋፈል እርስ በርስ እንዲባላ የፖለቲካ አላማው ማራመጃ ብማድረግ ላይ የሚገኘው የወያኔ አገዛ በአሁኑ ወቅት ተነቅቶበት ተቀባይነት እያጣ መሆኑ ታውቋል::