ዓረና ትግራይ ለዴሞክራሲና ለሉእላዊነት የ 2007 ዓ/ም ዘመነ ሉቃስ ተገባዶ ወደ 2008 ዓ/ም ዘመነ ዮሃንስ እንካን በሰላም አሸጋገረን በማለት አዲሱ ዘመን የሰላም ‘የደስታና የብልፅግና ኣመት እንዲሆንል በማለት ለመላ የኢትዮåያ ህዝቦች የመልካም ምኞት መግለጫውን ያቀርባል ፡፡
ኣዲሱ ኣመት የሰላም ‘የደስታና የብልፅግና ኣመት እንዲሆንልን ማደረግ በኛው ኢትዮåያውያን ዜጎች እጅ ነው፡፡ አዲሱ ዓመት የሰላም ፣ የደስታና የብልፅግና ዓመት እንዲሆንልን መመኘት የመጀመርያው እርምጃ ቢሆንም ምኞቱ ክውን ሆኖ ለማየት ግን በግልም ሆነ በቡድን ከእያንዳንዳችን ኢትዮጵያዊያን ዜጎች የሚጠበቅ ሃገራዊ ግዴታ አለብን፣፣ ስለሆነም መጪው ኣዲስ ኣመት የሰላም ‘የደስታና የብልፅግና ኣመት ይሆንልን ዘንድ ከመመኘት ወደ እውነታ ለመብቃት ከገ¸ው ፓርቲ ‘ከመንግስትና’ ከተቃዋሚ ፓርቲዎች እንዲሁም ከሲቪል ማሕበራትና ከእያንዳንዱ ዜጋ የሚጠበቀው ሚና ወሳኝነት ኣለው፡፡
የፍላጎት’የሃሳብና የእምነት ልዩነት መኖር የሰው ልጅ ተፈጥሮአዊ ባህሪ ሆኖ ለየተለያየ ፖሊሲ የሚያራምዱ ፓርቲዎችን መፈጠር ምክንያት ሆኖ ብሎም የህዝቦች የሰላም ፍላጎትና የህዝቦች ፍላጎት የበላይነት መከበር ሲባል የሰላማዊ ‘ሕጋዊና ዴሞክራሲያዊ ውድድር መኖር የግድ ማለቱ፣ ይህ ባልተቻለበት ወይም የሚቻል እያለ ባልተጠቀምንበት ደግሞ ለ የእርስ በርስ ጦርነቶች ማቆጥቆጥ ምክንያት እንደሚሆንና ይህን ለሃገር ሰብኣዊና ቁሳዊ ሃብት ውድመት ዓይነተኛ ምክንያት እንደሆነ ከታሪክ የምንማረው ብቻ ሳይሆን በህይወታችን ያየነው እውነታ ነው፡፡
ዓረና ትግራይ ለዴሞክራሲና ለሉእላዊነት ፓርቲ /ዓረና / መጪው አዲሱ ዓመተ 2008 የሰላም ፣ የደስታና የብልፅግና ዓመት እንዲሆንልን የሚያግዙት የኢትዮጵያ የወቅቱ የፖለቲካ ትኩሳት በጥልቅ በመገምገም ከሰላማዊ የፖለቲካ ስትራቲጂ የበለጠ የትግል አማራጭ እንደማይኖር አስምሮበታል፣ ሰብአዊ መብታቸው የተገነዘቡና ለሰብአዊ መብታቸው የቆረጡ ዜጎች በሰላማዊ የትግል ስትራተጂ እውን መሆን የሚችሉ መሆናቸውና መብቱና ነፃነቱ የተገነዘበ ዜጋ በሃይል መግዛት እንደማይቻል የንድፈ ሃሳብና የታሪክ ልምድ አስረጂነት በመደገፍ ያለንበት ወቅት፣ሃገራዊና ዓለም አቀፍ ሁኔታው ግምት ውስጥ በማስገባት በሰላማዊ መንገድ የለውጥ አጀንዳ ማራመድና ለውጤት መድረስ እንደሚቻል በፅኑ ያምናል፡፡ በአዲሱ አመት በሰላማዊ ስትራቴጂ ሀገር አቀፍ የለውጥ አመራጭ እንዲፈጠር ፍላጎት ካላቸው የፖለቲካ ፓርቲዎች በመተባበር ውሁድ ሀገራዊ አማራጭ ፓርቲ እውን ለማድረግ ሲያካሄድ የነበረው ዝግጅት በተግባር እውን ለማድረግ ወሰኑን በዚሁ አጋጣሚ ሲያበስር ደስታ ይሰማዋል ፡፡ በዚሁ ሰፊ የሃገር አጀንዳ ለውጥ ፈላጊ ዜጎች በግልም ሆነ በቡድን በጉዳዩ ገንቢ ሃሳባቸውና ፍላጎታቸው ቢያካፍሉን ደስታችን ወደር አይኖረውም ፡፡
ከተገባደደው ዓመት ወደ አዲሱ ዓመት ስንሸጋገር በተገባደደው አመት ያየናቸውና ያጋጠሙን ችግሮች ወደ አዲሱ አመት እንዳይሸጋገሩና አዲሱ ዐመት የሰላም ፣የደስታና የብልፅግና አመት እንዳይሆን የሚያውኩ መልከ ብዙ ችግሮቻችን ይወገዱ ዘንድ በግልም ሆነ በቡድን የዜግነት ሃላፊነታችን መወጣት የገድ የሚሉን አሉ፡፡
1. መላው ኢትዮጵያዊ ዜጎች ፣ ገዥው ፓርቲና ተቃዋሚ ፓርቲዎች የሁሉም ኢትዮጵያዊያን ችግር ያለ ልዩነት መላው ኢትዮጵያዊያንን ያቆሰለ እንጂ አንዱን ሸልሞ ሌላው የጎዳ ባለ መሆኑና የችግሩ መፍትሄም በሁሉም ኢትዮጵያዊያን የጋራ አsምና የጋራ መስዋእትነት ብቻ መሆኑን መገንዘብና ፣ እንዲሁም የአገራችን እጣ ፈንታ ለማስዋብና የሃገራችን ፖለቲካ ለማዘመን ከማናቸውም መልኩ ከዘር ፖለቲካ መራቅ የሚጠበቅብን መሆኑን፣
2. ሌላውን የሚጨቁን እራሱም ነፃ አይደለም ጦሱም ለሁሉም የሚተርፈ እንጂ ተቃዋሚ ፓርቲ ጎድቶ ገዢ ፓርቲ የሚያፋፋ ስለማይሆን ሰላማዊ የትግል አማራጭን የመረጡ የፖለቲካ ፓርቲዎች በዘመቻ ማሳደድ ፣የተቃዋሚ ፓርቲ አባላትን በግድ አባልነታቸው እንዲሰርዙ ማስገደድ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ከህዝብ የሚገናኙበት እንደ ህዝባዊ ፖለቲካዊ ስብሰባና ሰላማዊ ሰልፍ እንዳይደረግ ማፈን ፣ ከሁሉም ጥፋች የከፋ ጥፋትና የሰላም ጠንቅ በመሆኑ በተለይ በተለይ የገዢው ፓርቲ ካድሬዎች የሃገር እጣ ፈንታ ከፖለቲካ ፍላጎት እንደሚቀድም ተገንዝበው የበኩላቸውን ሃገራዊ ሃላፊነት እንዲወጡ ፣
3. ሰብአዊ መብትና ነፃነት በገዛ ትግልና ጥረት የምታመጣው እንጂ በገፀ በረከት የሚሰጥ ፀጋ ባለመሆኑ እያንዳንዱ ዜጋ የገዛ ራሱ መብትና ነፃነት ለማስከበር የሚያሳየው ድፍረትና ቆራጥ አsም መጪው አዲሱ አመት የሳላም ፣የደስታና የብልፅግና ሆኖ እነዲከወን የማድረግ ወሳኝ ሃላፊነት ያለው መሆንና ይህንኑ ሃላፊነቱ ለፖለቲካ ፓርቲዎች በመተው በገዛ መብቱ ባይተዋር ለመሆን መፍቀድ እንደማይጋበው፣ፍርሃት በማናቸውም መስፈርት ሰብአዊ መብትና ነፃነት አሳልፎ ለመስጠት ተቀባይነት ሊኖረው የማይችል መሆኑንና እንዲያውም መፍራት ያስፈልጋል ከተባለ ከሁሉም ባላይ መፍራት ያለብን እየፈሩ መኖር መሆኑን መገንዘብ ፍርሃትን በማስወገድ አዲሱ ዓመት የሰላም ፣ የደስታና የብልፅግና ዓመት ማድረግ የሚጠበቅብን መሆኑን፣
4. በፖለቲካ ፓርቲዎች የፖሊሲ ልዩነት እንዳለ ሆኖ በሃገራችን የሰላም ፣የደስታና የብልፅግናና ራኢ ሊተገበር የሚቻለው የኢትዮጵያ ህዝቦች እኩልነት በመቀበልና በመተግበር ፣ብሄርነትና ብሄረሰብነት እንዲሁም የተለያዩ ባህላዊና ማንነታዊ ማሕበረሰብነት ተፈጥሮአዊ ፀጋና የሃገሪቱ ውበት አድርጎ መቀበልና የሁሉንም ፍላጎት ያካተተ የፖሊሲ አቅጣጫ ብቻ የሃገራችን የሰላምና የብልፅግና መነሻና መድረሻ አድርጎ መቀበልና መተግበር አስፈላጊ መሆኑን ፣
5. በሃገራችን የሰላማዊ የለውጥ አጀንዳ ዋናው ባቤት ወጣቱ ትውልድ በመሆኑና የሰላማዊ የለውጥ አማራጭ መጥፋት ወናው ተጎጂም ወጣቱ በመሆኑ ተወደደም ተጠላም በለውጥ አጀንዳው ወጣቱ ለመብቱ ንቁ፣ብቁና ዝግጁ መሆን የሚጠበቅበት መሆኑን ፣
መገንዘብና ለጉዳዩ ቁርጠኛ አsም መሳየት እንደሚጠበቅብንና በጋራ እንድንቆም ዓረና ትግራይ ጥሪውን እንሆ አዲሱ ዓመት የሰላም ፣ የደስታና የብልፅግና ዓመት እንዲሆንልን ምኞቱን ለመላው የኢትዮጵያ ህዝቦች ያቀርባል፡፡

Berhanu Berhe
ዓረና ትግራይ ለዴሞክራሲና ለሉእላዊነት /ዓረና /
ጳጉሜን 6/2007 ዓ/ም
መቐለ