“በምህረት” እንዲፈቱ ከተወሰነላቸው ኡስታዞቻችን እና ወንድሞቻችን መካከል አራቱ ተፈቱ!
አቡ ዳውድ ኡማን
በሃሰት በሽብር ወንጀል የተፈረደባቸው በኡስታዝ አቡበከር አህመድ መዝገብ ከሚገኙት ኮሚቴዎቻችን እና ወንድሞቻችን መካከል ስድስት የሚሆኑትን አዲሱን አመት ምክንያት በማድረግ በይቅርታ መንግስት እንደፈቱ መወሰኑን መዘገቡ የሚታወስ ሲሆን እስከዛሬ ድረስ ሳይፈቱ መቆየታቸው ይታወሳል፡፡
በዛሬው ዕለት ግን ቃሊቲ ማረሚያ ቤት የነበሩት አራቱ ሰማቸው የተገለጸው ኡስታቻችን እና ወንድሞቻችን ከእስር መፈታታቸው ታውቋል፡፤
ከእስር የተፈቱት
1.ኡስታዝ ያሲን ኑሩ
2. ወንድም አቡበከር አለሙ ፣
3. ወንድም ሳቢር ይርጉ ፣
4.ወንድም ሙኒር ሁሴን ናቸው፡፡
የፍትህ ሚኒስተረ ምህረት አደረኩላቸው ያለው የህግ ታራሚዎች ባጠቃላይ 238 ሲሆኑ በተለያዩ ወንጀሎች ተፈርዶባቸው በማረሚያ ቤት የነበሩ መሆናቸው ተገልፆል፡፡
ከነዚህ 238 እስረኞች መካከልም ስድስቱ ኮሚቴዎቻችን እና ወንድሞቻችን ሲሆኑ በዛሬው ዕለት መስከረም 4 አራት የሚሆኑት ከእስር መለቀቃቸው ተዘግቧል፡፡
በአላህ ፈቃድ ከእስር ነፃ የወጣችሁት ኤስታዞቻችን እና ወንድሞቻችን እንዲሁም መላው ቤተሰባቸው እና ሙስሊሙ ማህበረሰብ እንኳን ደስ አላችሁ
አልሃምዱሊላህ አልሃምዱሊላ