በኬንያ በደረሰ የሄሊኮፕተር አደጋ የአገሪቱ ኢታማዦር ሹም እና ሌሎች መኮንኖች ሞቱ

ከ 4 ሰአት በፊት የኬንያ ጦር አዛዥ ጄኔራል ፍራንሲስ ኦሞንዲ ኦጎላ በምዕራብ የአገሪቱ ክፍል ይበሩበት የነበረው ወታደራዊ ሄሊኮፕተር ተከስክሶ ሕይወታቸው ማለፉን ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ አስታወቁ። ኦጎላ ከሌሎች 11 ወታደራዊ መኮንኖች ጋር ሆነው በሄሊኮፕተሩ ሲጓዙ ነው አደጋው የደረሰው። ከአደጋው የተረፉት ሁለት ሰዎች ብቻ ናቸው። ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ ሐሙስ ምሽት በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ አደጋው ለአገሪቱ “ትልቅ ሐዘን” […]

የዩክሬን ፕሬዝዳንትን ለመግደል ከሩሲያ ጋር ሲያሴር ነበር የተባለ ግለሰብ ፖላንድ ውስጥ ተያዘ

ከ 4 ሰአት በፊት የዩክሬን ፕሬዝዳንት ቭሎድሚር ዜሌንስኪን ለመግደል ከሩሲያ የደኅንነት አገልግሎት ጋር አሲሯል የተባለ ግለሰብ ፖላንድ ውስጥ በቁጥጥር ስር ዋለ። የፖላንድ ዐቃቤ ሕግ ፓዌል ኬ የተባለው ግለሰብ የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ፖላንድ ውስጥ ያለ አብዝተው ስለሚጠቀሙበት አየር ማረፊያ መረጃ እንዲሰበስብ ከሩሲያ ኃላፊነት ተሰጥቶታል ብሏል። ግለሰቡ በቁጥጥር ስር የዋለው የዩክሬን የደኅንነት መሥሪያ ቤት ለፖላንድ መንግሥት ጥቆማ ከሰጠ […]

ከአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የተሰጠ መግለጫ

Amhara Prosperity Party /APP/    ·  ከአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የተሰጠ መግለጫ ከትናንት ታሪካዊ ስህተቱ መማር የተሳነው ሕዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ (ህወሓት) የፕሪቶሪያውን ስምምነት ሙሉ በሙሉ በመጣስ ለአራተኛ ዙር ሕዝባችን ላይ ወረራ ፈፅሟል፡፡ ጀንበር ጠልቃ በወጣች ቁጥር ከጦርነት ውጭ ማሰብ የማይችለው የህወሓት ቡድን ከዉጭ እና ከዉስጥ ጠላቶቻችን ጋር ተናቦና ተቀናጅቶ በእርካሽ ፖለቲካዊ ብያኔና ፍረጃ በጊዜያዊ አሥተዳደሩ […]

ማንነቱንና ርስቱን አሳልፎ የሚሰጥ ትውልድ ኖሮም አያውቅም አይኖርምም – የሰብአዊ መብት ድርጅቶች የጋራ መግለጫ

Press Release Posted on 2024-04-15 Author rayaman   “ሆድ ሳያውቅ ዶሮ ማታ” እንዲሉ ወልቃይት ጠገዴ፤ ጠለምት፤ ራያ ያማነው? የሚለው ጥያቄ ጊዜው ያለፈበት ጥያቄ የሚያደርገው መልሱ በሁሉም ዘንድ የታወቀና የተመሰከረለት መሆኑ ብቻ ሳይሆን ዛሬ ህዝባችን ለዘመናት ባደረገው መራራ ትግልና በከፈለው ክቡር መስዋዕትነት ከትህነግ/ወያኔ ወረራ ነፃ የወጣና በልጆቹ እየተስተዳደረ የሚገኝ በመሆኑ ጭምር ነው። ሙሉ መግለጫውን ለማንበብ …

በህወሓት የተቀሰቀሰው ጦርነት በአስቸኳይ ይቁም!

Posted on 2024-04-18  ከኢሕአፓ የድጋፍ አስተባባሪ ኮሚቴ የተሰጠ መግለጫ የብልጽግና አገዛዝና ህወሓት በትግራይ፤ በአማራና በአፋር ክልሎች በሚሊዮን የሚገመተውን የወገኖቻችንን ነፍስ የቀጠፈውንና ሚሊዮኖችን ከቀያቸው ያፈናቀለውን ጦርነት ለሁለት ዓመታት ካካሄዱ በኋላ ዳግም ሌላ ጦርነትን ያደርጋሉ ተብሎ አይታሰብም ነበር፡፡ ሕዝባችን በታሪኩ አይቶት የማያውቀው ረሃብና ድህነት እያሰቃየው ባለበት በአሁኑ ወቅት ለሌላ ጦርነት መነሳታቸው እጅግ አሳዛኝ ክስተት ነው። የትግራይና የአማራ ሕዝብ […]