እራሱን ‘የእግዚአብሔር ልጅ’ እያለ የሚጠራው ፓስተር በሕጻናት የወሲብ ንግድ ወንጀል በቁጥጥር ስር ዋለ

ከ 3 ሰአት በፊት ሕጻናትን ለወሲብ ንግድ በማዘዋወር በፊሊፒንስ እና በአሜሪካ በጥብቅ ሲፈለግ የነበረው ተፅዕኖ ፈጣሪው ፓስተር በቁጥጥር ስር ዋለ። ፖሊስ እራሱን ‘የእግዚአብሔር ልጅ’ እያለ የሚገልጸውን ፊሊፒንሳዊውን አፖሎ ኩይቦሎይን በቁጥጥር ሥር ለማዋል የሚሰብክበትን ቤተክርስቲያን ለሁለት ሳምንት ያህል ከቦ ቆይቷል። በዚህም ምክንያት በሺዎች በሚቆጠሩ ተከታዮቹ እና በፖሊስ መካከል ውጥረት ተፈጥሮ የነበረ ሲሆን አንድ የቤተክርስቲያኑ አባል በልብ […]

በሕይወት ትርጉም ማግኘት ለአእምሮ ጤና የሚሰጠው ጥቅም

ከ 5 ሰአት በፊት አኪላ ሻኪህ በ19 ዓመቷ ልጅ ከወለደች በኋላ ሰዎችን የመንከባከብ ሙያ ውስጥ ገባች። በየቤቱ ለሰዎች እንክብካቤ መስጠት “ለኔ የተሰጠ ሙያ እንደሆነ አወቅኩ” ትላለች። ሥራው ግን አድካሚ ነው። ሕሙማንን ማንቀሳቀስ፣ አልጋ መግፋት፣ ቀኑን ሙሉ መቆም ይጠይቃል። ጀርባዋን መታመም የጀመረችው በሥራዋ ምክንያት ነው። ሕመሙ ሲበረታባት የሐኪሞችን ምክር ሰምታ ሥራውን አቆመች። ሆኖም እረፍት ማድረጓ ሕመሟን […]

በናይጄሪያ ነዳጅ ጫኝ ቦቴ ከሌላ መኪና ጋር ተጋጭቶ ቢያንስ 48 ሰዎች ሞቱ

ከ 4 ሰአት በፊት በናይጄሪያ ማዕከላዊ ግዛት ኒጀር አንድ ነዳጅ ጫኝ ተሽከርካሪ ሰዎች እና የቁም እንስሳትን ከጫነ መኪና ጋር ተጋጭቶ ቢያንስ 48 ሰዎች መሞታቸው ተገለጸ። በሁለቱ መኪኖች ግጭት የተነሳው ከባድ ቃጠሎ ለሰዎች እና እንስሳት ሞት ምክንያት መሆኑን የአገሪቱ የአደጋ ጊዜ አስተዳደር ኤጀንሲ አስታውቋል። ኤጀንሲው ይህ አደጋ ያጋጠመው ትላንት ዕሁድ እንደነበር ገልጾ ሁለቱ ተሽከርካሪዎች ሲጋጩ ከፍተኛ […]