በሊባኖስ ላይ እስራኤል በፈፀመችው የአየር ጥቃት ቢያንስ 100 ሰዎች መገደላቸው ተገለጸ

23 መስከረም 2024, 15:11 EAT እስራኤል ዛሬ በሊባኖስ ላይ በፈጸመችው የአየር ጥቃት ቢያንስ 100 ሰዎች መገደላቸውን የሊባኖስ የጤና ሚኒስትር አስታወቀ። በጥቃቱ ከ400 በላይ ሰዎች ጉዳት እንደደረሰባቸውም ተገልጿል። የሊባኖስ የሕብረተሰብ ጤና ሚኒስትር ባወጣው መግለጫ በአገሪቱ ደቡባዊ ክፍል ያሉ ሆስፒታሎች ከአጣዳፊ ቀዶ ሕክምና ውጪ ያሉ አገልግሎቶችን እንዲሰርዙ አሳስቧል። የሕክምና ባለሙያዎች ወደ ድንገተኛ ክፍል የሚወሰዱ ተጎጂዎችን ለማከም እንዲጠባበቁ […]

ሶማሊያ ከባድ የጦር መሳሪያዎችን ከግብፅ ማግኘቷ ተነገረ

23 መስከረም 2024, 15:16 EAT ሶማሊያ የተለያዩ ከባድ የጦር መሳሪያዎች ከግብፅ እንደተሰጧት እና ተጨማሪ መሳሪያዎችን በቀጣይነት እንደምትጠብቅ አንድ የሶማሊያ ከፍተኛ ባለሥልጣን አረጋገጡ። ስማቸው ሳይጠቀስ ለቢቢሲ ሶማሊኛ የተናገሩት ባለሥልጣን ባለፉት ቀናት በመርከብ ተጭነው ወደ ሞቃዲሾ ወደብ የደረሱት የጦር መሳሪያዎች የሶማሊያ መንግሥት ጦር የሚታጠቃቸው መሆኑን አመልክተዋል። ወደ ሶማሊያ የገቡት የጦር መሳሪያዎች ፀረ አውሮፕላን ሚሳኤሎች፣ መድፎች እና ሌሎች […]

ጌታቸው ረዳ ደብረፂሆንን ማስጠንቀቅ ቀጥሏል

September 23, 2024 – Konjit Sitotaw  የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር፣ ባኹኑ ወቅት በትግራይ ያለው ችግር በሕወሓትና በጊዜያዊ አስተዳደሩ መካከል ሳይኾን በሕወሓት ከፍተኛ አመራሮች መካከል የተፈጠረ ክፍፍል ነው ሲል ትናንት ምሽት አስታውቋል። የሕወሓት አመራር ክፍፍል በአስተዳደሩ መዋቅር ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ ማሳደሩን ያመነው አስተዳደሩ፣ የጊዜያዊ አስተዳደሩን ውሳኔዎች ለመሻር ወይም መዋቅሮቹን ለማዳከም በሚደረጉ ሙከራዎች ላይ ግን ሕጋዊ ርምጃ እወስዳለኹ በማለት አስጠንቅቋል። […]

የጋዜጠኞች ሥደት እና የመብት ተሟጋች ድርጅቱ ጥሪ

September 23, 2024 – DW Amharic  የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ተሟጋቾች ማዕከል ጋዜጠኞች እና የሰብአዊ መብቶች ተሟጋቾች እየገጠማቸው ነው ያለው ወከባ፣ እሥር፣ እንግልትና ማስፈራሪያ እየጨመረ መምጣት ​”በእጅጉ” እንዳሳሰበው አስታወቀ። የኢትዮ ኒውስ እና አልፋ ሚዲያ የበይነ መረብ ብዙኃን መገናኛዎች መሥራቾች በላይ ማናዬ እና በቃሉ አላምረው ከኢትዮጵያ መሰደዳቸውን ገልጸዋል… … ሙሉውን ለማየት ወይም ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ

እያሽቆለቆለ ለመጣው የተማሪዎች ውጤት እና የትምህርት ጥራት መፍትሄ ይኖረው ይሆን?

September 23, 2024 – DW Amharic  በኢትዮጵያ ባለፉት ተከታታይ ሶስት ዓመታት በ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ላይ እየተመዘገበ ያለው ውጤት ብዙዎችን እያሳሰበ ነው። በስርዓተ ትምህርቱ ፣በትምህርት ጥራት እና አሰጣጥ ላይም ጥያቄ እንዲነሳ እያደረገ ነው። ታዲያ የችግሩ መንስኤ ምንድነው? ተማሪዎች መምህራን ወይስ ስርዓተ ትምህርቱ?መፍትሄውስ?… … ሙሉውን ለማየት ወይም ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ

የአንጋፋው ጋዜጠኛ ጌታቸው ኃይለማሪያም የ30ኛ ዓመት ህልፍተ ህይወት መታሰቢያ ተካሔደ

September 22, 2024 – DW Amharic  ጋዜጠኛ ጌታቸው ኃይለማርያም በኢትዮጵያ ራዲዮ እና ቴሌቭዥን በተለያዩ ኃላፊነቶች ያገለገለ የዶይቼ ቬለው ነጋሽ መሐመድን ጨምሮ አንጋፋ ባለሙያዎች በክብር የሚያስታውሱት ባለሙያ ነበር። በዜና አጻጻፍ እና አቀራረብ የተለየ ክህሎት እንደነበረው የሚነገርለት ጌታቸው ጋዜጠኞች የመስክ ዘገባ እንዲሰሩ በማድረግ ላቅ ያለ አስተዋጽዖ አርክቷል።… … ሙሉውን ለማየት ወይም ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ