የጋምቤላ ክልል ላልተወሰነ ጊዜ የሚቆይ የሰዓት እላፊ ገደብ ጣለ

20 ሀምሌ 2023, 10:18 EAT የጋምቤላ ክልላዊ መንግሥት ከዛሬ ሐምሌ 13/2015 ዓ.ም ጀምሮ ተግባራዊ የሚሆን ላልተወሰነ ጊዜ የሚቆይ ክልላዊ የሰዓት እላፊ መጣሉን አስታወቀ። በክልሉ በአዲስ መልክ ተቀስቅሶ የሰዎች ህይወት መጥፋቱ መዘገቡንም ተከትሎ ነው በምሽት ሰዓታት የመንቀሳቀስ ገደብ የተጣለው። በሰዓት እላፊው መሰረት ከምሽቱ 1፡00 ሰዓት ጀምሮ እስከ ንጋቱ 12 ሰዓትንም መንቀሳቀስም ተከልክሏል። በስራ ላይ ከተሰማሩ የጸጥታ […]

ኢንስትራክተር ሠላም፡ የሉሲዎቹ የቀድሞ አሰልጣኝ የላይቤርያ ብሔራዊ ቡድንን በኃላፊነት ተረከበች

20 ሀምሌ 2023, 07:15 EAT ኢንስትራክተር ሠላም ዘርዓይ የላይቤርያ የሴቶች ብሔራዊ ቡድን ዋና አሰልጣኝ በመሆን ፊርማዋን ማኖሯን ለቢቢሲ ገለፀች። የቀድሞ የኢትዮጵያ የሴቶች ብሔራዊ ቡድን ቡድን ዋና አሰልጣኝ፣ ኢንስትራክተር ሠላም የላይቤሪያ የሴቶች ብሔራዊ ቡድንን በዋና አሰልጣኝነት ለሦስት ዓመት ለመምራት ፊርማዋን ማኖሯን ተናግራለች። የቅዱስ ጊዮርጊስ የሴቶች ቡድን እና የወንዶች ተስፋ ቡድን አሰልጣኝ የነበረችው ሠላም፤ የኢትዮጵያ ሴቶች ብሔራዊ […]

በጠለፋ ዙሪያ የሚካሄድ ባሕላዊ ሽምግልና ከኢትዮጵያ ሕግ ጋር ይቃረናል?

20 ሀምሌ 2023 የስምንተኛ ክፍል ተማሪ እያለች በ13 ዓመቷ የተጠለፈችው ደጊቱ ዳቃሟ፤ በጠለፋት ግለሰብ ጥቃት እየደረሰባት ለሁለት ወር ያህል ጫካ ውስጥ አሳልፋለች። የወሲብ ጥቃት ጨምሮ ከደረሰባት የአካል ጉዳት በተጨማሪ የሥነ ልቦና ጉዳቱም ቀላል አልነበረም። በደሉን የፈጸማበት ግለሰብ ሽማግሌዎችን ወደ ቤተሰቦቿ በመላክ እርቅ ይፈጽማል፤ በኋላም ወደ ቤቱ ይዟት ይገባል። ጉዳት ካደረሰባት ግለሰብ ጋር ትዳር እንድትመሠረት የተገደደችው […]

አሜሪካ የጠፋባትን ወታደር ለመፈለግ ወደ ሰሜን ኮሪያ የደወለችው ስልክ አለመነሳቱን ገለጸች

20 ሀምሌ 2023, 16:16 EAT ያለ ፈቃድ ወደ ሰሜን ኮሪያ ግዛት የገባውን የአሜሪካ ወታደር በተመለከተ ለመደራደር አሜሪካ ያደረገችው የስልክ ጥሪ በሰሜን ኮሪያ በኩል ምላሽ ሳያገኝ መቅረቱን አሜሪካ ገልጻለች። ትራቪስ ኪንግ የተባለው የአሜሪካ ወታደር ወደ ሰሜን ኮሪያ ግዛት ዘልቆ የገባው ባለፈው ማክሰኞ ነበር። ስለወታደሩ ዕጣ ፈንታም ሆነ ያለበትን ሁኔታ ለማወቅ ከሰሜን ኮሪያ በኩል ስልክ ባለመነሳቱ ለማወቅ […]

ሩሲያ ወደ ዩክሬን የሚያመሩ መርከቦችን በተመለከተ በሰጠችው ማስጠንቀቂያ የስንዴ ዋጋ ናረ

20 ሀምሌ 2023, 08:55 EAT ሩሲያ ወደ ዩክሬን ወደቦች የሚያመሩ መርከቦችን በተመለከተ ማስጠንቀቂያ ማስተላለፏን ተከትሎ ዓለም አቀፉ የስንዴ ዋጋ በከፍተኛ ሁኔታ ጨመረ። ሩሲያ እነዚህን መርከቦች እንደ ወታደራዊ ኢላማም ሊቆጠሩ ይችላሉ የሚል ማስጠንቀቂያም ነው ያስተላለፈችው። በዚህ ሳምንት በጥቁር ባህር በኩል እህል ደህንነቱ በተጠበቀ መልኩ ለማጓጓዝ ከሚያስችለው ስምምነትም እንደወጣች ሩሲያ አስታውቃለች። ሩሲያ በእቃ ጫኝ መርከቦች ላይ ለሚደርስ […]

የቫግነሩ መሪ ቤላሩስ ገብተው ለወታደሮቻቸው “ንግግር ሲያደርጉ ታዩ”

20 ሀምሌ 2023, 09:56 EAT በቴሌግራም ቻናል የተለቀቀ አንድ ምስል የቫግነሩ መሪ ቤላሩስ ገብተው ከታጣቂዎቻቸው ጋር ሲወያዩ አስመልክቷል። የቭገኒ ፕሪጎዢን ወታደሮቹን ሲቀበል፤ ቀጥሎ ደግሞ በዩክሬን ጦርነት እየሆነ ያለው “አሳፋሪ” ነው ሲል ይደመጣል። ግለሰቡ እንደሚጠቁመው የቫግነር ቅጥረኛ ወታደሮች በቅርቡ ጦርነቱን ሊቀላቀሉ ይችላሉ። ከዚህ ቀደም ቤላሩስ የቫግነር ወታደሮች ለሃገሪቱ ጦር አማካሪና አሠልጣኝ ሆነው ያገለግላሉ ያለችውንም ያረጋገጠ ምስል […]

ኒውዚላንድ የዓለም ዋንጫ ልታሰናዳ ሰዓታት ሲቀሯት በተከፈተ ተኩስ ሁለት ሰዎች ተገደሉ

20 ሀምሌ 2023, 07:52 EAT በኒውዚሏንዷ ኦክላንድ ከተማ አንድ ታጣቂ በከፈተው ተኩስ ምክንያት ሁለት ሰዎች ተገድለዋል። ከተማዋ የሴቶች የዓለም ዋንጫ ለማሰናዳት ደፋ ቀና እያለች ባለችበት ወቅት ነው ይህ የሆነው። አንድ የፖሊስ መኮንንን ጨምሮ ስድስት ሰዎች ጉዳት የደረሰባቸው ሲሆን ታጣቂውም መገደሉ ተገልጧል። ጠቅላይ ሚኒስትር ክሪስ ሂፕኪንስ ጥቃቱ እንደ የሽብር ተግባር የሚታይ አይደለም ብለዋል። አክለው የሴቶች የዓለም […]

የሰው ሠራሽ አስተውሎት (ኤአይ) ምንነት አጭር ማብራሪያ

የሰው ሠራሽ አስተውሎት (ኤአይ) ምንነት አጭር ማብራሪያ  አኒሜሽኑን ያስጀምሩ ከዚህ ቀደም ስለ ሰው ሠራሽ አስተውሎት (ኤአይ) አስበው ያውቃሉ? ባለፉት ስድስት ወራት እንደ ቻትጂፒቲ ያሉ ቻትቦቶች እንዲሁም የምስል ማፍለቂያ የሆኑ እንደ ሚድጆርኒ ያሉ የቴክኖሎጂ ውጤቶች ትኩረትን ስበዋል። ይሁን እንጂ ኤአይ ወይም “ማሽን ለርኒንግ” [ማሽንን የማስተማር] ሥርዓቶች ጥቅም ላይ መዋል ከጀመሩ ሰነባብተዋል። በዚህ ለጀማሪ ተብሎ በተዘጋጀ ቀላል […]

1.4 ሚሊዮን ፓውንድ የሚያወጣ የሴልቲክ ወርቅ ሳንቲም ሰርቀዋል የተባሉ ግለሰቦች ታሠሩ

ከ 4 ሰአት በፊት 1.4 ሚሊዮን ፓውንድ የሚያወጣ የሴልቲክ የወርቅ ሳንቲም ሰርቀዋል የተባሉት አራት ሰዎች ጀርመን ውስጥ በቁጥጥር ሥር ውለዋል። ባለፈው ኅዳር አንድ ምሽት በመቶዎች የሚቆጠሩ ሳንቲሞች ባቫሪያ ከሚገኝ አንድ ሙዚየም ተወስደዋል። አብዛኛዎቹ ሳንቲሞች በአንደኛው ክፍለ ዘመን የተሠሩ ናቸው። ባለሥልጣናት እንደሚሉት “ከበቂ በላይ ማስረጃ ተገኝቷል”፤ ምርመራውም እንደቀጠለ ነው። የወርቅ ሳንቲሞቹ ተገኝተዋል ወይ የሚለውን ጥያቄ ለመመለስ […]

በኬንያው ጸረ መንግሥት የአደባባይ ተቃውሞ ሁለት ሰዎች ተገደሉ

ከ 5 ሰአት በፊት በኬንያ መንግሥት የጣለውን የግብር ጭማሬ ለመቃወም በወጡ ሰልፈኞች እና በፖሊስ መካከል በተፈጠረ ግጭት ሁለት ሰዎች ተገደሉ። የሁለቱ ሰዎች ህይወት ያለፈው ረቡዕ ሐምሌ 13/ 2015 ዓ.ም ኪሱሙ ከተማ በነበረው የአደባባይ ተቃውሞ ነው። በመዲናዋ ናይሮቢ እና በባህር ዳርቻዋ ከተማ ሞምባሳም የኑሮ ውድነት በከፋበት መንግሥት የጣለውን የግብር ጭማሬ ለመቃወም በወጡ ሰልፈኞችም ላይ ፖሊስ አስለቃሽ […]