የእስራኤል እግረኛ ጦር ጋዛ ሲገባ ከሐማስ ምን ሊገጥመው ይችላል?

ከ 5 ሰአት በፊት እስራኤል ጋዛን በአየር ስትደበድብ ከሁለት ሳምንት በላይ ሆኗታል። በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ወታደሮቿንም በጋዛ ድንበር አቅራቢያ አሰባስባ፣ በጋዛ ላይ ወረራ ለመፈጸም እየተዘገጀች ነው። እስራኤል ከሐማስ የተቃጣባትን መብረቃዊ ጥቃት ለመበቀል ነው የተነሳችው። ሐማስን ከምድረ ገጽ ሳላጠፋ አልመለስም ስትል ዝታለች። አሁን የሚጠበቀውም፣ የሚፈራውም እግረኛ ሠራዊት ወደ ጋዛ ሲገባ እዚያ ምን ሊፈጠር ይችላል የሚለው ነው። […]

በአሜሪካ በተከፈተ ተኩስ ቢያንስ 16 ሰዎች መገደላቸው ተገለጸ

ከ 1 ሰአት በፊት በአሜሪካዋ ሊዊስተን ከተማ፣ ሜይን ቢያንስ 16 ሰዎች መገደላቸው ተገለጸ። አንድ ግለሰብ ተኩስ ከፍቶ ነው ሰዎቹ የተገደሉት። ትላንት በቦሊንግ መጫወቻና ሬስቶራንት አቅራቢያ ተኩሱ መከፈቱ የተገለጸ ሲሆን፣ ተኩሱን የከፈተው ሰው ፍለጋ እየተካሄደ ይገኛል። የሊዊስተን ነዋሪዎችና በአቅራቢያው ሊዝበን የሚኖሩ ሰዎችን ከለላ እንዲያገኙ ተነግሯቸዋል። ፖሊስ ተጠርጣሪው የ40 ዓመቱ ሮበርት ካርድ እንደሆነ ገልጿል። ግለሰቡ “የታጠቀና አደገኛ […]

ሩሲያ ‘ግዙፍ’ የኒውክሌር ጥቃት ልምምድ ማድረጓን አስታወቀች

ከ 4 ሰአት በፊት ሩሲያ “ግዙፍ” የኒውክሌር ጥቃት የማድረስ አቅሟን የሚፈትሽ ልምምድ ማከናወኗን አስታወቀች። ወታደራዊ ልምምዱ ለጠላት የኒውክለር ጥቃት ምላሽ መስጠትን እንደሚያካትት የመከላከያ ሚንስትሩ ሰርጌይ ሾይጉ አስታውቀዋል። ሚንስትሩ ለፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ልምምዱን በተመለከተ ማብራሪያ ሲሰጡ በመንግስታዊው ቴሌቭዥን ታይተዋል። ሞስኮ የኒውክለር መሣሪያዎችን እንዳትሞክር ከሚያግዳት ዓለም አቀፍ ስምምነት መውጣቷ በአገሪቱ ፓርላማ ማጽደቁን ተከትሎ የተደረገ ልምምድ መሆኑ ተሰምቷል። […]

እስራኤል ‘አሸባሪ አገር’ ናት ያለችው አየርላንዳዊት ከሥራ ተባረረች

ከ 4 ሰአት በፊት ኮርኒ ኬሪ የተባለች አየርላንዳዊት እስራኤል “አሸባሪ አገር ናት” ብላ ማኅበራዊ ሚዲያ ላይ በመጻፏ ከአየርላንድ የቴክኖሎጂ ተቋም ተባረረች። የአየርላንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ሊዮ ቫራድካር ከሥራ የተባረረችው በፖለቲካዊ አቋሟ እንደሆነ ካመነች ጉዳዩን ወደ ሕግ አካል እንድትወስደው ነግረዋል። ዊክስ ከሚባል የቴክኖሎጂ ተቋም ነው የተባረረችው። በደብሊን ወደ 500 የሚጠጉ ሠራተኞች አሉት። ኮርኒ ኋላ ላይ ማንኛውም ነውጥ […]

በወርቅ ማዕድን ጉድጓድ በገዛ ባልደረቦቻቸው ታግተው የነበሩ ሠራተኞች ተለቀቁ

ከ 4 ሰአት በፊት በደቡብ አፍሪካ በወርቅ ማውጫ ጉድጓድ በባልደረቦቻቸው ለቀናት ታግተው የነበሩ ወርቅ ቆፋሪዎች ተለቀቁ። የወርቅ ማዕድን አውጪዎቹ ላለፉት ሦስት ቀናት በመጥፋታቸው በደቡብ አፍሪካ ጉዳዩ አነጋጋሪ ሆኖ ነበር። አጋቾቹ ልዩ ልዩ ከቁፋሮ ጋር የተያያዙ መሣሪያዎችን በመያዝ ታጋቾቹን አስፈራርተዋል ተብሏል። ጎልድዋን በሚባለው የማዕድን ቁፋሮ ማዕከል ነው ክስተቱ የተፈጠረው። ከእገታው አምልጠን ነው የወጣነው ካሉት መካከል አንዱ […]

በአውሮፓ ሃገራት ጥቁሮች ላይ ያነጣጠረ ዘረኝነት “በአሳፋሪ” ሁኔታ እየጨመረ ነው

ከ 4 ሰአት በፊት የአውሮፓ ሕብረት መሠረታዊ መብቶች ኤጀንሲ ባወጣው ዘገባ አፍሪካዊያን ላይ የሚደርሰው የዘረኝነት ጥቃት እየጨመረ መምጣቱን አሳይቷል። በ13 የአውሮፓ ሃገራት የሚኖሩ ጥቁር ሕዝቦች የተካተቱበት ይህ ጥናት እንደጠቆሞው ጥቁሮች መገለልና ጥቃት እየደረሰባቸው ነው “የዕለተ ዕለት ኑሯቸውን የሚገፉት።” መሰል ጥናት ከተሰራበት 2018 ጀምሮ ባለው ጊዜ በተለይ በጀርመን መገለል የሚደርስባቸው ሰዎች ቁጥር ጨምሯል። የጥናቱ ውጤት “ማንቂያ […]

የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የተግባር ላይ ልምምድ በወጪ መጋራት ውስጥ እንዲካተት ጥናት መጀመሩ ተገለጸ

ማኅበራዊ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የተግባር ላይ ልምምድ በወጪ መጋራት ውስጥ እንዲካተት ጥናት መጀመሩ ተገለጸ ሲሳይ ሳህሉ ቀን: October 25, 2023 የመንግሥት ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በክፍል ውስጥ ከሚማሩት ትምህርት ውጪ ወደ ተለያዩ ኢንዱስትሪዎች ሄደው ለሚያደርጓቸው የተግባር ላይ ልምምዶች የሚደረግ ወጪ፣ ከምርቃት በኋላ በሚከፍሉት የወጪ መጋራት ውስጥ እንዲካተት ጥናት መጀመሩ ተገለጸ፡፡ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የወጪ መጋራት (Cost Sharing) መመርያ […]

‹‹በኑሮ ውድነቱ መሰለኝ ድጋፍ ስንጠይቅ በጎ ምላሽ አናገኝም›› አቶ ገዛኸኝ ሲሳይ፣ የበርቶሎሚዎስ በጎ አድራጎት ድርጅት ዋና ሥራ አስኪያጅ

ተመስገን ተጋፋው October 25, 2023 ምን እየሰሩ ነው? በኢትዮጵያ ቁጥራቸው ከፍተኛ የሆኑ አረጋውያን፣ ሕፃናትና እናቶች ጎዳና ወጥተው ምፅዋት ሲጠይቁ ማየት የተለመደ ሆኗል፡፡ የኑሮ ውድነት እንዲሁም በአገሪቱ የሚስተዋው አጠቃላይ ችግር ጎዳና ወጥተው ምፅዋት የሚጠይቁ ወገኖች በርካታ እንዲሆኑ ምክንያት መሆኑ በተደጋጋሚ ይነገራል፡፡ እነዚህን ምፅዋት የሚጠይቁ ወገኖች ከጎዳና ለማንሳት መንግሥትም ሆነ መንግሥታዊ ያልሆኑ ተቋማት እየሠሩ ቢሆንም፣ ችግሩ ግን […]

ትንሿ ምላጭ ዓለምን ትላጭ…

ልናገር ትንሿ ምላጭ ዓለምን ትላጭ… አንባቢ ቀን: October 25, 2023 በመኮንን ሻውል ወልደ ጊዮርጊስ የእስራኤልና የሃማስ ጦርነት ቀስ እያለ ጎራ እየፈጠረ መሄዱ አይቀሬ ነው። ለምን ብትሉ “በመብረቃዊው” የሃማስ ጥቃት ከእስራኤል ይልቅ አሜሪካ በእጅጉ ደንግጣለች። እናም፣ ‹‹እነዚህ ሰዎች በድሮ ዘመን ግንኙነት ሴራ እየሸረቡ ከሆነ ማንም ሊደርስባቸው አይችልም። እኛ በድሮ ዘመን ስለሌላ ሰው አስርገን ለማስገባትም ረፍዶብናል። ሰዓቱ […]