የነዳጅ ዋጋ እያሻቀበ ለረጅም ጊዜ ሊቆይ ይችላል ሲሉ የነዳጅ ላኪዎች ህብረት መሪ አስጠነቀቁ

ከ 9 ሰአት በፊት ለሃይል አቅርቦት ያለው ፍላጎት በመጨመሩ የነደጅ ዋጋ እንዳሻቀበ ይቀጥላል ሲሉ ‘ኦፔክ ፕላስ’ ዋና ጸሀፊ ተናገሩ። ‘ኦፔክ ፕላስ’ የ23 ነዳጅ ላኪ ሀገራት ህብረት ሲሆን በዓለም ገበያ ላይ የሚቀርበውን የድፍድፍ ነዳጅ መጠን የሚወስን ነው። ዋና ጸሃፊው ሄይታም አል ጋሂስ “በቀን የነዳጅ ፍላጎት ወደ 2.4 ሚሊዮን በርሜል ሲያድግ እየተመለከትን ነው” ሲሉ ለቢቢሲ ገልጸዋል። ሳዑዲ […]

ለኮቪድ ክትባት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያበረከቱ ሁለት ሳይንቲስቶች የኖቤል ሽልማትን አሸነፉ

2 ጥቅምት 2023 የኖቤል የጤና እና የፊዚዮሎጂ ሽልማት ኤምአርኤንኤ የተባለውን የኮቪድ ክትባትን ለመሥራት የሚያስችል ቴክኖሎጂን ላዳበሩ ሁለት ሳይንቲስቶች በጋራ ተሰጠ። ፕሮፌሰር ካታሊን ካሪኮ እና ፕሮፌሰር ድሪው ዋይስማን የዚህን ዓመት የኖቤል የጤና ሽልማትን በጋራ ማግኘታቸው ይፋ ሆኗል። ቴክኖሎጂው የኮቪድ ወረርሽኝ ከመከሰቱ በፊት በሙከራ ደረጃ ላይ የነበረ ሲሆን፣ አሁን በዓለም ዙሪያ በሚሊዮኖች ለሚቆጠሩ ሰዎች ወረርሽኙን ለመከላከል ተስጥቷል። […]

በሶማሊ እና ኦሮሚያ ክልል የፀጥታ ኃይሎች ግጭት ነዋሪዎች መጎዳታቸውን ኢሰመኮ ገለጸ

2 ጥቅምት 2023 በሶማሊ እና በኦሮሚያ ክልል የፀጥታ ኃይሎች መካከል በመስከረም ወር መጀመሪያ ላይ በተከሰተ ግጭት ምክንያት በሰዎች ላይ የደረሰው የሞት እና የአካል ጉዳት አንዳሳሰበው የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ገለጸ። የሁለቱ ክልሎች አዋሳኝ በሆነው እና ከባቢሌ አቅራቢያ በሚገኝ ስፍራ ሰኞ መስከረም 07/2016 ዓ.ም. በኦሮሚያ እና በሶማሊ ክልል የፀጥታ ኃይሎች መካከል በተፈጠረው ግጭት በአካባቢው የተጠለሉ […]

የዓለም ጤና ድርጅት ሁለተኛ የወባ ክትባት ለሕጻናት እንዲሰጥ ፈቀደ

October 3, 2023 – VOA Amharic  የዓለም ጤና ድርጅት ለወባ በሽታ መከላከያ የሚኾን ዐዲስ አማራጭ ክትባት ለሕጻናት እንዲሰጥ ፈቀደ። በእንግሊዝ ኦክስፎርድ ዩኒቨርስቲ የበለጸገው R21/Matrix M የተሰኘው ክትባት፣ በህንድ ሴረም ተቋም የተመረተ ሲሆን፣ በቡርኪና ፋሶ፣ ጋና እና ናይጄሪያ ጥቅም ላይ እንዲውል የዓለም ጤና ድርጅቱ ፈቅዷል። “በወባ በሽታ ላይ ምርምር በማደርግበት ወቅት ውጤታማ ክትባት እንዲኖር አልም ነበር… … ሙሉውን […]

ኬንያ በአንድ ዓመት ውስጥ 860 ሚሊዮን የመረጃ መረብ ጥቃት እንዳጋጠማት አስታወቀች

ከ 54 ደቂቃዎች በፊት ባለፉት አስራ ሁለት ወራት ውስጥ ኬንያ እጅግ ከፍተኛ ቁጥር ነው የተባለ የመረጃ መረብ ጥቃት እንዳጋጠማት የአገሪቱ የኮምዩኒኬሽን አገልግሎት ተቆጣጣሪ አካል አስታወቀ። ባለሥልጣኑ እንዳለው አንድ ዓመት በሚሆን ጊዜ ውስጥ 860 ሚሊዮን የመረጃ መረብ ጥቃቶች የተፈጸሙ ሲሆን፣ የጥቃቶቹ “ድግግሞሽ፣ ረቂቅነት እና በመረጃ ደኅንነት ላይ የደቀኑት ስጋት መጠን” በኬንያ ወሳኝ የመረጃ መረብ መሠረተ ልማቶች […]

በዋግ ኽምራ እና በሰሜን ጎንደር ዞኖች በተከሰተው ድርቅ ቢያንስ የ34 ሰዎች ሕይወት ማለፉን ባለሥልጣናት አስታወቁ

ከ 4 ሰአት በፊት በአማራ ክልል በሚገኙት የዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር እና የሰሜን ጎንደር ዞኖች በተከሰተው ድርቅ ቢያንስ የ34 ሰዎች ሕይወት ማለፉን የዞኑ ባለሥልጣናት ተናገሩ። የዞኖቹ የአደጋ መከላከል እና ምግብ ዋስትና ጽ/ቤት ኃላፊዎች ለቢቢሲ እንደተናገሩት፣ ባለፈው ዓመት ይጠበቅ የነበረው ዝናብ ባለመዝነቡ በተከሰተው ድርቅ ከጠፋው የሰው ሕይወት ባሻገር ከ54 ሺህ በላይ የቤት እንስሳት ሞተዋል። የሰሜን ጎንደር […]

ካርቱም በሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ላይ የከባድ መሣሪያ ጥቃት ተፈጸመበት

ከ 3 ሰአት በፊት ሱዳን ካርቱም ውስጥ በሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ላይ በተፈጸመ የከባድ መሣሪያ ጥቃት ጉዳት መድረሱን የቢቢሲ ዲፕሎማቲክ ምንጭ ተናገሩ። ለወራት በጦርነት ውስጥ በቆየችው ሱዳን ዋና ከተማ በሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ላይ የከባድ መሣሪያ ጥቃቱ የደረሰው ዛሬ ማክሰኞ መስከረም 22/2016 ዓ.ም. ጠዋት ላይ ነው። የከባድ መሣሪያ ጥቃቱ በኤምባሲው ሕንጻ እና ንብረት ላይ ውድመት ያደረሰ ሲሆን፣ […]

የዛሬ 10 ዓመት በኤርትራውያን ስደተኞች ላይ የደረሰው የላምፔዱዛው እልቂት

3 ጥቅምት 2023 ልክ የዛሬ 10 ዓመት፣ በዕለተ ሐሙስ እኤአ ጥቅምት 03 ቀን 2013፣ 368 ኤርትራውያን ስደተኞች በላምፔዱዛ የባሕር ዳርቻ በጀልባ አደጋ ሞቱ። ሟቾቹ ከቀናት በፊት ጉዞ መጀመራቸውን በስልክ የነገሯቸው ዘመዶቻቸው እና ጓደኞቻቸው “በሰላም ገብተናል” የሚል ምሥራች እየጠበቁ ሳለ ነበር በመላው ዓለም የመገናኛ ብዙኃን ይህ አስደንጋጭ ዜና ተሰማው። ከላምፔዱዛ የባሕር ዳርቻ አንድ ኪሎ ሜትር ርቀት […]

አሜሪካዊው የምክር ቤት አባል ሽጉጥ ተደግኖባቸው መኪናቸው ተዘረፈ

ከ 5 ሰአት በፊት የአሜሪካ የምክር ቤት አባል ሄንሪ ኩሌር ሽጉጥ ተደግኖባቸው መኪናቸው እንደተዘረፈ የአገር ውስጥ ሚዲያዎች ዘግበዋል። የምክር ቤቱ አባል መኪናቸው የተሰረቀው ሰኞ ማምሻውን መስከረም 21/2016 ዓ.ም በዋሸንግተን መሆኑ ተነግሯል። የቴክሳስ ግዛት የዴሞክራት ፓርቲ ተወካዪ ከአሜሪካ የካፒቶል ህንጻ በ1.6 ኪሎሜትር ርቀት ላይ መኪናቸውን አቁመው የነበረ ሲሆን ሦስት የታጠቁ ግለሰቦችም ሽጉጥ ደግነው መኪናቸውን እንደወሰዱ ተነግሯል። […]

ያለፈቃዳችን የእርግዝና መከላከያ እንድንጠቀም ተደርገናል ያሉ የግሪንላንድ ሴቶች ካሳ ጠየቁ

ከ 9 ሰአት በፊት በግሪንላንድ እንደ አውሮፓውያኑ በ1960ዎቹ የእርግዝና መከላከያ ያለፈቃዳችን እንድንጠቀም ተደርገናል ያሉ 67 ሴቶች የዴንማርክ መንግሥት ካሳ እንዲከፍላቸው ጠየቁ። በግሪንላንድ ነባር ሕዝቦች መካከል ያለውን የውልደት ምጣኔ ለመገደብ በታቀደው መርሃ ግብር በአስራዎቹ የዕድሜ ክልል የሚገኙ ታዳጊዎችን ጨምሮ ቢያንስ 4 ሺህ 500 ሴቶች የእርግዝና መከላከያ እንዲጠቀሙ ተደርገዋል። ይህንንም ተከትሎም ሴቶቹ ያቀረቡትን ጥያቄ የሚመረምር ኮሚሽን የተቋቋመ […]