ኢዜማ የፓርቲው ሊቀመንበር ዶ/ር ጫኔ ከበደ መታሰርን እንደሚደግፍ መግለጫ አወጣ

October 2, 2023 – Konjit Sitotaw  ኢዜማ የፓርቲው ሊቀመንበር ዶ/ር ጫኔ ከበደ መታሰርን እንደሚደግፍ መግለጫ አወጣ። ካሁን ቀደም ግለሰቡ ሲያዙ ስብሰባ ላይ የሰጡትን አስተያየት ተከትሎ ብርሃኑ ነጋ እንዲያዘ ለአብይ አገዛዝ ባስተላለፈው መልዕክት መሰረት እንደሆነ ከውስጥ ምንጮች የተገኘ መረጃ አመልክቷል። ጫኔ ከበደን ጽንፈኛ አማራ ነው ብሎ ያሳፈነው ብርሀኑ ነጋ ነው! ተብሎ መፃፉ ይታወሳል። በተባለው መሰረት ይህንን የሚያጠናክርና የሚያረጋገጥ […]

ኢትዮጵያዊቷ ትዕግሥት አሰፋ የሰበረችው የማራቶን ክብረ ወሰን ለምን መነጋገሪያ ሆነ?

1 ጥቅምት 2023 ከአራት ዓመታት በፊት በገጠማት ጉዳት ምክንያት በሐኪሞች ሩጫ እንድታቆም የተመከረችው ትዕግሥት፣ ባለፈው ሳምንት መስከረም 13/2016 ዓ.ም. ጀርመን ላይ ከባዱን የማራቶን ውድድር ክብረ ወሰን በሰፊ የሰዓት ልዩነት በማሻሻል ዓለምን አስደንቃለች። ይህንን የሴቶች ማራቶን ክብረ ወሰንን በሁለት ደቂቃ ከ11 ሰከንዶች ለማሻሻል ዓመታትን እና ከፍተኛ ልፋትን እንደሚጠይቅ በስፖርት ተንታኞች እየተነገረ ነው። ትዕግሥት ግን በርሊን ላይ […]

እስራኤል ውስጥ በኤርትራውያን መካከል በተፈጠረ አምባጓሮ አንድ ሰው ሲገደል በርካቶች ቆሰሉ

ከ 54 ደቂቃዎች በፊት እስራኤል ውስጥ በኤርትራ መንግሥት ደጋፊዎች እና በተቃዋሚዎች መካከል በተፈጠረ አምባጓሮ አንድ ሰው በስለት ሲገደል በርካቶች ቆሰሉ። ቅዳሜ መስከረም 19/2016 ዓ.ም. በኔታንያ በተለ ስፍራ በተፈጠረው ሁከት አንድ ኤርትራዊ በስለት ተወግቶ መገደሉን የአገሪቱ የመገናኛ ብዙኃን ፖሊስን ዋቢ አድርገው ዘግበዋል። የተገደለው ኤርትራዊ የአገሩን መንግሥት የሚቃወም በመሆኑ በአገዛዙ ደጋፊዎች በስለት ሳይወጋ እንዳልቀረ ፖሊስ መጠርጠሩን ታይምስ […]

ለ1977ቱ የኢትዮጵያ ረሃብ እርዳታ ማሰባሰቢያ የነበረው ሙዚቃ ወደ መድረክ ሊመጣ ነው

ከ 4 ሰአት በፊት በኢትዮጵያ ለተከሰተው የ1977ቱ አስከፊ ረሃብ እርዳታ እንዲውል በገንዘብ ማሰባሰቢያነት ከ38 ዓመታት በፊት የተዘጋጀው የሙዚቃ ዝግጅት ዳግም ወደ መድረክ ሊመጣ ነው። ‘ላይቭ ኤይድ’ የሚል ስያሜ የተሰጠው እና በርካታ ሙዚቀኞችን ያሰባሰበው የሙዚቃ ዝግጅት በዝነኛነቱ አሁንም ዓለማችን ከምታወሳቸው አንዱ ነው። በቀጥታ የተላለፈው የሙዚቃ ዝግጅትም ተዘጋጅቶ በመድረክ ሙዚቃነት በሚቀጥለው ዓመት በለንደን ይቀርባል። የመጀመሪያው የሙዚቃ ዝግጅት […]

በሜክሲኮ የቤተ ክርስቲያን ጣራ ተደርምሶ 7 ሰዎች ሲሞቱ 20 ሰዎች መውጫ ማጣታቸው ተነገረ

ከ 3 ሰአት በፊት በሜክሲኮ የአንድ ቤተ ክርስቲያን ጣር መደርመሱን ተከትሎ ሰባት ሰዎች መሞታቸውን እና 20 ሰዎች ደግሞ መውጫ ማጣታቸው ተዘግቧል። በሜክሲኮ ሲውሳድ ማደሬ ከተማ የሚገኘው የሳንታ ክሩዝ ቤተ ክርስቲያን ጣሪያ መውደቁን ተከትሎ 49 ሰዎች በደረሰባቸው ጉዳት ሆስፒታል መወሰዳቸውንም የሀገሪቱ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል። ቤተ ክርስቲያኑ የሚገኝበት የባህር ዳርቻ ግዛት የሆነው ታሙሊፓስ ፖሊስ አደጋው በደረሰበት ወቀት […]

በናይጄሪያ ሰራተኞች አድማ ለማድረግ እየተዘጋጁ ባሉበት ወቅት የደመወዝ ጭማሪ ተደረገ

ከ 4 ሰአት በፊት በናይጄሪያ ሰራተኞች የስራ ማቆም አድማ ለማድረግ ባቀዱበት ሰዓት የሀገሪቱ ፕሬዝዳንት ቦላ ቲኑቡ በዝቅተኛ የደመወዝ ወለል ላይ ለ6 ወራት የሚቆይ ጭማሪ እንዲደረግ አዘዋል። የሰራተኞች ማህበር ፕሬዝዳንቱ ስልጣን ከያዙበት ሰኔ ወር ጀምሮ እያሻቀበ ያለውን የኑሮ ውድነት ለመቋቋም ወርሃዊ ደመወዝ ወደ 255 ዶላር እንዲያድግ ሲጠይቁ ቆይተዋል። ፕሬዝዳንቱ ያደረጉት ጭማሪ ዝቅተኛ የደመወዝ ወለል ላይ ብቻ […]

ድርድርና ሽግግር ከፋሺስታዊው አገዛዝ ስንብት በኋላ (ከይኄይስ እውነቱ)

22/09/2023 ድርድርና ሽግግር ከፋሺስታዊው አገዛዝ ስንብት በኋላ  (አቋምን የበለጠ ለማጽናት) ከይኄይስ እውነቱ የዐምሐራ ሕዝብ ጀግናም ዐዋቂም ሞልቶታል፡፡ ጨዋነት፣ ሰብአዊነት፣ ሕግና ሥርዓትን መጠንቀቅ ተፈጥሮአዊ ገንዘቦቹ ናቸው፡፡ እነዚህ የእምነት የባህል መሠረት ያላቸው ጠባያት በሩቁ ትውልድ ብቻ የሚነገሩ የታሪኩ ክፍሎች ሳይሆኑ በትውፊት ሲተላለፉ ቆይተው የአሁኑም ትውልድ በዐይኑ አይቶ በዦሮው አድምጦ የመሰከረላቸው እውነታዎች ናቸው፡፡ መገለጫው ባይሆኑም እንደማንኛውም ማኅበረሰብ ደግሞ […]

የአቢይና ጓደኞቹ በሽታ ከሌሎች ይለያል! (ይነጋል በላቸው)

24/09/2023  አቢይ አህመድ በድርጊቱ የሚገለጹ በርካታ በሽታዎች ጎተራ ነው፡፡ አምባገነንነት አንዱ ነው፡፡ ይህ ግን የብዙ ደጋግ ሰዎችም ህመም ነው፡፡ አምባገነንነት በራሱ ብዙም መጥፎ አይደለም፡፡ ለአብነት ሣዳምም ጋዳፊም የኛዎቹ አፄዎችም አምባገነኖች ነበሩ፡፡ ግን አንዱን ብሔር በሌላው ላይ በማነሣሣት እንደጎርፍ በሚፈስ የሕዝባቸው ደም መታጠብን፣ በሕዝባቸው ሥጋ ሆዳቸውን መቆዘርን እንደኃጢአት እንጂ እንደጽድቅ አይቆጥሩም ነበር፡፡ አቢይ ግን በተለይ በአማራ ደም ካልዋኘ ለአፍታም በሕይወት የሚቆይ አይመስለውም፡፡ ለአቢይ ሰላምና ፍቅር ዋና ጠላቶቹ ናቸው፡፡ እዚህ ላይ መነሳት ያለበት ለብዙዎች ዕንቆቅልሽ የሆነ አንድ መሠረታዊ ነጥብ አለ፡፡ ብዙ ኦሮሞ ስለተታለለበት የአቢ የትውልድ ሐረግ ነው የማነሣው፡፡ ብዙ ጊዜ ቢነገርም ሰዎች ይህን እውነት ሊያምኑ አይአችሉም ወይም አይፈልጉም፡፡ አቢይ ኦሮሞ መስሏቸው በሱ አማራጠል ቅስቀሣ በመወናበድ አሁን በዚች ቅጽበት ጭምር አማራ ሕጻናትን እያረዱ የሚገኙ ኦሮሞዎች አሉ፡፡ እውነቱን ቢረዱ ግን አቢይን ነበር የሚያርዱት፡፡ አቢይ እኮ ሥልጣን በያዘ ሰሞን መቀሌ ላይ ለ13 ደቂቃዎች በተወላገደ ትግርኛ ባደረገው ንግግር ትግሬ መሆኑን ሣያፍር ለማሣየት ጥሯል፡፡ ኦሮሞ ነኝ እያለም ሚሊዮኖችን አነሁልሏል፡፡ ይቺን የ13 ቁጥር እና የአለቃው መለያ 666 ፍቅሩን ግን ያዙልኝ፤ በቅርቡ እንኳን 13 ሚ. የኢትዮጵያ ሕዝብ እንጨርሣለን ብሏል አሉ፡፡ ለማንቻውም ሁሉም ማወቅ ያለበት አቢይ አማራ እንጂ ኦሮሞም ትግሬም አለመሆኑን ነው፡፡ ጃዋር መሀመድም በጉዲፈቻ ያደገ የውርርስ ኦሮሞነት እንጂ ከዐረብና ከአማራ የዘለለ የዘር ሐረግ የለውም፡፡ በጥባጮች የአጋንንት እንጂ ከዚህ ወይ ከዚያ የሚባል የሰው ዘር ሐረግ ሲመዘዝባቸው አይስተዋልም፡፡ ብዙዎቹ አምባገነኖች ከየት እንደሚፈልቁ ብዙም አይታወቅም፤ እነሱም ለዚህ ግዴላቸውም፡፡ ለማስረጃነት ያህል ሂትለርን ፈትሹ፡፡ ጆሴፍ እስታሊንንም ፈትሹ ከፈለጋችሁ፡፡ አምባገነኖች የዘር ሐረጋቸው ነገር ጉዳያቸው አይደለም፤ እንደሥልት እንጅ እንደግብ አይቆጥሩትምና፡፡ እናም እያፋጀን ያለው የኦሮሞ ጠ/ሚንስትር ሣይሆን የሰንበት ጽንስ የሆነው የሣጥናኤል በኩር ልጅ ነው – ትምህርት ዕርሙ አቶ አቢይ አህመድ፡፡ ብዙ ይጠቅሙናል ያልናቸውን ዕንቁላሎች ግን በእጁና በጉንጮቹ አንዳንዴም በከንፈሮቹ እየነካካና እየሳሳመ አገማብን፡፡ ከትልልቅዬ ጉዳቶቹ አንዱ ይሄ ነው፡፡ እሱ ጨብጦትና በምኑም ይሁን በምኑ ስሞት በምር ወይም በቁም ያልሞተ ካለ ንገሩኝ፤ ወንድሜ ዳንኤል ብርሃኑ ይሙት!  – እውነቴን እኮ ነው፤ ለክፉ ቀን ይሆኑናል ያልናቸውን ስንቶችን አሳጣን፡፡ ለመሆኑ አልማርያም ለጤንነቱ ደህና ነው? ጠፋብኝ፡፡  ከወደጎንደር የምንሰማው መልካም ዜና የጎንደርን የቅርብ ጊዜ ታሪክ […]

በቃኝ አለ!

 27/09/2023 (ለህልውና ትግል ለሚፋለመው ለመላው የአማራ ሕዝብ) ጊዜው በሂደት ሲደርስ፣ ጽዋው ሞልቶ ሲፈስ፣ እምቢኝ አለ… የመከራን ስቃይ ቀንበር-ላንዲት ዕለት ላይሸከም፣ የሰቆቃን ብርቱ ሕመም- ለዘወትር ላይታመም፣ የትርክቱን ቅጥፈት ስንክሳር – ላንዲት ቅፅበት ችሎ ላይኖር፣ በሆድ-አምላክ፣ በምስለኔ – በቅጥረኞች ላይጠፈር…፣ በቃኝ አለ አመረረ! – ነጻነቱን አበሰረ! ለዘመናት ችሎ…ችሎ..፣ – “ለምጣዱ ሲባል..” ብሎ፣ “ያይጥ መንጎች” መጨፈሪያ፣ – አሰስ-ገሰስ […]

የፋኖን ባህሪ፣ ሂደትና እድገት አስመልክቶ (አንዱ ዓለም ተፈራ)

26/09/2023  የፋኖን አፈጣጠርና ምንነት ብዙዎች ስለዘረዘሩት እዚህ መደረት አልፈልግም። እኔ ማቅረብ የፈለግሁት፤ እኛ በውጪ አገራት የምንገኝ ኢትዮጵያዊያን፤ አሁን በተጨባጭ ያለውን የፋኖ ባህሪ፣ ሂደትና ዕድገት አስመልክቶ ስለአለን ግንዛቤ ነው። ፋኖ፤ አገር ወዳዱና ወገን አፍቃሪው ሁሉ፤ በያለበት አካባቢም ሆነ ባገር አቀፍ ደረጃ፤ መንደሩን ሆነ አገሩን የሚያሰጋ ሁኔታ ሲፈጠር፤ ይሄን ለመቋቋም በአንድነት ነፍጥ አንግቶ የሚነሳበት ክስተት ነው። በአብዛኛው […]