ከውጭ የልማት አጋሮች ዘንድሮ ለማግኘት ታቅዶ የነበረው 7.7 ቢሊዮን ብር፤ እስካሁን “ፈሰስ አለመደረጉን” የገንዘብ ሚኒስቴር አስታወቀ – ኢትዮጵያ ኢንሳይደር 

May 17, 2023 በአማኑኤል ይልቃል የፌደራል መንግስት በተያዘው በጀት ዓመት ከውጭ ቀጥታ የበጀት ድጋፍ 7.7 ቢሊዮን ብር ለማግኘት ቢያቅድም፤ እስካሁን “ፈሰስ አለመደረጉን”  የገንዘብ ሚኒስቴር አስታወቀ። ሶስት ሚሊዮን ዜጎች በጦርነት እና ግጭት ሳቢያ “ወደ ከፋ ድህነት” መግባታቸውን በጥናት ማረጋገጡንም ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ገልጿል።  የገንዘብ ሚኒስቴር ይህን ያስታወቀው የዘጠኝ ወራት የስራ አፈጻጸም ሪፖርቱን፤ ለተወካዮች ምክር ቤት የፕላን፣ […]

የቻትጂፒቲ መሥራች የአሜሪካ ሕግ አውጪዎች ሰው ሰራሽ አስተውሎት (ኤአይ) ላይ ቁጥጥር እንዲያደርጉ ጠየቀ

ከ 5 ሰአት በፊት ቻትጂፒቲን የፈጠረው ሳም አልትማን የአሜሪካ ሕግ አውጪዎች ሰው ሠራሽ አስተውሎት (ኤአይ) ላይ ቁጥጥር እንዲያደርጉ ጠየቀ። ቻትጂፒቲን የፈጠረው የኦፕንኤአይ ተቋም ዋና ኃላፊ ሳም በአሜሪካ ምክር ቤት ቃሉን በሰጠበት ወቅት ስለአዲሱ ቴክኖሎጂ ተስፋና ስጋት ገልጿል። በወራት ውስጥ ብዙ የኤአይ ሞዴሎች ገበያውን ተቀላቅለዋል። ሳም እንዳለው ለኤአይ ተቋማት ፈቃድ የሚሰጥ አዲስ የመንግሥት ድርጅት ሊቋቋም ይገባል። […]

ከ10 ደቡብ አፍሪካዊያን ሕፃናት ስምንቱ ማንበብ እንደሚከብዳቸው ጥናት ገለጠ

ከ 5 ሰአት በፊት ከ10 ደቡብ አፍሪካዊያን ሕፃናት ስምንቱ ዕድሜያቸው 10 እስኪሞላው ድረስ ማንበብ እንደሚከብዳቸው አንድ ጥናት ገልጧል። ፕሮግረስ ኢንተርናሽናል ሪዲንግ ሊትራሲ የተሰኘው ጥናት ደቡብ አፍሪካን ከ57 አገራት የመጨረሻዋ አድርጓታል። ተቋሙ በዓለም አቀፍ ደረጃ በሠራው ጥናት የ400 ሺህ ሕፃናትን የማንበብ አቅም ፈትኗል። በፈረንጆቹ 2016 ማንበብ የማይችሉ ደቡብ አፍሪካዊያን ሕፃናት 78 በመቶ ነበሩ። አሁን ይህ ቁጥር […]

በአፍሪካ ቀንድ የጦር ሠፈራቸውን የመሠረቱ ኃያላን አገራት

ከ 6 ሰአት በፊት ኢትዮጵያ፣ ኤርትራ፣ ጂቡቲ፣ ሱዳን፣ ደቡብ ሱዳን እና ሶማሊያን አንዳንድ ጊዜም ኬንያን የሚያካትተው የአፍሪካ ቀንድ የዓለማችችንን ትልቁን የባሕር ላይ የንግድ መስመርን ይዟል። የአፍሪካ ቀንድን ወሳኝ ስፍራ እንዲሆን ያስቻለው የቀይ ባሕር፣ ከመካከለኛው ምሥራቅ እና ከባሕረ ሰላጤው አገራት ነዳጅ፤ ከእስያ ደግሞ የኢንዱስትሪ ምርቶች ወደ አውሮፓ እና አሜሪካ የሚተላለፉበት በመሆኑ ነው። ይህ ምክንያት ሆኗቸው ከዓመታት […]

በኢትዮጵያ የሕዝብ እና ቤት ቆጠራ በቀጣይ ሦስት ዓመታት ውስጥ እንደሚካሄድ ተገለጸ

ከ 2 ሰአት በፊት አራተኛው የሕዝብ እና ቤት ቆጠራ በቀጣይ ሦስት ዓመታት ውስጥ እንደሚካሄድ የፕላን እና ልማት ሚኒስትሯ ፍጹም አሰፋ (ዶ/ር) ለቢቢሲ ገለጹ። ቆጠራው ባለፉት ዓመታት ለተደጋጋሚ ጊዜ ሲራዘም የቆየ ሲሆን፣ በዚህም ሳቢያ የአገሪቱ አጠቃላይ ሕዝብ ብዛትን የሚመለከት አስተማማኝ መረጃ የለም። የሕዝብ እና ቤት ቆጠራ ባለፉት ዓመታት በዋነኛነት በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ እንዲሁም በጦርነት ሳቢያ ሳይካሄድ መቅረቱን […]

ህወሓት የምርጫ ቦርድ ውሳኔ ‘ከፕሪቶሪያው ስምምነት ውጪ ነው’ በማለት ተቃወመ

ከ 5 ሰአት በፊት ህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) ሕጋዊነቱ እና ንብረቶቹ ከጦርነቱ በፊት ወደ ነበረበት እንዲመለስ ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ያቀረበው ጥያቄ ውድቅ መደረጉ ከፕሪቶሪያው ስምምነት ውጪ ነው በማለት ተቃወመው። በትግራይ የተካሄደው ጦርነት መቀስቀሱን ተከትሎ ህወሓት በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሽብርተኛ ቡድን ተብሎ መሰየሙ እና በምርጫ ቦርድም የነበረው እውቅና ተሰርዞ ሕገ ወጥ ተደርጎ ቆይቶ […]

ሊቃጠል ወራት የቀሩት ከ2000 በላይ የዲቪ ሎተሪ ባለዕድል ኢትዮጵያውያን ጉዳይ

ከ 6 ሰአት በፊት የአውሮፓውያኑ 2023 የዲቪ ሎተሪ ደርሷቸው ወደ አሜሪካ የሚያደርጉት የጉዞ ሂደት የዘገየባቸው ኢትዮጵያውያን ዕድለኞች ስጋት ላይ መሆናቸውን ለቢቢሲ ገለፁ። ባለፈው ዓመት ግንቦት ወር 2700 ኢትዮጵያውያን የ2023 የዲቪ ሎተሪ ዕድለኞች ሆነው መመረጣቸው ተነግሯቸው ነበር። የዚሁ የዲቪ ሎተሪ ዕድለኞች የሆኑ ሰዎችም በአዲስ አበባ በሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ በኩል የተለያዩ መስፈርቶችን ካሟሉ በኋላ ቪዛ በማግኘት ወደ […]

ሕወሓትን ጨምሮ የትግራይ የፖለቲካ ፓርቲዎች የብርቱካን ሚደቅሳ ምርጫ ቦርድ እያሰቃየን ነው ሲሉ አማረሩ

May 17, 2023 – Konjit Sitotaw  ህወሓት የምርጫ ቦርድን ውሳኔ እንደማይቀበል አስታወቀ ውሳኔው በፕሪቶርያ የተደረሰው ስምምነትና ህግን መሰረት ያላደረገ ነው ብሏል የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህ.ወ.ሓ.ት) ህጋዊ ሰውነት የመመለስን ጥያቄ ውድቅ ማድረጉን ተከትሎ ህወሓት የቦርዱን ውሳኔ እንደማይቀበል አስታወቀ። ድርጅቱ ምርጫ ቦርድ ጥር 10/2013 ያስተላለፈውን ውሳኔ ዳግም በማጤን የህወሓት ህጋዊ ሰውነት ከጦርነቱ በፊት ወደ ነበረበት […]

በኢመደበኛ የሕገ መንግስት ማሻሻያ ሽፋን አዘናግቶ ብልጽግና የፈለገውን ሕግ አምጥቶ እንዲጭንብን ልንፈቅድለት አይገባም።

May 17, 2023 – ምንሊክ ሳልሳዊ  ምንሊክ ሳልሳዊ ፡ ሕግ አውጪውም፣ ሕግ አስፈጻሚውም፣ ሕግ ተርጓሚውም ያላከበረው ፣ ለሕዝብ ያልበጀው፣ በኢሕአዴግ የፖለቲካ ፕሮግራም የተቀረጸው (ሕገ አራዊት) ሕገመንግስትን ከማሻሻል በፊት ሕግና ስርዐት ያለው መንግስት ይኑር ። ሕገመንግስት ማሻሻል የሁላችንም የአስርት አመታት ጥያቄ ቢሆንም የሃገርን ሰላምና የዜጎችን ደሕንነት መጠበቅ ያልቻለ መንግስት ባሌለበት እንዴት ሕገ መንግስት ይሻሻል ይባላል ? ቅድሚያ መንግስት ይኑር […]

የኢሳያስ አፈወርቂ የቻይና ጉብኝት አለምን እያነጋገረ ነው ።

May 17, 2023 – DW Amharic የኤርትራው ፕሬዝዳንት ኢሳይያስ አፈወርቂ፤ ከቻይናው መሪ ፕረዚደንት ጅፒንግ በቀረበላቸው ግብዣ፤ ካለፈው ዕሁድ ጀምሮ ላራት ቀናት በቻይና  ይፋዊ ጉብኝት  በማደረግ ላይ ናቸው። ፕሬዝደትን ጂፒንግ በትናንትናው ዕለት ለፕሬዝደንት ኢሳይያስና ለኡካቸው በቲያናንማን አደባባይ  ደማቅ ፕሬዝዳንታዊ አቀባበል አድርገውላቸዋል።Audio Player ከአደባባይ የአቀባበል ስነስርቱ በኋላ በቤተመንግስት በነበረው የጋራ ስብሰባም ፕሬዝዳንት ጂፒንግ፤  የቻይናና ኤርትራ መልካም ግንኙነት ለአፍርካ ቀንድ […]