የአዲስ አበባ ፈጣን የትራንዚት አውቶቡስ አገልግሎት ከሦስት ዓመት በኋላ ይጀመራል ተባለ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትራንስፖርት ፕሮግራም ማኔጅመንት ጽሕፈት ቤት የቢአርቲ ፕሮጀክት ኃላፊ አቶ ቴዎድሮስ ፀጋዬ ብርሃኑ ፈቃደ 157 አውቶቡሶች ለሚሠማሩበት የመጀመርያው ምዕራፍ 130 ሚሊዮን ዩሮ ተመድቧል የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የከተማዋን የብዙኃን ትራንስፖርት አቅርቦት እጥረት ለመቅረፍ ያስቻላል ያለውን የፈጣን ትራንዚት አውቶቡስ (ቢአርቲ-ቢ2 ኮሪደር) አገልግሎት፣ በሦስት ዓመታት ውስጥ ሥራ ለማስጀመር እየሠራ እንደሚገኝ አስታወቀ፡፡ ከፈረንሣይ የልማት ትብብር […]
በሸካ ዞን ተቃውሞው ቀጥሏል

August 12, 2018 በሸካ ዞን ተቃውሞው ቀጥሏል (በውብሸት ታዬ) -ሆቴሎችና ባንኮች ተዘግተዋል -የትራንስፖርት አገልግሎት ተስተጓጉሏል -ተቃውሞው አራተኛ ቀኑን ይዟል ከሁለት ሳምንት በፊት አንድ የ’መንጃ’ ብሔረሰብ አባል በአንድ ከፊቾ(የከፋ ብሔረሰብ አባል) ላይ ግድያ ፈጽሟል በሚል መነሻ በተቀሰቀሰ ግጭትና የበቀል እንቅስቃሴ በርካታ ቤቶች የተቃጠሉ ሲሆን በሰው አካል ላይም ጉዳት መድረሱን በቦታው የተገኘው ባልደረባችን ዘግቧል። የተከሰተውን ግጭት ተከትሎ […]
“ጄል” ኦጋዴን እና የጅግጅጋ ፖለቲካ (መስከረም አበራ)

12/08/2018 መስከረም አበራ የሃገራችን ፖለቲካዊ ከባቢ በተበድዬ ተረክ “የበለፀገ” የጎሳ ፍትጊያ የተንሰራፋበት ነው፡፡ የጎሳ ፖለቲካችን ንረት ፖለቲካ ማለት ጎሳ ማለት ብቻ እንደሆነ እርግጠኛ ሊሆን ይሞክረዋል፡፡ ይሄው አደገኛ አዝማሚያ የሚዘወረው ደግሞ የግል ደም-ፍላታቸውን በካሜራ ፊት ሲሆኑ እንኳን መቆጣጠር በማይችሉ፤ ደርሶ ቱግ ባይ የፖለቲካ ሊቅ ነን ባዮች ነው፡፡ ይህ ህወሓት ይዘውረው በነበረው መንግሥታዊ መሰላልም፣ ተቃዋሚ ነን በሚሉ […]
በሻሸመኔ ጀዋር መሐመድን ለመቀበል የወጡት ወጣቶች ስለሰቀሉት ወጣትና ስለሞቱ ሰዎች የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽነር የሰጡት መግለጫ

12/08/2018 https://www.youtube.com/watch?time_continue=11&v=BjOhtLrCkmg
”ወጣቱን የአገሪቱም ሆነ የተጀመረው ለውጥ አድራጊ ፈጣሪ አለመሆኑን ማስረዳት/ማሳየት ያስፈልጋል።” (መስፍን ነጋሽ)

12/08/2018 የማናውቀው፣ ያልጠበቅነው፣ ያልፈራነው አልሆነም። በሻሸመኔም ሆነ በሌሎች ቦታዎች የሚሆነውን አውሬያዊ የሰው ድርጊት ስንመለከት ማዘን እንጂ ደርሶ እንግዳ መሆን የለብንም። የሻሽመኔው ድርጊት እስካሁን ከታዩት ሁሉ የመንጋውን አደገኛ አውሬነት የሚያሳይ ነው። ሁለት መሠረታዊ ገፊ ምክንያቶች አሉ። የዘውግ ፖለቲካ እና ከአቅሙ በላይ እየተወጠረ፣ መረን እየወጣ ያለ ወጣት ኀይል። የዘውግ/ብሔር ፖለቲካ በእያንዳንዱ ተፈጥሯዊና የማይቀርበት ፌርማታው ሲደርስ እንዲህ እርቃኑን […]
አመፃ ይቁም! የአመፃ ፍትሕ የለም! (በፈቃዱ ዘ ሃይሉ)

12/08/2018 አመፃ ይቁም! የአመፃ ፍትሕ የለም! በፈቃዱ ዘ ሃይሉ (< የሚታየው ምስል ዘግናኝ በመሆኑ አደብዝዤዋለሁ ) ሐዲስ ዓለማየሁን የሚያክል የሚያስደምመኝ የተዋጣላቸው ኢትዮጵያዊ አክቲቪስት እና ደራሲ አላውቅም። ድርሰቶቻቸው የአክቲቪዝም ዓላማ ነበራቸው። ‘የሠላማዊነት’ አቀንቃኝ ነበሩ። “የልምዣት” በተሰኘው የረዥም ልቦለድ ሥራቸው ላይ ባሻህ ዘለሌ የሚባል ሰው የሚመራ አንድ ኅቡዕ ድርጅት ነበር። የድርጅቱ ዓላማ የባለጉ ባለሥልጣናትን መቅጣት ነበር። የድርጅቱ […]
የሻሼመኔው ድርጊት በኢትዮጵያ ውስጥ የመጨረሻው ስህተት መሆን አለበት (ታማኝ በየነ)

12/08/2018 የሻሼመኔው ድርጊት በኢትዮጵያ ውስጥ የመጨረሻው ስህተት መሆን አለበት ታማኝ በየነ በ 1953 ዓ/ዓም ጄኔራል መንግስቱና ወንድማቸው ገርማሜ ነዋይ ከሌሎች ጋር በመሆን የቀዳማዊ ህይለስላሴን መንግስት በሃይል ለመገልበጥ የክብር ዘበኛን ጦር ይዘው ተንቀሳቀሱ ፡፡ እቴጌ ታመዋልና ወደ ቤተመንግስት ኑ በማለት ብዙዎቹን ባለሰልጣናት ከጠሩ በኋላ በግፍ ረሸኗቸው ፡፡ በሌላ በኩል ሌሎች የንጉሱ ታማኞች ደግሞ የምድር ጦርን ይዘው […]
ለቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር ለአቶ ታምራት ላይኔ ጥያቄ አልኝ? እውነተኛው ታምራት ማን ናቸው? (ከደመቀ እውነቱ)

August 11,2018 ስሞችዎ ብዙ መሆናቸውን በአንደበትዎ ስለመስከሩ በእውነተኛው ስምዎ ሳይሆን በfake “ታምራት “ይህችን ጥያቄ ላቀርብልዎ ፈለግሁ:: አርስዎ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው የአማራ ዘመዶቼ በግፍ ከገደል ተወርውረዋል:: ለዚህም አርስዎ እኔ እንዲወረወሩ አላዘዝኩም :አላስጨፈጨፍኩም ብለዋል:: እኔ ግን እርስዎ አስወርውረዋል እላለሁ:: አዲስ አበባም በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ላይ ቦንብ የወረወሩትን ሳይሆን የህዝቡ ጥያቄ ያስወረወሩት ላይ ነው:: ለመወርወር ብር ካለ ችግር […]
ወገን ሆይ ንቃ! መደመር የያዘው ያልታየው አደጋ ሊያስበላን ነው !!! – ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው

አሁን ማምሻውን በኢቴቪ ዜና ላይ ዐቢይና ደብረጽዮን ቅዱስ ፓትርያርኩን ለመጠየቅ ፋታ ከማይሰጥና አጣዳፊ ወቅታዊ ሥራ ላይ ተነሥተው እንደመጡ በመግለጽ የሶማሌ ክልል በሚሉት የሀገራችን ክፍል የተፈጠረውን ቀውስ ለማረጋጋት እጅግ አድካሚ በሆነ ሥራ ተጠምደው እንደሰነበቱ ዐቢይ ትንሽም ሳያፍር ሊነግረን ሞክሯል፡፡ ጉድ እኮነው እናንተየ! ወይ ዐቢይ!!! የተከበሩ ጠ/ሚ ሆይ! ይሄ ግን ሕዝብ በደረሰበት ሰቆቃ፣ አረመኔያዊ ግፍ፣ አሳር፣ ስቃይ […]
ህዝቤ ሆይ አትወናበድ! (ታዬ ደንደአ)

11/08/2018 ህዝቤ ሆይ አትወናበድ! ታዬ ደንደአ ከትላንት ወድያ የኢትዮጵያ ህዝብ ተባብሮ በከፈለዉ ዋጋ አስደማሚ አብዮት ማካሄዱን እና የፀረ-ለዉጥ ቡድኑ ለዉጡን ለመቀልበስ በተለያዬ ዘዴ የህዝቡን አንድነት ለማላላት እየሰራ መሆኑን ገልጬ ነበር። ዛሬ ደግሞ የሚከተሉትን ነጥቦች ላክል። እዉነት ለመናገር አሁን ላይ የተደራጁ ሌቦች ተገርስሷል። ፈፅሞ የኢትዮጵያን የዴሞክረሲ ህደት የሚያሰናክሉበት አቅም የለቸዉም። ልፋታቸዉ ከንቱ ነዉ። በእርግጥ ትላንትም አቅም […]