የኦዴግ ወንዝ ወደ ኢሕአዴግ ባሕር ትፈሳለች (መስፍን ነጋሽ)

23/05/2018 ለዋዜማ ራዲዮ የእነ ሌንጮ ለታ ቡድን ወደ አገር ቤት መመለሱ መልካም ዜና ነው። ሆኖም የግለሰቦቹ መመለስም ሆነ የድርጅታቸው የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ኦዴግ) አገር ቤት መግባት ያለው ፖለቲካዊ ፋይዳ መጋነን የለበትም። በመሠረቱ አሁን ባለው የፖለቲካ አሰላለፍ ግለሰቦቹም ሆኑ ድርጅታቸው ይህ ነው የሚባል ተጨባጭ ተጽእኖ የላቸውም። በድርጅታዊ አቅምም ይሁን በርእዮተ ዓለማዊ ተዋስኦ ለአገር ቤቱ ፖለቲካ የሚጨምሩለት […]
“ ህገ መንግስቱን ተቀበል” የሚል ቅድመ ሁኔታ አስቀምጦ ወደ ድርድር አይገባም! (ፋሲል የኔዓለም)

23/05/2018 አህመድ ሽዴ የተባለው የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ የእነ ኦቦ ሌንጮችን ጉዞ በተመለከተ የሰጠውን መግለጫ ሰማሁት። “ህገመንግስታዊ ስርዓቱን” የተቀበሉ ሃይሎች መግባት አለባቸው ይላል። ያው እነ መለስ ዜናዊ ሲሉት ከነበረው የተለዬ ነገር የለውም። ህገመንግስታዊ ስርዓቱ ሁሉንም በሚያሳትፍ መልኩ እንዲከለስ የሚቀርበው ጥያቄ ተቀባይነት እንደሌለው ከአህመድ ንግግር ለመረዳት ችያለሁ። በአጭሩ ወያኔ ለድርድር ያስቀመጠውን “ቅድመ ሁኔታ” አልለወጠም ማለት ነው። […]
የኦ.ዴ.ግ ተደራዳሪ ቡድን አዲስ አበባ ገባ!? (መለሰ በቃሉ)

23/05/2018 የድርጅቱ ሊቀመንበር አቶ ሌንጮ ለታን ጨምሮ ሌሎች አመራሮች ዛሬ አዲስ አበባ ሲገቡ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የደህንነት ጉዳዮች አማካሪ አቶ አባ ዱላ ገመዳ የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ፅህፈት ቤት ሃላፊ ሚኒስትር አቶ አህመድ ሺዴን ጨምሮ የተለያዩ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች አቀባበል አድርገውላቸዋል። አምስት የተደራዳሪ ቡድኑን ልዑክ እየመሩ የመጡት የግንባሩ ሊቀ መንበር አቶ ሌንጮ ለታ በቦሌ አለም አቀፍ አውሮፕላን […]
ሁለት ሄክታር (ቃዳ) መሬት ለአንድ የአማራ ገበሬ አዲሱ የወያኔ አማራን የማፈናቀያ ስልት!-ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው

የእነ ለማ መገርሳ አሥተዳደር “ሁለት ሄክታር (ቃዳ) መሬት ለአንድ የአማራ ገበሬ!” የሚል ድንጋጌ ይዞ የአማራ ገበሬዎች ግብር እየከፈሉበት ለዐሥርት ዓመታት እያረሱት የኖሩትን መሬት እየነጠቀ ለኦሮሞ ወጣቶች እየከፋፈለ በመስጠት ሒደት ላይ ይገኛል፡፡ አቶ ሽፈራው ሽጉጤም ተመሳሳይ እርምጃ በአማራ ገበሬዎች ላይ ለመውሰድ ትዕዛዝ እንዳስተላለፈ የሰጠውን ትዕዛዝ ባለፈው ሳምንት በማኅበራዊ የብዙኃን መገናኛ መውጣቱ ይታወሳል፡፡ ወያኔ ሽፈራውን በዐቢይ ሸንጎ […]
አብይ ለማ ገዱና አጋሮቻቸው እውነቱን የአላችሁበት ድርጅት ጠላታችን መሆንን አትዘንጉ (ሰርፀ ደስታ)

May 23, 2018 በአዴን ሲጀምር የአማራን ሕዝብ ለማጥቃት የተደራጀ እንጂ ለአማራ ሕዝብ እንዳልሆን በራሱ በቡድኑ ፕሮገራም ተብለው በተቀመጡ ሰነዶች ማይት ይቻላል፡፡ በተለይ በተለያዩ ክልሎች የሚኖረውን የአማራ ተወላጅ ነፍጠኛ በማለት በአገሪቱ በሙሉ በጠላትነት ሁሉም በእዚህ ሕዝብ ላይ አንድ ሆኖ እንዲቆም ሲሰሩ ከነበሩ ቡድኖች በዓዴን የተባለው በዋናነት ቢጠቀስ ስህተት አደለም፡፡ በወንበዴዎቹ የመጀመሪያ ዓመታት የቀድሞው ኢህዲን ቡድን ዋና […]
መጨረሻዎች እንደመነሻዎች አያምሩም (ጠ/ሚ ዶ/ር አቢይም አንብልኝ!)

May 23, 2018 – አጠቃላይ ምሕረት ዘገዬ (mz23602@gmail.com) ከጠቅላላ ዕውቀት ግብይት ባለፈ ብልኅና አስተዋይ ትግሬዎች ይህን ወረቀት በተለዬ ትኩረት ቢያነቡልኝ ደስ ይለኛል፡፡ ሕወሓት በኢትዮጵያና ሕዝቧ ላይ ያደረሰውንና እያደረሰ ያለውን ተዘርዝሮ የማያልቅ ግፍና በደል የማያውቅ የትግራይ ማኅበረሰብ አባል ይኖራል ተብሎ አይገመትም፡፡ የዚህ ሁሉ ሰቆቃና ዋይታ የዞረ ድምር ምን ሊያከትል እንደሚችል ደግሞ – በአንዳንዶች ግንዛቤ ጥቂት እንደሆኑ […]
መንግሥቱ እና የኮሎኔል አጥናፉ ኑዛዜ

Surafel Atnafu አጭር የምስል መግለጫ መስከረም 2/1967 የአብዯት በዓል- ከግራ ወደ ቀኝ መንግሥቱ ኃይለማርያም (ሻለቃ)፣ ተፈሪ በንቲ (ብ/ጄኔራል)፣ አጥናፉ አባተ (ሻለቃ) ኮ/ል መንግሥቱ ደርግን ኮትኩተው አሳድገውት ይሆናል። ነገር ግን አልወለዱትም። የደርግ እናትም አባትም ኮ/ል አጥናፉ ናቸው። ኾኖም ደርግ ፈጣሪውን መልሶ ለመብላት የወሰደበት ጊዜ ከ5 ዓመት ያነሰ ነበር፡፡ ኅዳር 3/ 1970 በዕለተ ቅዳሜ አጥናፉ ተገደሉ። “አብዮት […]
የዳቦና የወተት እጥረት በአዲስ አበባ

Image copyright FEDERICO PARRA ባለፉት ሁለት ሳምንታት የአዲስ አበባ የዳቦ መጋጋሪያና ማከፋፈያ ደጃፎች ረጃጅም ሰልፎችን ሲያስተናግዱ ሰንብተዋል። በሌላ በኩል የሸቀጣ ሸቀጥ መሸጫ መደብሮችም ከሁለት በላይ የታሸጉ ወተቶችን እንደማይሸጡ የሚደነግጉ ማስታወቂያዎችን ለጥፈው ተስተውለዋል፥ የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ ችግሩ ባለፈው ሚያዝያ ወር ቢስተዋልም በያዝነው የንግቦት ወር ግን ተቀርፏል ባይ ነው። በመዲናይቱምና በሌሎችም የአገሪቱ አካባቢዎችም የትንሳዔ በዐልን ተከትሎ […]
“ትጥቅ ትግል ወደ ዴሞክራሲ አያመራም” አቶ ሌንጮ ለታ

የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ግንባር አምስት አባላትን የያዘ ልኡካን ቡድን ወደ አዲስ አበባ ዛሬ ገብቷል። የቀድሞ የኦነግ አመራርና የኦዴግ ሊቀ-መንበር አቶ ሌንጮ ለታ ከመንግሥት ጋር ለመወያየት ሙከራ ሲያደርጉ ስድስት ዓመታት እንደፈጀባቸው ተናግረው አሁን ያለውን ለውጥ ተከትሎ ጥሪ ሲደረግላቸው መምጣታቸውን በቦሌ አየር ማረፊያ በነበረው ጋዜጣዊ መግለጫ ተናግረዋል። ከኢትዮጵያ መንግሥት ጋር አብሮ ለመስራት መወሰናቸውንም ተከትሎ መንግሥት አሸባሪ ብሎ ከፈረጀው […]
ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ግዕዝ ቋንቋን ማስተማር መጀመሩን አስታወቀ

May 22, 2018 /ኢትዮጵያ ነገ ዜና/፡- ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ በሀገሪቱ ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ ግዕዝ ቋንቋን ማስተማር መጀመሩን አስታወቀ። በሀገሪቱ ታሪክ የግዕዝ ቋንቋ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርሲቲያን አልፎ በዩኒቨርሲቲ ደረጃ ሲሰጥ የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ የመጀመሪያ መሆኑንም ጨምሮ ገልጿል። ዩኒቨርሲቲው በየትኛውም የትምህርት መስክ የመጀመሪያ ድግሪ ያላቸውን ተማሪዎች ተቀብሎ በሁለተኛ ዲግሪ መርሃ-ግብር ማስተማር መጀመሩን ገልፆ እስካሁን ከ32 በላይ ተማሪዎችን መቀበሉንም […]
