Africa 1914 on Map

 · Africa can and will only advance through African integration, which can be realized through the Federal United States of Africa” ~ Cheikh Anta Diop We can only prosper in a system designed by ourselves. Our economy, politics, education and our society as a whole is tailored like the westerns own and that’s exactly why we’re […]

የየካቲት 12ቱ ጸረ ፋሽስት ተጋድሎ መሪ ታላቁ አርበኛ ደጃዝማች ለጥ ይበሉ ገብሬ ፟ አቻሜለህ ታምሩ

  · እነሆ ጀግና — የየካቲት 12ቱ ጸረ ፋሽስት ተጋድሎ መሪ ታላቁ አርበኛ ደጃዝማች ለጥ ይበሉ ገብሬ የካቲት 12 ቀን 1929 ዓ.ም. በማርሻል ግራዚያኒ ላይ የተፈጸመው የቦንብ ጥቃትና የአርበኛነት ተጋድሎ ሲነሳ ቀድመው የሚታወሱት የኤርትራ ጠቅላይ ግዛት ተወላጆቹ አብርሃ ደሞጭና ሞገስ አስገዶም፤ ግፋ ካለም የሐረርጌው አማራ ሰምዖን አደፍርስ ብቻ ናቸው። በተለይም በዘመነ ደርግ ሻዕብያና ጀብሀ የተባሉ ተገንጣዮችን ትርክት […]

 · እነሆ ጀግና! ፟ አቻሜለህ ታምሩ

 · እነሆ ጀግና! የአባቶቻችን ኢትዮጵያ ከራሳቸው በላይ ለሆነ አላማ የኖሩ፣ ራሳቸውን ከነሱ በላይ ለሆነ አላማ የሰጡ፣ ከአንድ ግለሰብና ከአንድ ትውልድ በላይ በላይ ለሆነ አላማ ራሳቸውን ያስገዙ አገር ወዳድ ልጆች ነበሯት። ከራሳቸው በላይ ለሆነ አላማ ቆመው፣ ራሳቸውን ድልድይ አድርገው ክፉውን ዘመን ያሻገሩና የተረከቧትን የአባቶቻቸውን አገር ከነሙሉ ክብሯ ለቀጣዩ ትውልድ ካስረከቡ የኢትዮጵያ የምንጊዜም ጀግኖች መካከል ስመጥሩ አርበኛ ደጃዝማች […]

የክልሎችን የድጎማ በጀት የሚቆጣጠር ኮሚሽን ለማቋቋም እንቅስቃሴ ተጀመረ

ፖለቲካ የክልሎችን የድጎማ በጀት የሚቆጣጠር ኮሚሽን ለማቋቋም እንቅስቃሴ ተጀመረ 10 April 2022 ምስጋናው ፈንታው የክልሎችን የድጎማ በጀት የሚቆጣጠር ኮሚሽን እንዲቋቋም እንቅስቃሴ መጀመሩን የፌዴሬሽን ምክር ቤት አስታወቀ።  ክልሎች ከፌዴራል መንግሥት የሚያገኙትን የድጎማ በጀት የሚቆጣጠረው የፌዴሬሽን ምክር ቤት የበጀት ክፍፍሉ ራሱን በቻለ ተቋም እንዲመራ በጥናት የተደገፈ እንቅስቃሴ መጀመሩን፣ በፌደሬሽን ምክር ቤት የፊስካል ጉዳዮችና የክልሎች የተመጣጠነ ዕድገት ጥናት ዳይሬክተር ዋቅቶሌ […]

ለፖለቲካ ፓርቲዎች ከተመደበው የገንዘብ ድጋፍ ብልፅግና ከፍተኛውን ድርሻ ሲያገኝ ዝቅተኛው ለትዴፓ ተመደበ

ፖለቲካ 30 March 2022 ሲሳይ ሳህሉ በ2014 ዓ.ም. በጀት ዓመት ለፖለቲካ ፓርቲዎች በመንግሥት ከሚደረገው የገንዘብ ድጋፍ፣ ከ19 አገር አቀፍ የፖለቲካ ፓርቲዎች መካከል ብልፅግና 7.7 ሚሊዮን ብር በመውሰድ ከፍተኛ ድርሻ ሲይዝ፣ የትግራይ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ትዴፓ) 281 ሺሕ ብር በመውሰድ ዝቅተኛውን ድጋፍ ያገኘ ፓርቲ ሆኗል፡፡ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ማክሰኞ መጋቢት 20 ቀን 2014 ዓ.ም. ከተለያዩ አገራዊና […]

በትግራይ ክልል 73 የረድኤት ድርጅቶች መኖራቸውን ኮሚሽኑ ገለጸ

ፖለቲካ 30 March 2022 አማኑኤል ይልቃል በምግብና በምግብ ነክ ባልሆኑ አቅርቦቶች ላይ የተሰማሩ 73 የረድኤት  ድርጅቶች፣ በትግራይ ክልል ውስጥ እየተንቀሳቀሱ መሆኑን ብሔራዊ የአደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን አስታወቀ፡፡ በድርጅቶቹ አማካይነትም ከሐምሌ 2013 ዓ.ም. ጀምሮ 1.2 ቢሊዮን ብር ወደ ትግራይ ክልል መላኩን ኮሚሽኑ ገልጿል፡፡ በክልሉ ውስጥ ያሉት 73 ግብረ ሰናይ ድርጅቶች የውጭና የአገር ውስጥ መሆናቸውን ለሪፖርተር […]

የዓለም ባንክ ኢትዮጵያንና ጂቡቲን ዳግም ለሚያስተሳስረው የኃይል ማስተላለፊያ መስመር ድጋፍ ሊያደርግ ነው

ፖለቲካ 30 March 2022 ዮሐንስ አንበርብር መስመሩ ኢትዮጵያን ከሳዑዲና ሌሎች ዓረብ አገሮችንም እንደሚያገናኝ ታሳቢ ተደርጓል ኢትዮጵያና ጂቡቲን ዳግም ለሚያስተሳስረው ሁለተኛው የኃይል ማስተላለፊያ መሠረተ ልማት ግንባታ፣ የዓለም ባንክ የገንዘብ ድጋፍ ለማድረግ የመጨረሻ ግምገማ ላይ መሆኑ ታወቀ።  ለሁለተኛው የኃይል ማስተላለፊያ መሠረተ ልማት ግንባታ ከሚያስፈልገው ወጪ ውስጥ፣ ከኢትዮጵያ ድንበር በኋላ ያለውን የመሠረተ ልማት ግንባታ የዓለም ባንክ እንዲሸፍን በጂቡቲ መንግሥት መጠየቁ ታውቋል። በጂቡቲው ፕሬዚዳንት ኢስማኤል ኦማር ጌሌ የተመራ የልዑካን ቡድን በኢትዮጵያ ለሁለት ቀናት የቆየ የሥራ ጉብኝት አድርጎ ማክሰኞ መጋቢት 20 ቀን 2014 ዓ.ም. ወደ ጂቡቲ የተመለሰ ሲሆን፣ የልዑካን ቡድኑ በኢትዮጵያ ቆይታው ከጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) እና ከሌሎችም ከፍተኛ ባለሥልጣናት ጋር ከመከረባቸው ጉዳዮች መካከል፣ የኃይል አቅርቦትና የጋራ መሠረተ ልማት ዝርጋታ እንደሚገኝበት፣ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ያወጣው መረጃ ያመለክታል። ለሁለተኛው የኃይል ማስተላለፊያ መስመር ግንባታ የጂቡቲ መንግሥት ያቀረበውን የብድር ጥያቄ፣ የዓለም ባንክ ሲገመግም የቆየ ሲሆን፣ የባንኩ ቦርድ በብድር ጥያቄው ላይ በጥቂት ሳምንታት ውስጥ ውሳኔ ይሰጣል ተብሎ ይጠበቃል። ከኢትዮጵያ ወደ ጂቡቲ የተዘረጋውንና በአሁኑ ወቅት የኤሌክትሪክ ኃይል እየቀረበበት የሚገኘው የኃይል ማስተላለፊያ መስመር፣ በዓለም ባንክ የገንዘብ ድጋፍ የተገነባ ሲሆን፣ ሁለተኛው የኃይል ማስተላለፊያ ግንባታ ደግሞ በአፍሪካ ልማት ባንክና በዓለም ባንክ የፋይናንስ ድጋፍ እንደሚከናወን ታውቋል። በኢትዮጵያ በኩል የሚገነባውን የኃይል ማስተላለፊያ መስመር ግንባታ ለማከናውን የሚያስፈልገውን ወጪ የአፍሪካ ልማት ባንክ ለመሸፈን ባለፈው ዓመት በነሐሴ ወር እንደወሰነ መረጃዎች ያመለክታሉ።  በኢትዮጵያ በኩል የሚገነባው መስመር ከአፋር ክልል ሰመራ ከተማ እስከ ጂቡቲ ድንበር ጋላፊ የሚዘልቅ 102 ኪሎ ሜትር የኃይል ማስተላለፊያ አንዱ ሲሆን፣ በሌላ በኩል ከኮምቦልቻ አንስቶ በአፋር ሚሌ ከተማ ውስጥ እስከሚገነባው የኃይል ማከፋፈያ ጣቢያ የሚዘረጋ 170 ኪሎ ሜትር የሚሸፍን የኃይል ማስተላለፊያ መስመር ይገኝበታል። ይህንን ግንባታ ለማከናውን የሚያስፈልገውን አጠቃላይ ወጪ የአፍሪካ ልማት ባንክ የሚሸፍን ሲሆን፣ ለዚህም 83 ሚሊዮን ዶላር ብድር ፈቅዷል። በጂቡቲ በኩል የሚገነባው መስመር ከጋላፊ ድንበር እስከ ነጋድ የተባለ አካባቢ የሚዘልቅና 190 ኪሎ ሜትር የሚሸፍን የኃይል ማስተላለፊያ መስመር ሲሆን፣ ለዚህ ግንባታ የሚያስፈልገውን 55 ሚሊዮን ዶላር የዓለም ባንክ በብድር እንዲያቀርብ የጂቡቲ መንግሥት ጠይቋል። የጂቡቲ መንግሥት ለዓለም ባንክ ያስገባው የፕሮጀክት ሰነድ እንደሚያስረዳው፣ ሁለተኛው የኃይል ማስተላለፊያ መስመር ግንባታ ጂቡቲ ያለባትን ከፍተኛ የኃይል አቅርቦት ችግር ለመፍታት፣ እ.ኤ.አ. እስከ 2035 እተገብረዋለው ላለችው የኢኮኖሚ ልማት መርሐ ግብር ትልቅ ፋይዳ ይኖረዋል። ኢትዮጵያንና ጂቡቲን ካስተሳሰረው የመጀመሪያው የኃይል ማስተላለፊያ መስመር በአማካይ 80 ሜጋ ዋት ኃይል ጂቡቲ እያገኘች መሆኑን የሚያመለክተው መረጃው፣ ይህ የኃይል አቅርቦት ካለው የጂቡቲ የኃይል ፍጆታ ውስጥ 70 በመቶ የሚሆነውን ይሸፍናል። ይሁን እንጂ ይህ የኃይል አቅርቦት ጂቡቲ ካቀደችው ግዙፍ የኢኮኖሚ ልማት መርሐ ግብር አንፃር መገምገም ኢምንት እንደሆነና ሁለተኛው የኃይል ማስተላለፊያ መስመር ግንባታ ሲጠናቀቅ ግን፣ ጂቡቲ ከኢትዮጵያ የምታገኘውን የኃይል አቅርቦት ወደ 220 ሜጋ ዋት እንደሚያደርሰው ያመለክታል። ይህ ፕሮጀክት የጂቡቲን የኃይል አቅርቦት ችግር ከመፍታቱ ባሻገር፣ የዓለም ባንክ የሰሜን አፍሪካና የመካከለኛው ምሥራቅ የዓረብ አገሮችን በኤሌክትሪክ ኃይል ለማስተሳሰርና ቀጣናዊ የኃይል አቅርቦት ገበያ ለመመሥረት ከወጠነው የመካከለኛ ጊዜ ዕቅድ ጋር የሚጣጣም መሆኑን፣ የጂቡቲ መንግሥት የፕሮጀክት ሰነድ ያሳያል። ሰነዱ እንደሚገልጸው ጂቡቲ የሰሜን አፍሪካና የመካከለኛው ምሥራቅ የዓረብ አገሮችን (ፓን ዓረቢያ የኤሌክትሪክ አቅርቦት ገበያ) አባል አገር በመሆኗ፣ ሁለተኛው የኢትዮ ጂቡቲ የኃይል መስመር መገንባት የኢትዮጵያ ብሔራዊ የኃይል ቋትን በመካከለኛ ጊዜ ዕቅድ ውስጥ በጂቡቲ በኩል ከሳዑዲ ዓረቢያ በማገናኘት የፓን ዓረቢያ የኃይል አቅርቦት ትስስርን እንድትቀላቀል ያደርጋታል። ጂቡቲን ከሳዑዲ ዓረቢያ ጋር በየመን በኩል በኃይል የማስተሳሰር ውጥን የተያዘ ሲሆን፣ በአሁኑ ወቅት በየመን ያለው ፖለቲካዊ አለመረጋጋት ከተቀረፈ ፕሮጀክቱን በአጭር ዓመታት ውስጥ ለመጀመር ዕቅድ መያዙን መረጃዎች ያመለክታሉ። የየመን ቀውስ የሚቀጥል ከሆነ ፕሮጀክቱ ሊዘገይ እንደሚችል ወይም የፕሮጀክት ወጪውን ከፍ በማድረግ ከየመን ውጪ በቀይ ባህር ውስጥ በሚያልፍ የባህር መስመር ከሳዑዲ ዓረቢያ የማገናኘት አማራጭ መኖሩንም፣ የተገኙ ሌሎች መረጃዎች ያመለክታሉ። ግብፅና ሳዑዲ ዓረቢያ ብሔራዊ የኤሌክትሪክ ኃይል ቋቶቻቸውን ለማገናኘት፣ ከግብፅ ባደር እስክ ኤል መዲናህ የሚዘረጋ ባለ 500 ኪሎ ቮልት የኃይል ማስተላለፊያ መሠረተ ልማት ግንባታ ፕሮጀክት ተግባራዊ ለማድረግ በእንቅስቃሴ ላይ ናቸው።  በሌላ በኩል ዩሮ አፍሪካ ኢንተርኮኔክተር የተሰኘ የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት ትስስር ፕሮጀክት የግብፅን ብሔራዊ ቋት በባህር ውስጥ በሚዘረጋ የኃይል ማስተላለፊያ መስመር ከግሪክ የማገናኘት ፕሮጀክት፣ እ.ኤ.አ. በ2020 ይፋ መደረጉን መረጃዎች ያሳያሉ። በጂቡቲ መንግሥት የፕሮጀክት ሰነድ ላይ እንደተገለጸው፣ በመካከለኛ ጊዜ ውስጥ በጂቡቲና በሳዑዲ ዓረቢያ መካከል የኃይል አቅርቦት ትስስር መሠረተ ልማት የሚገነባ ከሆነ፣ በኢትዮጵያ ያለውን ዕምቅ የኤሌክትሪክ ኃይል አቅም ወደ ሳዑዲ ዓረቢያ፣ እንዲሁም ወደ ግብፅና ለሌሎች የዓረብ አገሮች ኤክስፖርት የማድረግና ሜዲትራኒያን በማቋረጥ የአውሮፓ የኃይል ገበያን የመቀላቀል ዕድል መኖሩን ያመላክታል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) ከአንድ ወር በፊት በብራሰልስ የተካሄደውን የአውሮፓና የአፍሪካ የጋራ ፎረም ተካፍለው ሲመለሱ በሰጡት መግለጫ፣ ኢትዮጵያ ዕምቅ የሆነውን የኤሌክትሪክ ኃይል ሀብቷን ለአውሮፓ ገበያ ጭምር የማቅረብ ዕድል እንዳላት መናገራቸው ይታወሳል።

የፖለቲካ ፓርቲዎች ገዥው ፓርቲ እንግልት እያደረሰብን ነው ሲሉ አቤቱታ አቀረቡ

ፖለቲካ 30 March 2022 ሲሳይ ሳህሉ ፓርቲዎቹ ያቀረቡት አቤቱታ እውነት መሆኑን ምርጫ ቦርድ አረጋግጧል በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች የሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ ገዥው ፓርቲ ብልፅግና በተለያዩ መንገድ የመብት ጥሰት እየፈጸመባቸው እንደሆነ አቤቱታ አቀረቡ፡፡ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ከአገራዊና ከክልላዊ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር፣ ማክሰኞ መጋቢት 20 ቀን 2014 ዓ.ም. በተለያዩ አጀንዳዎች ላይ በአዲስ አበባ ውይይት አካሂዷል፡፡ በውይይቱ ተሳታፊ […]

ጋዜጠኛ ፤ የታሪክ ፤ ተመራማሪ ፣ ደራሲ አምባሳደር ዘውዴ ረታ…!!! – ታሪክን ወደኋላ

29/03/2022  ጋዜጠኛ ፤ የታሪክ ፤ ተመራማሪ ፣ ደራሲ አምባሳደር ዘውዴ ረታ…!!! ታሪክን ወደኋላ አምባሳደር ዘውዴ ረታ ከአባታቸው ቀኝአዝማች ረታ ወልደአረጋይ ከእናታቸው እማሆይ አፀደ ረድኤቱ በወርሃ ነሐሴ 7 ቀን 1927 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ ተወለዱ፡፡ እድሜያቸው ለአቅመ ትምህረት ሲደርስ በዘመኑ በነበረው ማህበረሰባዊ ልማድ መሰረት የአማርኛ እና የግዕዝ ቋንቋ ትምህርታቸውን በሚገባ ከተማሩ በኋላ በ 7 አመት እድሜያቸው […]

ተስፋዬ ደበሳይ- አንጋፋው ኢህአፓ—-ጸሐፊ፡ አፈንዲ ሙተቂ

.አፈንዲ ሙተቂ/Afendi Muteki- Ethnographic Researcher and Author Yesterday at Thursday,24 March 2022 14:46  · ተስፋዬ ደበሳይ- አንጋፋው ኢህአፓ —- ጸሐፊ፡ አፈንዲ ሙተቂ —— ከኢህአፓ መስራቾች አንዱ የነበረው እና የድርጅቱ አውራ ታጋይ የነበረው ሰው ከሞተ ትናንት መጋቢት 14/2014 አርባ አምስተኛ ዓመቱን ደፍኗል። እኛም ዝክሩን በማስመልከት ይህንን ጽሑፍ ልናስነብባችሁ ነው። — አዎን! ዶ/ር ተስፋዬ ደበሳይ ነው፡፡ ኢህአፓዎች ከማንም […]