April 2, 2019

ምን እየተሰራ እንደሆነ የገባችሁ ካላችሁ እስኪ ማብራሪያ ስጡን ወደ አላስፈላጊ አናሊቲካለ ኢንቨስቲጌሽን ከመሄዳችን በፊት፡፡ እውነት ለመናገር ነገሮች እንዲህ በወረደ ሁኔታ የሚሸውዱን ከሆነ ችግሩ የሸዋጆቻችን ሳይሆን የእኛ ነው፡፡ በቃ እኛን ከማንነታቸው አውርደናቸዋል ብለው እንደፈለጋቸው ይሆናሉ፡፡ ባለፈው ዶ/ር በድሉ ዋቅጂራ የተባሉ ሰው የሉሲን የሰላም አስከባሪነት ተልዕኮ ግልብ ብለው ያጣጣሉበት ጽሁፋቸው በአግራሞት ነው ያነበብኩት፡፡ እውነቱን ቁጭ ስላረጉት እያሳቀኝ ሁሉ ነበር፡፡
እኔ የአብይን ዲስኩር ብዙም ከማይመቻቸው ነኝ፡፡ ጠቅላይ ሚኒስቴር ከሆነ በኋላ ጥሩ የሆነ መስሎኝ ነበር፡፡ ብዙም ስለእሱ መልካም ነገሮችን ጽፌያለሁ፡፡ በቅንነት አገርን ወደ ሰላም ይወስዳል በሚልና ለዛም እየሠራ ስለመሰለኝ ነበር፡፡ በቆይታ ሳየው ነገሮች ወደ ሠላም እየሄዱ አይመስልም፡፡ የሠላም ሚኒስቴር እስከማቋቋም የደረሰው የአብየሄ መንግስት አንደም ቦታ ሠላምን ለማምጣት የተለየ ይሄ ነው የሚባል እንቅስቃሴ የለም፡፡ በሁሉም ቦታዎች ችግር አለ፡፡ ችግሩ ደግሞ አሁን መሀል አገር ላይ እየፈነጨ ነው፡፡ ለምሳሌ የአዲስ አበባ ጉዳይ በጣም አደገኛ የሆነ አካሄዶች በሕግ ግልጽ የሆኑ እውነቶች አብይ እንድም ቦታ እውነቱን ሊናገር አልሞከረም፡፡ ሁሉንም በማለባበስ ያልፈዋል፡፡ እስክንድር ግልጽ ነው፡፡ አዲስ አበባ የኦሮሚያ ጎረቤት እንጂ ኦሮሚያ ውስጥ አደለችም፡፡ የኦሮሚያ ዋና ከተማም አዳማ ነው፡፡ ይህ ብቻ አደለም አንድም የኢሕአዴግ ባለስልጣን አዲስ አበባ የአዲስ አበቤዎች ነች ሊል አይፈልግም፡፡ ግልጽ ነው፡፡ የትኛውም የአስተዳደር ወሰን የነዋሪዎቹ ነው፡፡ በዛ ግዛት የሚመርጡ የሚመረጡ እነዛ ነዋሪዎች ናቸው፡፡ ይሄ የሁላችንም ነች የሚል ማደናገሪያ እጅግ አደገኛ የሆነ ሴራ አለበት፡፡ መጀመሪያ በዛ አስተዳደር ውስጥ የመምረጥና የመመረጥ ስልጣን ያለው ነዋሪው እንጂ ከሌላ ክልል የሚመጣ ወይም የአፍሪካ መዲና ነችና አፍሪካዊ በሙሉ አደለም፡፡ ይሄን አስረግጦ መናገርና መጥራት ሲገባው አሁንም በማለባበስ እየተደሰኮረ ነው፡፡ የበቀደሙ የእስክንድርን መግለጫ መከልከል ሲታሰብ ነገሮች አስቂጭ ድራማ ሆነው ነው ያገኘኋቸውለ፡፡ የእስክንድር የራስ ሆቴሉ ስብሰባ አይነተኛ የመናገር ነጻነት እንደሌለ በግልጽ ያሳየ ነበር፡፡ ለደህንነቱ ስንል ነው ብለዋል፡፡ ከቤተመንግስት መግለጫ ይሰጣል ብለዋል፡፡ እስኪ እንያቸው፡፡ ጉዳዩ የእስክንድር ጉዳይ መስሏቸው ከሆነ ጥሩ ያሰቡ አይመስለኝም፡፡
ሌላው በየቦታው ያሉ ችግሮችን በዘላቂነት ለመፍታት ሕዝብን ከሕዝብ የሚያቀራርብ ልዩ የሚዲያ ፕሮገራሞች በማዘጋጀትና በመሥራት ሕዝቡን ማረጋጋትና ወደ ሠላም መመለስ ሲገባቸው ጭራሽ በሠላም የሚኖሩትንም ቤት በማፍረስ ይሄው የተፈናቃዩን ቁጥር እየበዙት ናቸው፡፡ የቤት ማፍረስ የወሮበላ አሰራር እንጂ በምንም መስፈርት ማንም ተነስቶ በግሬድር የማንንም ቤት የሚያፈርስበት ሕጋዊ አግባብ ያለ አይመስለኝም፡፡ በዘልማድ የወሮበላ አሰራርን ስለለመዱ ሁሉም በጉልበት እንጂ በሕግ እንደማይሰራ ግልጽ ነው፡፡ አሁን እንደምናየው የቤት ማፍረስ ዘመቻ ከአገር አገር ነው፡፡ አይገርምም?! በግልጽ የምናውቃት የወያኔ ጭር ሲል አልወድም ሴራ ነው፡፡ ለመሆኑ በየትኛው ሕግ ነው ያልፍርድ ቤት ውሳኔ የአንድን ሰው ንብረት ሕገ ወጥ በሚል ማፍረስ የሚቻለው፡፡ ከላይ ከሕገ-መንግስት ተብሎ ከተቀመጠው ሕግ ውጭ ዛሬ አዲስ አበባ ላይ የሚሆነውን እያየን ነው፡፡ ማንም ሕግ ሲጣስ የሚጠይቅ የለም፡፡ የሕግ ባለሙያዎች ምን እየሠሩ እንደሆነ ባይገባኝም ግን የኢትዮጵያ ሕዝብ በሕገ-ወጥ ባለሥልጣኖች ብዙ ችግር እየደረሰበት ነው፡፡ ሕጉን ወይ አያቁትም ወይ ማን አለብኝነት ነው፡፡ ለነገሩ ሰዎቹ እኮ እነዛው ናቸው፡፡ ምንም የተቀየረ የለም፡፡ አሁንም ደራማ እየሠሩብን ነው የሚመስለው፡፡ በጣም አዝናለሁ፡፡ ይሄን ማለት ፈቅጄ አደለም ግን ነገሮች አልተመቹኝም፡፡
አብይ የሕዝብና አገረሩን ሠላም ወደጎን ትቶት ሚዲያዎቹን የእሱን ዶኪመንተሪ ለማሰራጨት እየተጠቀመባቸው ነው፡፡ እንደ እውነቱ አብይ በዚህ ዶኪመንተር እየወረደ እንደሆነ እየገባው አይመስልም፡፡ ሲጀምር የትኛውን ጥሩ ነገር ሰርቶ ዶኩመነተሪ መሥራት እንዳስፈለገ አልገባኝም፡፡ ምን በሌለበት የመለመላል ምን አይት ሆኖ እንጂ እውን አብይ እኔ ተፈራና በረከት የሚደመሙበት እውቀትና ችሎታ ትንሽ የዓለምን የዛሬ እውነት ለሚረዳ ይሄ ቁም ነገር ነው? ለማንኛውም በዚህ መልኩ የራሱንም ገጽታ ባያጠፋ ጥሩ ነው፡፡ እኔ አብይ ወደ ሥልጣን ከመምጣቱ በፊት ሲናገራቸው የነበሩትን ዲስኩሮች ስከታትል አንድም ቦታ ክሪቲካል (ወሳኝ) ነገሮችን ሲናገር አልሰማሁትም፡፡ በትልልቅ ጉዳዮች ነገሮችን እያገዘፈ ለማያውቁ ሰዎች ማጃጃያ ነው ሆኖ የሚሰማኝ፡፡ ሥልጣን ከያዘ በኋላ ጥሩ ነው ስል የሆነ ቦታ ሲደነቁል ነው የማገኘው፡፡ በትልቁ የአገር ካባ አልፈንው እንጂ ብዙ ቦታዎች አገርን ባለመጠነ ሁኔታ ነው የሚያወራውም የሚንቀሳቀሰውም፡፡ አሁንም እላለሁ፡፡ ይሄ ራሱን ማካበድና ማስተዋወቅ አቁሞ እንደመሪ አገርንና ሕዝብን መምራት ቢችል ጥሩ ነው፡፡ አሁን ሕዝቡ ስለአብይ ያለው ስሜት ጥሩ አደለም፡፡ እንደገና የማይረባ (ግልብ) ነገር እየጨመረበት ለአገርም አደጋ ሊሆን እንሚችል ይሰማኛል፡፡ ይሄ ስለአሱ ዶኩመንተሪ ተብሎ የተለቀቀውን ፊልም ከማሳየት ሕዝብ-ከሕዝብ የሚያቀራርቡ ፕሮግራሞች ቢሰሩ ጥሩ ነው ባይ ነኝ፡፡ የእሱ ዶኩመንተር ሲጀምር መልካም ሥራ ተብሎ ያለ ነገር የለውም ሲቀጥል በሕዝብና በአገር ሀብት ራስን ማካበድ እንደሆነ ሳይገበው የበለጠ ሕዝብን የሚያቆስል ስራ እየሰራ ነው፡፡ አደገኛም ሊሆን ይችላል፡፡ በነገራችን ላይ አንድ ምህረት ደበበ የተባለ ግለሰብ የሚያፏጨውን ፉጨት አልወደድኩትም፡፡ አብይ አድገናቂው ነው፡፡ አብይ ማድነቅ ይችላል እኔ ግን መጃጃል አልፈልግም! ችግር አለ!
በሌላ በኩል አገሪቱ ውስጥ የሚሰሩ ፕሮጄክቶች በምን መልኩ እንደሆነ አላውቅም፡፡ የቤተመንግስቱን ፕሮጄክት ነው እንደ ትልቅ ነገር በየቀኑ የሚነገረን፡፡ ሌላውስ? በሆነ ጊዜ ግድቡ ሊያልቅ ነው፣ ስኳር ሊመረት ነው፣ ማዳበሪያ ሊመረት ነው ወሬ ነበር፡፡ እሱም ራስን ማስተዋወቂያ እንዳይሆን፡፡ አሁን ደግሞ ጭራሽ የአገሪቱ ምንዛሬ አደጋ ላይ ነው እየተባለ ነው፡፡ በሚሊየኖች ዶላር እነደልብ በመኪና ተጭኖ በሚወጣባት አገር ይሄ አይገርምም፡፡ ባለፈው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 14 ሚሊየን ብር በካሽ ለአንድ ግለሰብ ከሰጠ በኋላ በጥርጣሬ ገንዘቡ ከባንኩ ሳይወጣ እንደተያዘና የተጭበረበረ እንደሆነ እነደ ልዩ ጀብዱ ሲያወሩልን ነበር፡፡ ልብ በሉ እንግዲህ በካሽ ይሄን ያህል ገንዘብ ማውጣት የሚቻልባት አገር እንግዲህ ኢትዮጵያና ሌሎች በወሮበሎች የሚመሩ አገራት መሆን አለባቸው፡፡ በየትኛም እኔ በማውቀው አገር ግፋ ቢል ጥቂት አስር ሺዎች የማይሞላ ገንዘብ በካሽ ከተሰጠ አስተማማኝ ምክነያት ቀረቦበትና ገንዘቡን በባንክ ለማዘዋወር የማያስችል ከሆነ ነው፡፡ ጉዳዩ ከገነዘቡ መጥፋት ጋር ብቻም ሳይሆን ከአገር ደህንነት ጋርም እጅግ ቁርኝት ያለው ነው፡፡ ለማንኛውም ግን ከሁሉም ቅድሚያ ግን ሕዝብ ሠላም ይሁን፡፡
ኢሳት ግቢ ውስጥ እሳት የተቀጣጠለ ይመስላል፡፡ አበበ ገላውና ኤርሚያስ ለገሰ፡፡ እኔ ስለ አበበ ብዙ አላውቅም ነበር፡፡ እንደ እውነቱ ግን አበበ አሁን ከሚናገራቸው በሳል ሰው ይመስለኛል፡፡ ደግሞም ከልቡ ነው፡፡ ኤርሚየስን ግን ከበፊት ጀምሮ እጅግ እጠረጥረው ነበር አሁን ለይቶለታል፡፡ ስለዚህ ግለሰብ ብዙ ጊዜ ተናግሬ ነበር፡፡ አንዳንዶቹ ጽሁፎቼ እንደውም በግልጽ አደገኛነቱን ስለሚጠቁሙ ሳተናው ሊያወጣቸው አልፈለገም፡፡ የእኔ ችግር የኤርሚየስ የግል ጉዳይ ሳይሆን ከኢትዮጵያ ወደ አሜሪካ የገባበት ከዛም ኢሳትን የተቀላቀለበት ሁኔታ ለወያኔ ለመሥራት ነው የሚል ጽኑ እምነት አለኝ፡፡ ለዛ ደግሞ በገዛ ገንዘባችን እሱን እየቀለብን ወያኔ ደግሞ ጠቀም ያለ ጉርሻ ትሰጠዋለች የሚል እምነት ነው ያለኝ፡፡ ይሄ የሞኝነት እንዳይመስላችሁ፡፡ ይሄን ለመገመት እስኪ ኤርሚየስ ያዘጋጃቸውን የኢሳት ፕሮግራሞች ወደኋላ ሄዳችሁ አድምጡ፡፡ ሁሌም ሲነግረን የነበረው ወያኔ እንደማይቻልና አርፈን እንድንቀመጥ ነበር፡፡ በመጨረሻ ወያኔ ስትፍረከረክ እሱንም ብርክ ይዞት ነበር፡፡ አሁን ከአብይ ጋር አልተመቸውም፡፡ ጀዋርም እንደዛው ነው የሆነው፡፡ ሕዝቤ ሆይ አትሸወድ ይሄ ግለሰብ ለወያኔ እየሰራ ነው፡፡ ትላንት በአንድ ስብሰባ ሲናገር ብዙ አጭብጫቢ ነበረው፡፡ ጀነራል ተፈራን ያሳሰረው አብይ ነው፡፡ ውሾን ያነሳ ውሾ ነው ምናም፡፡ እነዴ ምን ነካን፡፡ ለምን መረጃ ያለው አያወጣም ታዲያ? ቢያወጣውም እኮ ግፋ ቢል አሁን የተናገረውን ያህል ነው፡፡ እናቴ ኢትዮጵያዊ ስትሞት ኦሮሞ?ኧረ ሕዝቤ እንዴት እንዲህ ያሉ ተራ ሰዎች ይቆምሩብሀል? በነገራችን ላይ ሀብታሙ አያሌውና ተወልደ በየነንም እንዲሁ ነው የማስባቸው፡፡ ሀብታሙ በእስር ቤት ተሰቃየ ተብሎ ወደ አሜሪካ የመጣበትን ሂደት ሳየው ምነው ያኔ ምን ልታዘዝ ድራማ ቢኖርና የሀብታሙን ሴራዊ ድራማ ከማይ እነ ጋሼ አያልቅበትን ባይ ነው የሚያስብለው፡፡ እስር ቤት ውስጥ የምርም ታስረው የነበሩትን ሲወጡ ምን እንደሚመስሉ አይተናል፡፡ በነገራችን ላይ ዘረኛው በቀለ ገርባም ድራማ ከሚሠሩት አንዱ እንደሆነ ክፉኛ እየመረመርኩት ነው፡፡ ኦሮሞ ኦሮሞ እያለ የኦሮሞን ሕዝብ ከሌላው ሕዝብ ጋር አብሮ እንዳይኖር ለማድረግ ጠቀም ያለ ጉርሻ የተሰጠው ይመስላል፡፡ አሁን ይሄን ብናገር ማን ያምናል፡፡ ግን ቆይተን ሁሉም ማመን ቢከብደውም ይሰማታል፡፡ ከኦሮሞ ብዙዎች ናቸው፡፡ ሕዝቤ ሆይ አባክህ ሰዎች የሚናገሩትን አስተውል፡፡ ማንም እንዳያስታችሁ ተጠንቀቁ የተባለው ለሥጋዊ ኑሮህም ይጠቅማል፡፡ነገሮችን ቀለል አድርጌ መጠቆሜ ነው፡፡
በኤርሚየስና ሌሎች ላይ ጠንከር ያሉትን እይታዎቼን ሳተናው አላወጣቸውም፡፡ የሚከተሉትን ግን ከዚህ በፊት በመሀል ጠቆም ያደረኩባቸው ናቸው
ቅዱስ እግዚአብሔር ማስተዋሉን ይስጠን! አገራችንንና ሕዝቧን ከክፉ ይጠብቅልን! አሜን!
ሰርፀ ደስታ
