አቶ በቀለ ገርባ በዋስ ከእስር እንዲወጡ ተወሰነ-BBC

አቶ በቀለ ገርባ በ30ሺ ብር ዋስትና ከእሰር እንዲወጡ መወሰኑን ጠበቃቸው ተናገሩ። አቶ በቀለ ገርባ በ30ሺ ብር ዋስትና ከእሰር እንዲለቀቁ የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት መወሰኑን የአቶ በቀለ ጠበቃ አብዱልጀባር ሁሴን ለቢቢሲ ተናግረዋል። አቶ አብዱልጀባር እንደተናገሩት ፍርድ ቤቱ ብይኑን የሰጠው ዛሬ ጠዋት ሲሆን፤ ”የአቶ በቀለ ገርባ ቤተሰቦች የተጠየቀውን ገንዘብ ሲፒኦ እያሰሩ ነው። የተለየ ነገር ከልተፈጠረ በቀር አቶ […]

የቀይ ሽብር ተከሳሹ ሄግ ፍርድ ቤት ቀረበ

የቀድሞው የኢትዮጵያ ወታደራዊ መሪ ረዳት ነበር የተባለው ግለሰብ የጦር ወንጀል የፍርድ ሂደት በኔዘርላንድስ ሄግ መታየት ጀመረ። የ63 ዓመት ዕድሜ ያለው አቶ እሸቱ አለሙ የተባለው ግለሰብ ወታደራዊው መንግሥት ስልጣን ላይ ከወጣ በኋላ ተቀናቃኞቹን ለመምታት ባካሄደው ‘የቀይ ሽብር‘ ዘመቻ ወቅት 75 ሰዎች እነዲገደሉ ትዕዛዝ ሰጥቷል ተብሎ ነው የተከሰሰው። የቀድሞው ኮሚኒስት መሪ መንግሥቱ ኃይለማሪያም ረዳት ነበር የተባለው ይህ […]

በቤኒሻንጉል ጥቃትን በመፍራት ሰለባዎች ወደመኖሪያቸው መመለስን ፈርተዋል-BBC

ባለፈው ሐሙስ ጥቅምት 16 ቀን በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ካማሽ ዞን ሃሮ ዴዴሳ ቀበሌ የተቀሰቀሰውና ለሕይወት መጥፋት እንዲሁም ለንብረት መውደም ምክንያት የሆነው ግጭት ግላዊ ጠብ የጫረው ነው ቢባልም ቢቢሲ ያነጋገራቸው የጥቃቱ ሰለባዎች ግን ማንነታቸው ላይ ያነጣጠረ መሆኑን ይናገራሉ። በተለያዩ ጊዜያት ከምዕራብ ጎጃም ዞን ለስራ ወደአካባቢው አቅንተው ኑሯቸውን በመሰረቱ የአማራ ተወላጆች እና በጉሙዝ ብሔረሰብ አባላት ውጥረቶች እና […]

ጠ/ሚ የኦሮሚያ – ሶማሌ ግጭት ምክንያቶችን ተናገሩ

Sunday, 29 October 2017 00:00 Written by  አለማየሁ አንበሴ የዶላር የኮንትሮባንድ ዝውውርን ለማሳለጥ የብሄር መልክ ያለው ግጭት ተቀስቅሷል 2 ሚ. ዶላር በህገ ወጥመንገድ ሲዘዋወር ተይዟል የክልሎቹ የመንግስት ሚዲያዎች ግጭቱን ለማቀጣጠል ሞክረዋል ፖሊስ ከፖለቲካ ወገንተኝነት ነፃ መሆን አለበት በመቶዎች ለሚቆጠር ህይወት መጥፋትና ለመቶ ሺዎች መፈናቀል ምክንያት የሆነው የኦሮሚያ ሶማሌ ግጭት መንስኤው የድንበር ጉዳይ አይደለም ያሉት ጠ/ሚኒስትር […]

ፕ/ር በየነ ጴጥሮስ በአገሪቱ ወቅታዊ ችግሮች ዙሪያ

Sunday, 29 October 2017 00:00 Written by  አለማየሁ አንበሴ በተፈጠረው ችግር የአቶ ኃይለማርያም መንግስት ሥልጣን መልቀቅ ነበረበት በየዞኑና በየወረዳው የሚፈጠረውን ግጭት የሚያነሳሱት ካድሬዎች ናቸው ህዝቡ የህግ ጥበቃ ያስፈልገዋል፤ አጥፊዎች በህግ መጠየቅ አለባቸው የኢትዮጵያ ህገ መንግስት ዶግማ አይደለም፤መከለስ ይችላል አስቸኳይ ጊዜ አዋጁ የተነሳው ሰላምና መረጋጋት ሰፍኗል በሚል ቢሆንም ግጭቱና አለመረጋጋቱ በየጊዜው እየተባባሰ ነው የመጣው። ለዚህ ምክንያቱ ምን ይመስልዎታል? […]

መንግስት፤ አቶ አባዱላ በሃላፊነታቸው እንዲቀጥሉ ይፈልጋል

Sunday, 29 October 2017 00:00 Written by  አለማየሁ አንበሴ የባለሥልጣናት በገዛ ፍቃድ ከሥራ መልቀቅ መለመድ አለበት ተባለ አቶ በረከት ስምኦን፤ የመልቀቂያ ጥያቄያቸው ተቀባይነት አግኝቷል። የመንግስት ባለሥልጣናት በገዛ ፍቃዳቸው ከስራ መልቀቃቸው ዲሞክራሲዊ በመሆኑ መለመድ አለበት ያሉት ጠ/ሚኒስትር ኃ/ማርያም ደሳለኝ፤ በቅርቡ የስራ መልቀቂያ ጥያቄ ያስገቡት የኢህአዴግ ከፍተኛ አመራር አቶ በረከት ስምኦን፣ ጥያቄያቸው ተቀባይነት ማግኘቱን ጠቁመው፣ የአቶ አባዱላ […]

የኢሠማኮ ጠቅላይ ምክር ቤት እስከ ሥራ ማቆም አድማ የሚደርስ ዕርምጃ ለመውሰድ ወሰነ

29 October 2017 ዳዊት ታዬ የደመወዝ ማስተካከያ ያስፈልጋል ብሏል የኢትዮጵያ ሠራተኞች ማኅበራት ኮንፌዴሬሽን ጠቅላይ ምክር ቤት እንደ አዲስ ተረቅቆ የተዘጋጀውን የአሠሪና ሠራተኛ ረቂቅ አዋጅ ፈፅሞ እንደማይቀበለው፣ ረቂቁ እንዲሻሻል በተደጋጋሚ ያቀረበው ጥያቄ ምላሽ ካላገኘ የሠራተኛውን መብትና ጥቅም ለማስከበር በአገር አቀፍ ደረጃ እስከ ሥራ ማቆም አድማ የሚደርስ ዕርምጃ ለመውሰድ ውሳኔ አሳለፈ፡፡ የአሠማኮ ጠቅላይ ምክር ቤት ይህን ውሳኔ […]

ተመራማሪዎች በሞቃታማውና በአሲዳማው የአፋር ክፍል ህይወት ያለው ነገር አገኙ

12 ሴፕቴምበር 2017LBECK, MARTYN አካባቢው በተለያዩ ቀለማት ቢያሸበርቅም የቢጫና የአረንጓዴ ቀለማት ተጽእኖ አለው። አየሩም በመርዛማው ክሎሪን ሰልፈር ጋዝ ተሞልቷል። በኢትዮጵያ የሚገኘው ዳናክል ዲፕሬሽን ከዓለማችን ሞቃታማ እና ለኑሮ ምቹ ካልሆኑ አካባቢዎች አንደኛው ነው። ሆኖም በቅርቡ የተደረገ አንድ ጥናት በአካባቢው ህይወት ያላቸው ነገሮች እንደሚኖሩ አረጋግጧል። ዳናክል ዲፕሬሽን አነስተኛ ጥናት ከተካሄደባቸው የዓለም አካባቢዎች አንዱ ነው። ከኤርትራ ድንበር በቅርብ […]

እስር ቤት ውስጥ በደል እየተፈፀመባቸው መሆኑን የዋልድባ መነኮሳት ተናገሩ

October 26, 2017 –  ቆንጅት ስጦታው  እስር ቤት ውስጥ በደል እየተፈፀመባቸው መሆኑን የዋልድባ መነኮሳት ተናገሩ “ማዕከላዊ ብዙ በደል ደርሶብናል። በአካልም በስነ ልቦናም ብዙ በደል እየደረሰብን ነው።” አባ ገ/ እየሱስ ኪ/ ማርያም ” ከ2004 ጀምሮ እየተሰቃየን ነው። ገዳም እንዳንቀመጥ እየተደበደብን ነው” አባ ገ/ ስላሴ ወ/ሀይማኖት (በጌታቸው ሺፈራው) የ”ሽብር” ክስ ቀርቦባቸው ቂሊንጦ የሚገኙት የዋልድባ መነኮሳት እስር ቤት ውስጥ […]

ከደህንነት ቢሮ የወጣ ምስጢራዊ መረጃ – ሕብር ሬድዮ

October 26, 2017 በኢሉባቦር የደረሰው እልቂት በባሌ፣ በአሶሳ እና በወለጋ እንዲዛመት እቅድ መውጣቱን ከደህንነት ቢሮ የወጣ ምስጢራዊ መረጃ ይጠቁማል። በምዕራብ ኢትዮጵያ እየተነሱ ያሉ ተቃውሞዎችን ለመቀልበስ የኦሮሞ እና የአማራ ተወላጆችን ማገዳደል በብሄራዊ የደህንነት ቢሮ እንደ ዋነኛ እቅድ እና ስትራቴጂ መነደፉን መረጃው ያጋልጣል። ከደህንነት ምንጮች አሁን የደረሰን መረጃ