የመገናኛ ብዙኃንን ባለሥልጣን ሕግ የሚጥሱ የሚዲያ ተቋማትን በማባበል አልቀጥልም አለ
23 May 2021 ሲሳይ ሳህሉ የመንግሥት ተቋማት በሮቻቸውን ለጋዜጠኞች ክፍት እንዲያደርጉ አሳሰበ የመገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ሕጉን ጠብቀው የማይሠሩ የሚዲያ ተቋማትን በማባበል እንደማይቀጥል አስታወቀ፡፡ ባለሥልጣኑ ጥፋት በሚፈጽሙ የሚዲያ ተቋማት ላይ በመረጃ የተደገፈ ዕርምጃ እንደሚወሰድ በመግለጽ፣ ሕጋዊነት ላይ የሚኖር የድርድር ሒደት አይኖርም ሲሉ ዋና ዳይሬክተሩ አቶ መሐመድ ኢድሪስ ተናግረዋል፡፡ በመሆኑም የወጣውን ሕግ ለማስከበር ባለሥልጣኑ ‹‹ቆፍጣና›› ሆኖ ለመሥራት ዝግጁ ነው ብለዋል። ከዚህ በፊት የነበረው እንቅስቃሴ ልስላሴው የበዛ፣ ጥሰቶችና ግድፈቶች ሲያጋጥሙ ባለሥልጣኑ የሚሰጣቸውን የዕርምት ማስጠንቀቂያዎች ወይም ግብረ መልስ እንደ ግብዓት ከመውሰድ ይልቅ፣ ውድቅ በማድረግ ባለሥልጣኑ መሳለቂያ የመሆን ደረጃ የደረሰቡት ሁኔታ እንደነበረ በመግለጽ፣ የሚዲያ ተቋማት ይህን ያህል ሲወርዱ ዝም ብሎ ማየት የባለሥልጣኑ ችግር እንደነበር ጠቁመዋል። አቶ መሐመድ አክለውም መንግሥት ሚዲያውን ለማገዝ ያለውን ቁርጠኝነት በመገናኛ ብዙኃን ፖሊሲ ገልጿል ብለዋል፡፡ በተመሳሳይየመንግሥት ተቋማትና አመራሮቻቸው በሮቻቸውን ለሚዲያ ተቋማት ክፍት በማድረግ ለሕዝብ መድረስ ያለበት መረጃ እንዲደርስ፣ ጋዜጠኞች ሊታገዙ እንደሚገባ አቶ መሐመድ አሳስበዋል፡፡ የመረጃ አሰጣጡ ተቋማት የፈለጉትን ጉዳይ ብቻ አዘጋጅተው መግለጫ በመስጠት እንዲዘገብ መፈለግ መሆን እንደሌለበት ጠቁመዋል፡፡ የባለሥልጣኑን የዘጠኝ ወራት አፈጻጸም ሪፖርት ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሕግ፣ ፍትሕና ዴሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ግንቦት 11 ቀን 2013 ዓ.ም. አቅርበዋል፡፡ የመንግሥት ተቋማት ሚዲያዎች በሙሉ ሁነት ላይ እንዲዘግቡ የሚያደርግ አካሄድ ስለሌላቸው፣ ከዚህ በተሻለ መንግሥት ለሕዝቡ የገባው ቃል ምን ደረሰ ብለው ቃለ መጠይቅ ለማድረግ ለሚሄዱ ሚዲያዎች የተዘጉ በሮች መከፈት እንዳለባቸው አሳስበዋል፡፡ የተሳሳተ መረጃን ማቆም የሚቻለው የመንግሥት አካላት ስለፈጸሙትና እየፈጸሙት ስላለው ሥራ፣ ሚዲያ ሲጠይቃቸው መልስ መስጠት ሲችሉ እንደሆነም ጠቁመዋል። ‹‹ይሁን እንጂ ሚዲያው በዘገባው በአገራዊ ጉዳዮች የማይደራደር መሆን አለበት። ሰላም ብሔራዊ ጥቅማችን ነው፤›› ብለዋል። በተመሳሳይ ዜና ከዚህ በፊት ያልነበረውና በአዲሱ የመገናኛ ብዙኃን አዋጅ መሠረት ሕጋዊ ሆነው እንዲመዘገቡና ፈቃድ እንዲያወጡ የተደነገገባቸው የበይነ […]
‘ጥቁር ፈንገስ’፡ በሕንድ 9 ሺህ ገደማ ሰዎች በሚዩኮማይኮስስ በሽታ መያዛቸው ተረጋገጠ
ሕንድ ገዳይ በሆነው እና እየተስፋፋ ባለው የ‘ጥቁር ፈንገስ‘ በሽታ የተያዙ ከ8 ሺህ 800 በላይ ሰዎች መዘገበች። እምብዛም ያልተለመደውና ሚዩኮማይኮስስ የተባለው ይህ በሽታ 50 በመቶ ገዳይ ሲሆን አንዳንዶችን ደግሞ የዓይን ብርሃናቸውን ያሳጣል። ከቅርብ ወራት ወዲህ ሕንድ ከኮቪድ-19 ያገገሙ እና እያገገሙ ያሉ ህሙማንን የሚያጠቃውን በሽታ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ላይ አግኝታለች። ሐኪሞች እንደሚሉት በሽታው ኮቪድን ለማከም ከሚጠቀሙት ስቴሮይድ […]
የፖለቲካ አመራሮች፣ የሃይማኖት አባቶችና የአገር ሽማግሌዎች በአገራቸው ጉዳይ ላይ እንዲመክሩ ጥሪ ቀረበ
Saturday, 22 May 2021 11:58 መታሰቢያ ካሳዬ • “ሚዲያን አስወጥታችሁ በር ዘግታቸሁ ምከሩ” ሰላም ሚኒስቴር የፖለቲካ አመራሮች፣ የሃይማኖት አባቶችና የአገር ሽማግሌዎች በአገራቸው ጉዳይ ላይ በጋራ እንዲመክሩና አገሪቱ ካለችበት እጅግ ፈታኝ አጣብቂኝ ውስጥ ልትወጣ የምትችልበትን መንገድ በመፈለጉ ጉዳይ ላይ የበኩላቸውን አስተዋፅኦ እንዲያደርጉ ጥሪ ቀረበ፡፡ የመገናኛ ብዙኃንም በዚህ ወሳኝ ወቅት ላይ ተዓማኒነት ያለው መረጃ በማቅረብ ግጭቶችን ማርገብ […]
የአሜሪካ ሴኔት የውሳኔ ሃሳብና የኢትዮጵያውያን ተቃውሞ
መታሰቢያ ካሳዬ Saturday, 22 May 2021 12:20 • የሴኔቱ ውሳኔ አሜሪካ በተደጋጋሚ ስትናገረው ከነበረው ጉዳይ ውጪ ምንም አዲስ ነገር የለውም። • ውሳኔው ህውኃትን ወደ ስልጣን ለመመለስ የሚደረግ ጥረት አካል ነው። • ትናንትና ለኤምባሲዎች የተቃውሞ ደብዳቤ ለማስገባት ተይዞ የነበረው ፕሮግራም ተሰርዟል። የአሜሪካ ሴኔት በኢትዮጵያ ትግራይ ክልል ውስጥ እየተካሄደ ነው ያለውን ግጭት አስመልክቶ ከትናንት በስቲያ ባካሄደው ዝግ […]
የቱ ነዉ አማራ? መለኪያዉስ ደም ነዉ ወይስ አስተሳሰብ?
የቱ ነዉ አማራ? መለኪያዉስ ደም ነዉ ወይስ አስተሳሰብ? —- ሸንቁጥ አየለ ————– 1.ታዲዮስ ታንቱ —- “አማራን በሀሰት መክሰስ ነዉር ነዉ። የአማራን ዘር ከኢትዮጵያ ለማጥፋት የሚሰራዉን ስራ ሁሉ እቃወማለሁ። የአማራ ህዝብ ለኢትዮጵያ ባለዉለታ እንጂ ሀሰተኞች እንደሚሉት የሌሎችን ባህል አላጠፋም። የሌሎችንም ቋንቋ አልተጋፋም። ከዚያ ይልቅ ፊደል አስተምሯል። ሀገር ጠብቋል።ስነጽሁፍ አሳዉቋል። ብዙዉን ከአረመኔነት ወደ መንፈሳዊ ሰዉነት መልሷል። አሁን […]
ዘረኛ አምባገነን መንግሥትና እብድ ውሻ አንድም ሁለትም ናቸው
ሚያዝያ 28 ቀን 2013 ዓም(06-05-2021) እብድ ውሻ በዬሄደበትና በዬደረሰበት ልሃጩን እያዝረከረከ የማይበክልው፣የማይነክሰው እንስሳም ሆነ ሰው የለም።በሽታው ባሳደረበት የአይምሮ መዛባትና ፍርሃት የተነሳ ከፊቱ የቆመውን ሁሉ ይነጅሳል፣ይለክፋል፣ በመጨረሻውም እንደተቅበዘበዘ ይሞታል። በተመሳሳይ ደረጃም በአንድ አገር የሚነሳ ዘረኛና ጸረ ሕዝብ የሆነ አምባገነናዊ መንግሥት ገና ከጅምሩ የብዙሃኑን ፍላጎት ይዞ ስለማይነሳ የተቃውሞ ጎራ አብሮት ይወለዳል።ዕድሜው እየጨመረ ሲሄድም የተቃዋሚው መጠንና ተቃውሞው ይጨምራል፤የዃላዃላም […]
የማይታወቀው የተባበሩት መንግሥታት ዲፕሎማት እና ሌሎች ትግራይን የተመለከቱ ሐሰተኛ ዘገባዎች

በትግራይ ክልል ያለው ውጥረት አሁንም አልረገበም። የሰብዓዊ መብት ጥሰት ክሶች እየተዘገቡ ነው። አለመረጋጋቱ ሊቀጥል እንደሚችልም ስጋት አለ። የፕሮፓጋንዳ ጦርነት በማኅበራዊ ድር አምባዎች እየተካሄደ ነው፡፡ ሁለቱም ወገኖች ሐሰተኛ እና አሳሳች መረጃዎችን በማሰራጨት ተጠምደዋል። ከግጭቱ ጋር ተያይዞ በፌስቡክ እየተዘዋወሩ ያሉ የተጭበረበሩ ምሥሎች ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ ለምን መከላከያውን ወደ ትግራይ አዘመቱ? የአክሱም ‘ቄስ’ የተባለው ግለሰብና የፈጠረው ውዝግብ […]
ወቅታዊውን የሱዳን መሬት ወረራ በተመለከተ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ በፓርላማ የተናገሩት

ሱዳንን በሚመለከት በዲፕሎማስው ሰፊ ስራ እየሰራን ነው፡፡ ከሱዳን ጋር ጦርነት መጀመር አያስፈልግም ኪሳራ ነው ፤ ሱዳንም አሁን ባለው ሁኔታ ከጎረቤት አገር ጋር ለመዋጋት በሚያስችል ቁመና ላይ አይደለም ያለችው ፡፡ብዙ የውስጥ ችግር አለባት፤ ኢትዮጵያም አሁን ባለው ሁኔታ ከሱዳን ጋር ለመዋጋት ብዙ ችግር አለባት፤ ስለዚህ ጦርነቱ ለሁለታችንም አያስፈልገንም፤ ችግሩን በንግግር፣ በውይይት፣ በድርድር መፍታት ነው የሚያስፈልገው፤ ያ ተጀምሯል፤ […]
በሰሜን ሸዋና ኦሮሞ ብሔረሰብ ዞኖች የተከሰተው የፀጥታ ችግር አንጻራዊ ሰላም መፈጠሩን የክልሉ ሰላምና ደህንነት ቢሮ አስታወቀ፡፡

በአማራ ክልል በሰሜን ሸዋ እና ኦሮሞ ብሔረሰብ ዞኖች የተከሰተው የፀጥታ ችግር አንጻራዊ ሰላም መፈጠሩን የክልሉ ሰላምና ደህንነት ቢሮ አስታወቀ፡፡ የአማራ ክልል ሰላምና ደህንነት ቢሮ ሃላፊ አቶ ሲሳይ ዳምጤ በክልሉ የተከሰተውን የፀጥታ ችግር አስመልክቶ ዛሬ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡ የፀጥታ ችግሩ የተከሰተው መጋቢት 1ዐ/2ዐ13 ዓ.ም በአንድ ሰላማዊ ነዋሪ ላይ በተፈፀመ ጥቃት ነው ያሉት ኃላፊው በዋናነት ጉዳዩ ታቅዶበት […]
የግጭቱ መነሻ “ጽንፈኝነት እና የፖለቲካ አሻጥር ነው”- የኦሮሚያ ብልጽግና

የገዢው ፓርቲ አንድ አካል የሆነው የኦሮሚያ ብልጽግና ፓርቲ በአማራ ክልል በኦሮሞ ብሔረሰብ ዞን የተከሰተው ግጭት መነሻው “ጽንፈኝነት እና የፖለቲካ አሻጥር ነው” አለ። የኦሮሚያ ብልጽግና ፓርቲ ሰኞ ማታ ባወጣው መግለጫ በአካባቢው ከአርብ ጀምሮ በተቀሰቀሰው ግጭት በንፁሃን ዜጎች ሕይወትና ንብረት ላይ ከባድ ጉዳት ደርሷል ሲል አስታውቋል። የአማራ ክልል መስተዳደር ክስተቱን አስመልክቶ ቅዳሜ እለት ባወጣው መግለጫ በጥቃቱ የሰዎች […]