ሄዝቦላህ በሊባኖስ 9 ሰዎች ለሞቱበት እና 3 ሺህ የሚደርሱ ለቆሰሉበት ፍንዳታ እስራኤልን ተጠያቂ አደረገ

ከ 4 ሰአት በፊት በሊባኖስ የሚገኙ የሄዝቦላህ አባላት መረጃ ለመለዋወጥ የሚጠቀሙባቸው በእጅ የሚያዙ ‘ፔጄሮች’ ፈንድተው አንድ ሕፃንን ጨምሮ ዘጠኝ ሰዎች ሲሞቱ ወደ ሦስት ሺህ የሚጠጉ ሰዎች መቁሰላቸውን የአገሪቱ የጤና ጥበቃ ሚኒስትር አስታወቀ። በቤይሩት እና በሌሎች በርካታ ክልሎች በተመሳሳይ ሰዓት በደረሰው ፍንዳታ ከቆሰሉት ከ2 800 በላይ ሰዎች መካከል በሊባኖስ የኢራን አምባሳደር ይገኙበታል። ፔጀር አነስተኛ ገመድ አልባ […]

በ17 የአሜሪካ ግዛቶች ለሚገኙ የምርጫ አስፈጻሚዎች ምንነቱ ያልታወቀ እሽግ በፖስታ ተላከ

ከ 4 ሰአት በፊት ከሳምንታት በኋላ የሚደረገውን ምርጫ ለሚያስተባብሩ በ17 የአሜሪካ ግዛቶች ለሚገኙ የምርጫ ኃላፊዎች የተላከ እሽግ ፖስታ ላይ ምርመራ እያደረጉ እንደሚገኙ ኤፍቢአይ እና የአሜሪካ ፖስታ አገልግሎት ገለጹ። የአሜሪካ ፌዴራል ምርመራ ቢሮ ባልደረቦች እሽጎችን ከተቀባዮቹ መሰብሰባቸውን የገለጹ ሲሆን፣ አንዳንዶቹ ምንነቱ ያልታወቀ ነገር እንደተገኘባቸው አመልክተዋል። ሆኖም ግን በእሽጎቹ ምክንያት የደረሰ ጉዳት የለም ተብሏል። እሽጎቹ ከኒው ዮርክ […]

ሴቶችን ለወሲብ ንግድ በማዘዋወር ተጠርጥሮ በቁጥጥር ሥር የዋለው አሜሪካዊው ራፐር ዲዲ ዋስትና ተከለከለ

ከ 4 ሰአት በፊት ሴቶችን ለወሲብ ንግድ በማዘዋወር የተጠረጠረው ታዋቂው አሜሪካዊ ራፐር በቁጥጥር ሥር ከዋለ በኋላ በዋስትና እንዲለቀቅ የቀረበው ጥያቄ ውድቅ ሆነ። በኒው ዮርክ የሚገኘው ፍርድ ቤት የፌዴራል ዳኛ፤ ሙዚቀኛው ከሀገር ሊጠፋ ስለሚችል በቁጥጥር ሥር እንዲቆይ አቃቤ ሕግ ያቀረበውን ጥያቄ ተቀብለው ዋስትና ከልክለዋል። የ54 ዓመቱ ዲዲ ሰኞ አመሻሹን ነው በቁጥጥር ሥር የዋለው። ራፐሩ ከአውሮፓውያኑ 2008 […]