ትራምፕ የካማላ ሀሪስና ሂላሪ ክሊንተንን ምሥጢራዊ መረጃ የመመልከት ፈቃድ አነሱ

23 መጋቢት 2025, 08:46 EAT የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የቀድሞዋ ምክትል ፕሬዝዳንት ካማላ ሀሪስ የነበራቸውን ምሥጢራዊ መረጃ የመመልከት ፈቃድ አነሱ። ባለሥልጣኖች የአገሪቱን ምሥጢራዊ መረጃ መመልከት የሚችሉበትን ፈቃድ የተነጠቁት የትራምፕ ተቀናቃኝ የነበሩት ካማላ ሀሪስ ብቻ ሳይሆን ሂላሪ ክሊንተንም ጭምር ናቸው። ትራምፕ የቀድሞ ባለሥልጣኖችና ተቺዎቻቸውን ፈቃድ አንስተዋል። የቀድሞው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደንን እንዲሁም የቤተሰቦቻቸውን ፈቃድ እንደሚያነሱም ሲናገሩ ነበር። […]

የትራምፕ ልዑክ እንግሊዝ ከተኩስ አቁም በኋላ ለዩክሬን ዓለም አቀፍ ድጋፍ ያስፈልጋል ማለቷን አወገዙ

23 መጋቢት 2025, 09:21 EAT የዩናይትድ ኪንግደም ጠቅላይ ሚኒስትር በዩክሬን የተኩስ አቁም ስምምነት ዓለም አቀፍ ኃይል ተሳታፊ እንዲሆን ማለታቸውን የትራምፕ ልዑክ አወገዙ። ስቲቭ ዊትኮፍ እንዳሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ሰር ኪር ስታርመር ያመነጩት ሐሳብ “ቀላል መንገድ የተከተለ” እና አውሮፓውያን “እንደ ዊንስተን ቸርችል መሆን አለብን” የሚል እሳቤ እንዳላቸው የሚያሳይ ነው ብለዋል። ዊትኮፍ የትራምፕ ደጋፊ ከሆነው ጋዜጠኛ ታከር ካርልሰን […]

በኢላን መስክ ምክንያት አእምሮውን የሚያነብ ቺፕ በአንጎሉ ያስቀበረው ሰው

23 መጋቢት 2025, 09:35 EAT ኖላንድ አርባግ አንጎሉ ውስጥ ቺፕ አስቀብሯል። አእምሮው የሚያስተላልፈውን ትዕዛዝ ወደ ኮምፒውተር የሚያሻግርለትም ይህ ቺፕ ነው። የ30 ዓመቱ ኖላንድ በአደጋ ሰውነቱ አልታዘዝ ካለው በኋላ ነበር ቺፕ ያስቀበረው። ቺፑን ካስቀበረ ስምንት ዓመት ሆኖታል። የኢላን መስክ ኒውራሊንክ ተቋም አንጎሉ ውስጥ ቺፕ የቀበረለት የመጀመሪያው ሰው ኖላንድ ነው። ቺፑ ሲቀበር የጎንዮሽ ጉዳቶች ሊኖሩ እንደሚችሉ ጠብቆ […]