በአማራጭነት ከቀረበው የጂቡቲው ታጁራ ወደብ ጋር ተያይዞ የሚነሱ ጥያቄዎች

ከ 5 ሰአት በፊት ኢትዮጵያ ራሷን በነጻ አገርነት ካወጀችው ሶማሊላንድ ጋር በፈረመችው የባህር በር መግባቢያ ስምምነት የተነሳ ከሶማሊያ ጋር የተፈጠረውን ውጥረት ለማርገብ እንዲሁም የኢትዮጵያን የባህር በር መዳረሻ ችግር ለመቅረፍ በሚል ጂቡቲ አማራጭ ያለችውን ሀሳብ ያቀረበችው ባለፉት ሳምንታት ነበር። የጂቡቲው ውጪ ጉዳይ ሚኒስትር፣ ማህሙድ አሊ ዩሱፍ፣ ቢቢሲ ፎከስ ኦን አፍሪካ ላይ በቀረቡበት ወቅት፣ የታጁራ ወደብን ኢትዮጵያ […]

ዶ/ር አሸብርን ጨምሮ የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቲ አመራሮች በሕገ ወጥ የሰዎች ዝውውር ክስ ተመሰረተባቸው

ከ 2 ሰአት በፊት የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቲ ፕሬዝዳንት [ዶ/ር] አሸብር ወልደጊዮርጊስን ጨምሮ አራት አመራሮች በሕገ ወጥ የሰዎች ዝውውር እና ሌሎች ተያያዝ ጉዳዮች ክስ ተመሰረተባቸው። የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቲም ከተከሳሾቹ መካከል ነው። ክሱን የመሰረቱት ሻለቃ አትሌት ኃይሌ ገብረሥላሴ፣ አትሌት ገዛኸኝ አበራ፣ የኢትዮጵያ ቦክስ ፌዴሬሽን እና የኢትዮጵያ ቴኒስ ፌዴሬሽን ናቸው። በፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ችሎት […]

የአሜሪካ ምርጫ ትንበያ፡ ማን እየመራ ነው – ትራምፕ ወይስ ሃሪስ?

ከ 2 ሰአት በፊት ጥቅምት 25/2017 ዓ.ም አሜሪካውያን ቀጣዩን ፕሬዝደንት ለመምረጥ ወደ ድመጽ መስጫ ጣቢያዎች ያመራሉ። ይህ ምርጫ ከአራት ዓመት በፊት ከተካሄደው እና ጆ ባይደን ከሸነፉበት ምርጫ ጋር ይመሳሰላል ተብሎ ተጠብቆ ነበር። ሆኖም ባለፈው ሀምሌ ፕሬዝዳንት ባይደን ከፉክክሩ እራሳቸውን እንዳገለሉና በምትኩ ምክትላቸውን ካማላ ሀሪስ እንዲወዳደሩ ይሁንታ ከሰጡ በኋላ የዘንደሮ ምርጫ የተለየ መልክ እንደሚኖረው ተገምቷል። ትልቁ […]

አጼ ኃይለሥላሴ በእንግሊዟ ባዝ ከተማ እንዴት በስደት ሊኖሩ ቻሉ?

ከ 5 ሰአት በፊት በበርካቶች ዘንድ “የአፍሪካ አባት” በመባል የሚታወቁት አጼ ኃይለሥላሴ በወታደሮች መፈንቅለ መንግሥት ከተደረገባቸው እነሆ 50 ዓመት ሞላው። መስከረም 2፤ 1967 ዓ.ም. ነበር የደርግ አባላት የሆኑት ወታደሮች፣ ኢትዮጵያን ለ44 ዓመታት የገዟትን ንጉሥ “. . . ለአገር እና ለሕዝብ ደህንነት ሲባል በዛሬው ዕለት ግርማዊ ቀዳማዊ አጼ ኃይለሥላሴ ከስልጣን ወርደዋል” በማለት የአገዛዛቸው ዘመን ማብቃቱን የነገሯቸው። […]

አዲሱ የቦይንግ ሥራ አስኪያጅ ሠራተኞቻቸው አድማ እንዳይመቱ ተማፀኑ

ከ 4 ሰአት በፊት አዲሱ የቦይንግ ሥራ አስኪያጅ ኬሊ ኦርትበርግ የድርጅቱን ማገገም ስጋት አደጋ ላይ ሊጥል ይችላል በሚል የድርጅቱ ሠራተኞች አድማ እንዳይመቱ ተማፀኑ። የሠራተኞች ማኅበር አድማ መምታትን በተመለከተ የድምፅ አሰጣጥ ለማድረግ ሰዓታት ሲቀሩት ነው ሥራ አስኪያጁ ተማፅኖ ያሰሙት። የግዙፉ የአቪየሽን ኩባንያ ኃላፊዎች እና የሠራተኞች ማኅበር ተወካዮች በያዝነው ሳምንት በደረሱት ስምምነት መሠረት ቦይንግ በሚቀጥሉት አራት ዓመታት […]