በሲድኒ በስለት የተወጉት የኦርቶዶክስ ጳጳስ ጥቃት አድራሹን “ይቅር ብያለሁ” አሉ
ከ 4 ሰአት በፊት ባለፈው ሰኞ በአውስትራሊያ ሲድኒ ከተማ በቀጥታ በሚተላለፍ ሰብከት ላይ ሳሉ በስለት ጥቃት የደረሰባቸው አቡነ ማር ማሪ ኢማኑኤል በፍጥነት እያገገሙ እንደሆነ ገልጸው፣ ጥቃቱን እንዳደረሰ ለተጠረጠረው ግለሰብም ይቅርታ እንዳደረጉ ተናግረዋል። ጳጳሱ በተቀረጸ ድምጽ ባስተላለፉት መልዕክት ኅብረተሰቡ እንዲረጋጋም ጥሪ አቅርበዋል። በዚህ ሳምንት መግቢያ ላይ በተፈጸመው ጥቃት አራት ሰዎች ተጎድተዋል። ፖሊስ ጥቃቱ ሃይማኖታዊ መነሻ ያለው […]
ኢራን እና እስራኤል ለምን ደመኛ ጠላቶች ሆኑ?
ከ 5 ሰአት በፊት ወትሮም በጠላትነት የሚተያዩት እስራኤል እና ኢራን ባለፉት ሳምንታት ወደ ለየለት ፍጥጫ በመግባታቸው በመካከለኛው ምሥራቅ ያለው ውጥረት አይሏል። እስራኤል በሶሪያ መዲና ደማስቆ የሚገኘውን የኢራን ቆንስላን ጽህፈት ቤት በቦምብ ማጋየቷ ነው ሁለቱ አገራት ወደ ቀጥተኛ ጥቃት እና ፍጥጫ እንዲገቡ ያደረጋቸው። ባለፍነው ቅዳሜ ሌሊት ኢራን በመቶዎች የሚቆጠሩ ሚሳኤሎችን እና ድሮኖችን ወደ እስራኤል ማስወንጨፏ ቀጠናውን […]
የዱባይ አየር ማረፊያ በጎርፍ መጥለቅለቁን ተከትሎ በመቶዎች የሚቆጠሩ በረራዎች ተሰረዙ
ከ 1 ሰአት በፊት የባህረ ሰላጤው አገራት አውሎ ንፋስ በቀላቀለ ከባድ ዝናብ መመታታቸውን ተከትሎ በዓለማችን ሁለተኛ የሆነው የዱባይ አየር ማረፊያ በጎርፍ ተጥለቀለቀ። በዚህም የተነሳ በመቶዎች የሚቆጠሩ በረራዎች ሲሰረዙ፣በርካታዎችም ተስተጓጉለዋል። የዱባይ አለም አቀፍ አየር ማረፊያ “በጣም ፈታኝ ሁኔታዎች” እንደገጠመው አስጠንቅቆ መንገደኞች በጎርፍ የተጥለቀለቁ አካባቢዎችን እንዲያስወግዱም መክሯል። አንድ ግለሰብ መኪናው በጎርፍ በመወሰዱ ህይወቱ ማለፉ ተገልጿል። በኦማን ሳሃም […]
ስዊድን ፆታን በሕጋዊ መንገድ የመቀየሪያን እድሜን ከ18 ወደ 16 ዝቅ አደረገች
ከ 4 ሰአት በፊት የስዊድን ፓርላማ ፆታን በሕጋዊ መንገድ የመቀየሪያን እድሜ ከ18 ወደ 16 ዝቅ በማድረግ ሂደቱን የሚያቀል ህግ አጸደቀ። ህጉ በ234 የድጋፍ ድምጽ እና በ94 ተቃውሞ ነው የጸደቀው። ምንም እንኳን ስዊድን ጾታ መቀየርን በአውሮፓውያኑ 1972 ህጋዊ ለማድረግ የመጀመሪያዋ ሃገር ብትሆንም አዲሱ ህግ ከበድ ያለ ክርክር ማስነሳቱ አልቀረም። አንዳንዶች ህጉ ጠቃሚ ለውጥ እንደሚያመጣ አስተያያታቸውን ቢሰጡም […]
ኳታር በእስራኤል እና ሐማስ በሚደረገው ድርድር የአሸማጋይነት ሚናዬን እያጤንኩ ነው አለች
ከ 3 ሰአት በፊት ኳታር በእስራኤል እና በሐማስ መካከል የሚደረገውን የተኩስ አቁም ድርድር የአሸማጋይነት ሚናዋን እንደገና እያጤነችው ነው ሲሉ የአገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ተናገሩ። አገሪቱ በጋዛ የተኩስ አቁም እንዲኖር እና የእስራኤል ታጋቾችን ለማስፈታት ከግብጽ እና ከአሜሪካ ጋር በመሆን ቁልፍ ሚና ተጫውታለች። ጠቅላይ ሚንስትሩ ሼክ መሐመድ ቢን አብዱልራህማን አል-ታኒ የፖለቲካ ነጥብ ለማስቆጠር በሚሞክሩ ሰዎች ምክንያት ዶሃ “እየተበዘበዘች […]
ከአላማጣ እና ከሌሎች የራያ አካባቢዎች የተፈናቀሉ ነዋሪዎች፤ በቆቦ ኢንዱስትሪ መንደር እንዲጠለሉ መደረጋቸው ተገለጸ – ኢትዮጵያ ኢንሳይደር
April 17, 2024 በአማራ እና የትግራይ ክልሎች “የወሰን ይገባኛል” ጥያቄዎች ከሚነሱባቸው አካባቢዎች አንዱ በሆነው የራያ አካባቢ ባለፉት ቀናት ውጊያ መካሄዱን ተከትሎ በሺህዎች የሚቆጠሩ ነዋሪዎች ከቀያቸው ተፈናቅለው ቆቦ ከተማ መግባታቸውን የአካባቢው ባለስልጣናት ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ተናገሩ። ተፈናቃዮቹ በአሁኑ ወቅት ከቆቦ ከተማ ወጣ ብሎ በሚገኝ የኢንዱስትሪ መንደር በጊዜያዊነት እንዲጠለሉ መደረጋቸውንም አስታውቀዋል። በአወዛጋቢዎቹ የራያ አካባቢዎች ውጊያ የተቀሰቀሰው፤ ከአካባቢው የተፈናቀሉ […]
በአዲስ አበባ ከተማ ተቋርጦ የነበረው የመታወቂያ መስጠት እና እድሳት አገልግሎት በቀጣዩ ሳምንት ዳግም ይጀመራል ተባለ – ኢትዮጵያ ኢንሳይደር
April 17, 2024 በናሆም አየለ በአዲስ አበባ ከተማ ከአንድ ሳምንት በላይ ተቋርጦ የቆየውን የመታወቂያ መስጠት እና እድሳት አገልግሎትን በሚቀጥለው ሳምንት ለመጀመር የጥገና ስራ እያከናወነ መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ ገለጸ። ኤጀንሲው ይሰጣቸው የነበሩ መደበኛ አገልግሎቶች የተቋረጡት፤ ከመረጃ ማከማቻ ቋቱ ጋር በተገናኙ “የቴሌኮም ኬብሎች” ላይ ጉዳት በመድረሱ መሆኑን ገልጿል። በአዲስ ከተማ […]
በዘመናዊ ዕውቀት መታገዝ የሚሻው የማዕድን አወጣጥ
ማኅበራዊ በዘመናዊ ዕውቀት መታገዝ የሚሻው የማዕድን አወጣጥ አበበ ፍቅር ቀን: April 17, 2024 በቴክኖሎጂው የተራቀቁ አገሮች በአፍሪካ ምድር ያሉ ከርካሽ የሰው ጉልበት እስከ የተፈጥሮ ሀብት ለመቀራመት ሲፈልጉ በድርድር ካልሆነ ደግሞ በብድር እጅና እግራቸውን በመጠፍነግ ያሻቸውን ጥሬ ሀብት እየዛቁ ለፋብሪካቸው ግብዓት ሲያጓጉዙ ኖረዋል። በተለይ ደግሞ አሁን ላይ እየደረሱበት ላለው የቴክኖሎጂ ፈጠራዎች ትልቁ ግብዓታቸው በአፍሪካ ውስጥ የሚገኙ […]
በግብርና ምርቶች ብክነት በዓመት ከ474 ቢሊዮን ብር በላይ እየታጣ መሆኑ ተነገረ
በናርዶስ ዮሴፍ April 17, 2024 በዓመት 46 ሚሊዮን ሕዝብ ሊመግብ የሚችል ምርት ይባክናል ተብሏል የግብርና ሚኒስቴር አዲስ ያስተዋወቀው የግብርና ምርቶች አስተዳደርና አመራር ስትራቴጂ፣ በኢትዮጵያ በየዓመቱ 474.67 ቢሊዮን ብር የሚያወጣ የምርቶች ብክነት መኖሩን አመላከተ፡፡ ሚኒስቴሩ ከዚህ ቀደም ብክነትን ለማስቀረት ሲሠራበት የቆየው ስትራቴጂ እህልና ጥራጥሬ ላይ ብቻ ትኩረት ያደረገ ሲሆን፣ አዲሱ ስትራቴጂ ተጨማሪ ሁለት ዘርፎችን አካቷል። ከተያዘው […]
የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ከለጋሾች የሚያገኙት ገንዘብ የታክስ ሥርዓቱን እንዲከተል መመርያ ተዘጋጀ
ዜና የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ከለጋሾች የሚያገኙት ገንዘብ የታክስ ሥርዓቱን እንዲከተል መመርያ ተዘጋጀ ሰላማዊት መንገሻ ቀን: April 17, 2024 የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ከለጋሾች የሚያገኙት ገንዘብ የታክስ ሥርዓቱን ካልተከተለ ምርመራ እንደሚደረግበት፣ በሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ባለሥልጣን መመርያ ተዘጋጀ፡፡ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች በተመዘገቡበት ዓላማ መሠረት ሥራቸውን ማከናወናቸውን ለመከታተል፣ ለመቆጣጠርና ምርመራ ለማድረግ የሚያስችል መመርያ ነው የተዘጋጀው፡፡ በመመርያው መሠረት ከለጋሾች የሚገኝ […]