ሶማሌላንድ ዕውቅና የምታገኝበትን ሥምምነት ከኢትዮጵያ ጋር በሁለት ወራት ገደማ ትፈራረማለች ተብሎ እንደሚጠበቅ የሶማሌላንድ ሚኒስትር ተናገሩ

April 30, 2024 – DW Amharic ለሶማሌላንድ እውቅና ለኢትዮጵያ የባሕር ኃይል የጦር ሠፈር በኪራይ የሚሰጠው ሥምምነት በሁለት ወራት ገደማ ይፈረማል ተብሎ እንደሚጠበቅ የሶማሌላንድ የውጭ ጉዳይ እና ዓለም አቀፍ ትብብር ሚኒስትር ኢሳ ካይድ ለዶይቼ ቬለ ተናግረዋል። ኢትዮጵያ ለባሕር ኃይል የጦር ሠፈር ልትከራይ የምትችላቸው ሦስት አማራጭ ቦታዎች መለየታቸውን ሚኒስትሩ ገልጸዋል።… … ሙሉውን ለማየት ወይም ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ

የጋዛን ጦርነት እየተቃወሙ ያሉት የኮሎምቢያ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ሕንጻ ተቆጣጠሩ

ከ 1 ሰአት በፊት በርካታ ፍልስጤምን የሚደግፉ የኮሎምቢያ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች በተቃውሟቸው ቀጥለው የአካዳሚክ ሕንጻውን መቆጣጠራቸው ተገለጸ። የጋዛን ጦርነት በመቃወም በኒው ዮርክ ዩኒቨርስቲ ተቃውሟቸውን እያሰሙ የሚገኙ ተማሪዎች ደግሞ ሀሚልተን የተባለውን ሕንጻ ተቆጣጥረዋል። በሌሎች ዩኒቨርስቲዎችም ተቃውሞዎችን ያቀጣጠለውን የተማሪዎች ተቃውሞ ለማስቆም የዩኒቨርስቲው አመራሮች ቢሞክሩም አልተሳካም። አንድ ተማሪ ዩኒቨርስቲው “ሕግ አልባ ሆኗል” ስትል ገልጻለች። ተማሪዎች እና ሠራተኞች ከዩኒቨርስቲው እንዲርቁ […]

የአብን አባሉ አቶ ጣሂር ሙሐመድ “በግል ምክንያት” ከአማራ ክልል የመንግሥት ኃላፊነት መልቀቃቸውን አስታወቁ

ከ 4 ሰአት በፊት ላለፈው ሁለት ዓመት ከስምንት ወር ገደማ የአማራ ክልል ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ ሆነው ሲሰሩ የነበሩት የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ አብን (አባሉ) አቶ ጣሂር ሙሐመድ “በግል ምክንያት” ከኃላፊነት መልቀቃቸውን ለቢቢሲ ተናገሩ። በአቶ ጣሂር ቦታ ሌላኛው የአብን አባል አቶ መልካሙ ፀጋዬ በክልሉ ርዕሰ መስተዳድር መሾማቸውን የአማራ ክልል ኮሚዩኒኬሽን አስታውቋል። ስድስተኛው አገር አቀፍ ምርጫን ያሸነፈው […]

በአሰቃቂ ሁኔታ የተገደሉት ፖለቲከኛው በቴ ኡርጌሳ ሲታወሱ

ከ 2 ሰአት በፊት በኦሮሞ ነጻነት ግንባር ውስጥ ‘የማይናወጥ ጽናት’፣ ‘በሀሳብ ውይይት ጀርባውን የማይሰጥ’፣ እና ‘የግንባሩ አዲስ ትውልድ ምልክት’ እየተባሉ የተወደሱት አቶ በቴ ኡርጌሳ ሚያዝያ 3/2016 ዓ.ም. በመቂ ከተማ በአሰቃቂ ሁኔታ ተገድለው ተገኝተዋል። አቶ በቴ እስከ ተገደሉበት ቀን ድረስ የኦሮሞ ነጻነት ግንባር የፖለቲካ ዘርፍን ይመሩ ነበር። ከዚያ ቀደም ብሎ በተደጋጋሚ በሽብርተኝነት ክስ ተደጋጋሚ እስራት እና […]

የቢቢሲ ጋዜጠኛ አሳዛኝ የጋዛ ገጠመኞች

ከ 9 ሰአት በፊት አድናን አል-ቡርሽ ይባላል። በጋዛ ድንኳን ቀልሶ ለቢቢሲ ይዘግባል። የሚላስ የሚቀመስ የለምና በቀን አንድ ጊዜ ይመገባል። የማይበላበትም ቀን አለ። ምግብ ጠፍቶ ሳይሆን በሌላ ምክንያት። ባለቤቱንና 5 ልጆቹን ከእስራኤል የአየር ላይ መቅሰፍት ለማዳን ቀን ተሌት ላይ ታች ይላል። ጋዜጠኛ አድናን በጋዛ በየዕለቱ ከሞት ጋር ይተናነቃል። ታሪኩን በራሱ አንደበት፦ ሞትና ሕይወት ባለፉት 6 ወራት […]

ሐማስ የእስራኤልን አዲስ የተኩስ አቁም ስምምነት እንደሚቀበል አሜሪካ ‘ተስፋ ሰንቃለች’

ከ 6 ሰአት በፊት እስራኤል ያቀረበችውን እና አሜሪካ “በጣም ለጋስ” ስትል የጠራችውን የጋዛ ተኩስ አቁም እና ታጋቾችን የመልቀቅ ስምምነት ሐማስ እንደሚቀበል የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ተስፋ ማድረጋቸውን ገለጹ። አንቶኒ ብሊንከን ይህንን የገለጹት የሐማስ ልዑካን ቡድን በአዲሱ ሃሳብ ላይ ከግብጽ እና ከኳታር አሸማጋዮች ጋር በሚወያይበት ወቅት ነው። ለውይይቱ ቅርብ የሆነ ምንጭ ለቢቢሲ እንደተናገሩት ተስፋ አላቸው። የቀረበው […]

በናይሮቢ አቅራቢያ 50 ሰዎች በጎርፍ ተወሰዱ

ከ 8 ሰአት በፊት በኬንያ መዲና ናይሮቢ አቅራቢያ በምትገኝ ስፍራ ነፋስ የቀላቀለ ከባድ ዝናብ ባስከተለው ጎርፍ 50 ሰዎች መወሰዳቸውን የቀይ መስቀል ባለስልጣን አስታወቁ። ከናይሮቢ በ60 ኪሎሜትር ርቀት ላይ በምትገኘው የማይማሂዩ መንደሮች ነዋሪዎችን ነው ጎርፍ ጠርጎ የወሰዳቸው። ነዋሪዎቱ ተኝተው እንደነበር የተገለጸ ሲሆን የሟቾች ቁጥር ሊጨምር እንደሚችልም ተፈርቷል። በጭቃ ውስጥ የተቀበሩ ነዋሪዎችን ለማውጣት የህይወት አድን ጥረቱ ቀጥሏል። […]

ከካንሰር ህመም ጋር እየታገለ ያለው ስደተኛ በአሜሪካ የ1.3 ቢሊዮን ዶላር ሎተሪ አሸናፊ ሆነ

ከ 5 ሰአት በፊት ከካንሰር ህመም ጋር እየታገለ ያለው የላኦስ ተወላጁ ስደተኛ በአሜሪካ 1.3 ቢሊዮን ዶላር የሎተሪ ጃክፖት አሸናፊ ሆነ። የ46 ዓመቱ ቼንግ ሳፋን ፓወርቦል በተሰኘው የሎተሪ ጃክፖት ጨዋታዎች እድለኛ መሆኑን የውድድሩ ባለስልጣናት ገልጸዋል። ቼንግ ዕድለኛ ያደረገውን የሎተሪ ቲኬት የገዛው በኦሪጎን ግዛት በፖርትላንድ ከተማ ከሶስት ሳምንት በፊት ነበር። ግለሰቡ አሸናፊ የሆነበትን ገንዘብ ግብር ተቀንሶ 422 […]