በአዲስ አበባ ከተማ እየተስፋፋ የመጣው የእገታ ወንጀል

March 29, 2024  በአዲስ አበባ ከተማ እየተስፋፋ የመጣው የእገታ ወንጀል  ( ኤሊያስ መሰረት ) ከሰሞኑ በስፋት እየደረሱኝ ያሉ መረጃዎች እንደሚጠቁሙት በፊት በፊት በክፍለ ሀገራት፣ ከዛም በአንዳንድ የአዲስ አበባ አቅራቢያ ስፍራዎች ሲከናወኑ የነበሩ የእገታ ወንጀሎች አሁን ላይ በአዲስ አበባ ከተማ መታየት ጀምረዋል። ከ10,000 ብር ጀምሮ እስከ 1 ሚልዮን ዶላር የተጠየቀባቸው ሰዎች እንዳሉ፣ እገታዎቹ በቀንም ይሁን በጭለማ […]

እስራኤል ለጋዛ ዕርዳታ እንዳይደርስ መከልከሏን እንድታቆም ዓለም አቀፉ ፍርድ ቤት አዘዘ

March 29, 2024 – DW Amharic  ደቡብ አፍርካ ውሳኔውን በጣም በማለት አፈጻጸሙን እንደምትከታተል ስታስታውቅ፤ የፍልስጤም አስተዳደር የውጭ ጉዳይ ቢሮ ደግሞ እርምጃው በአለማቀፍ ደረጃ ሊወሰዱ የሚገባቸውን እርምጃዎች የሚያመላክት ነው በማለት ደቡብ አፍርካን አመስግኗል።… … ሙሉውን ለማየት ወይም ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ

የአዲስ አበባን ማስተር ፕላን ያልተከተለው በአብይ አሕመድ ውሳኔ የሚሰራው የኮሪደር ልማቱ ከ1.5 ሚልየን በላይ ሰዎች ይጎዳሉ

March 29, 2024  የተጀመረው የኮሪደር ልማት በርካታ ጥንታዊና ታሪካዊ ህንጻዎች እንዲፈርሱ ምክንያት ሆኗል። ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ አንድ የምጣኔ ሀብት ባለሞያ ለአዲስ ማለዳ እንደገለጹት “በኮሪደር ልማቱ” 200 ሺህ ይሚሆኑ ነባር ይዞታዎችና ሱቆች እንደሚፈርሱ ግምታቸውን አስቀምጠው ከ1.5 ሚልየን በላይ ሰዎች በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ይጎዳሉ ብለዋል። አዲስ ማለዳ ያነጋገረቻቸው ፖለቲከኛዎች ደግሞ ብልጽግና ፓርቲ ምርጫ ለማሸነፍ የሚያስችለውን ሕዝብ ለማስፈርና […]

የሲቪክ ድርጅቶች ምክረ ሀሳብ – ለተመድ

March 29, 2024 – DW Amharic 25 ሀገር በቀል የሲቪል ማህበራት የተበበሩት መንግሥታት በየ አራት ዓመት ተኩል የሁሉንም አባል ሀገራት የሰብዓዊ መብት ሁኔታ ለመከታተል በሚያዘጋጀው ሁለንተናዊ ወቅታዊ ግምገማ መንግሥት ከሚያቀርበው ግምገማ በተጓዳኝ በ12 የተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ የራሳቸውን ትይዩ ዘገባ በጋራ አዘጋጅተው ዛሬ ውይይት አድርገውበታል… … ሙሉውን ለማየት ወይም ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ

እነ አቶ ክርስቲያን ታደለ “እንደ መደበኛ ታሳሪ እንዲታዩ” ፍርድ ቤት ትዕዛዝ አስተላለፈ

29 መጋቢት 2024, 18:17 EAT ከስምንት ወራት በኋላ ዛሬ ለመጀመሪያ ጊዜ ፍርድ ቤት የቀረቡት የሕዝብ ተወካዮች እንዲሁም የአማራ ክልል እና የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት አባላት “እንደመደበኛ ታሳሪ እንዲታዩ” ፍርድ ቤት ትዕዛዝ አስተላለፈ። ዐቃቤ ሕግ ተከሳሾቹ ወደ ማረሚያ ቤት እንዲወርዱ ያቀረበው ጥያቄ በፍርድ ቤቱ ውድቅ እንደተደረገም የተከሳሾቹ ጠበቃ ለቢቢሲ ተናግረዋል። የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሁለተኛ […]

ብሪታኒያ የአውሮፓ ዋንጫን የሚታደሙ ዜጎቿ የጀርመን ቢራን ሲጠጡ እንዲጠነቀቁ አሳሳበች

29 መጋቢት 2024, 11:25 EAT ብሪታኒያ በመጪው ክረምት ጀርመን ውስጥ የሚካሄደውን የአውሮፓ ዋንጫ ጨዋታዎችን ለመመልከት ወደ ጀርመን የሚሄዱ የእግር ኳስ ደጋፊዎች ቢራ ሲጠጡ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ የሚመክር ማሳሰቢያ አወጣች። የዩናይትድ ኪንግደም የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት በመጪው ሰኔ እና ሐምሌ ከሚካሄደው የእግር ኳስ ውድድር አስቀድሞ ማሳሰቢያውን ያወጣው የጀርመን ቢራ ከብሪታኒያ ቢራ ጠንካራ በመሆኑ ነው። በዩሮ2024 ላይ ተሳታፊ […]

በአፋር እና ኢሳ ሱማሌ ጎሳዎች መካከል ግጭት አገረሸ

March 29, 2024 – Konjit Sitotaw በአፋር ክልል፣ በአፋር እና ኢሳ ሱማሌ ጎሳዎች መካከል በድጋሚ በተያዘው ሳምንት ግጭት ማገርሸቱን ዋዜማ ሰምታለች። ግጭቱ የተከሰተው፣ በገቢ ረሱ ዞን (ዞን ሦስት) አሚባራ ወረዳ ውስጥ አፋርና ሱማሌ ክልሎች በሚወዛገቡበት ገዳማይቱ ቀበሌ እንደኾነ ታውቋል። በግጭቱ ቁጥራቸው ያልታወቁ ሰዎች ሳይገደሉና ሳይቆሰሉ እንዳልቀሩ ተነግሯል።