ያለፉት 5 ዓመታት የእንቁጣጣሽ ገበያ፡ ሽንኩርት፣ ዶሮ፣ ዕንቁላልና በግ ምን ያህል ጨመረ?

ከ 9 ሰአት በፊት በዓል ሲቃረብ ሸማች የሚለው ብዙ ነው። ‘የዘንደሮ ገበያ አይቀመስም’ ቀዳሚው ነው። ‘በዓል እንዴት ሊያልፍ ነው?’ ‘ኑሮ ጣራ ነካ!’ ሌላም ሌላም. . . ነጋዴ ደግሞ በተራው ‘አቅርቦት የለም’ ከሚለው ጀምሮ ‘ከቦታው ጨመረ’፣ ‘ምርት አልገባም’ የሚሉ ሰበቦችን ይደረድራል። መንግሥት በበኩሉ ‘በስግብግብ ነጋዴዎች የተፈጠረ ጭማሪ’ አልያም ‘የኢኮኖሚ አሻጠር’ ነው ይላል። አንዳንዴም በቂ አቅርቦት እንዳለ […]

ኡጋንዳዊቷን አትሌት በእሳት አቃጥሎ የገደለው የቀድሞ ፍቅረኛዋ በቃጠሎ ምክንያት ሞተ

ከ 1 ሰአት በፊት የኡጋንዳዊቷ ኦሊምፒክ አትሌቷ ሬቤካ ቺፕቴጌ የቀድሞ ፍቅረኛ የነበረው እና በእሳት አቃጥሎ የገደላት ግለሰብ መሞቱን የኬንያው ሆስፒታል ኃላፊዎች አሳወቁ። ግለሰቡ በደረሰበት ቃጠሎ ምክንያት ሆስፒታል ውስጥ የሕክምና እርዳታ ሲያገኝ እንደነበር ኃላፊዎቹ ተናግረዋል። ከአንድ ሳምንት በፊት ነበር ዲክሰን ንዲየማ የተባለው ግለሰብ የማራቶን ሯጯ ከቤተ-እምነት ስትመለስ ጠብቆ ነዳጅ በማርከፍከፍ በእሳት ያቃጠላት። የሰሜን ምዕራብ ኬንያ ባለሥልጣናት […]

የ2016 ዋነኛ ፖለቲካዊ ሁነቶች ምን ነበሩ?

ከ 9 ሰአት በፊት እየተሸኘ ያለው 2016 ዓ.ም. ሲገባ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ “የእንኳን አደረሳችሁ” መልዕክታቸውን ያስተላለፉት በአጭር ፅሁፍ ነበር። ቀደም ባሉት ዓመታት ከ600 ባላነሱ ቃላት መልዕክታቸውን ሲያስተላልፉ የነበሩት ዐቢይ፤ በ2016 ሀሳባቸውን በ100 ቃላት በቅቷቸው ታይተዋል። የዐቢይ መልዕክት አስኳል፤ “በቀጣዩ ዓመት ፈተናዎቻችን እጅግ ቀንሰው፤ ኅብረ ብሔራዊ አንድነታችን ከአልማዝ ጠንክሮ፤ የኢትዮጵያን ሰላም እና ደህንነት በጽኑ መሠረት […]

ሰሜን ዕዝ ላይ ጥቃት በመፈጸም የሞት ቅጣት የተፈረደባቸው 178 የመከላከያ ሠራዊት አባላት ተለቀቁ

ከ 3 ሰአት በፊት ከአራት ዓመት ገደማ በፊት በትግራይ ክልል በሚገኘው የአገር መከላከያ ሠራዊት ሰሜን ዕዝ ላይ “በክህደት መንፈስ ጥቃት” ከፍተዋል በሚል እስከ የሞት ቅጣት ድረስ ተላልፎባቸው የነበሩ የትግራይ ተወላጅ የሠራዊቱ አባላት በይቅርታ ተለቀቁ። በእስር ላይ የነበሩት የሠራዊቱ አባላቱ ይቅርታ የተደረገላቸው አዲስ ዓመትን በማስመልከት እንደሆነ የመከላከያ ሠራዊት ዛሬ ጷጉሜ 5/2016 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ አስታውቋል። የትግራይ […]

የጸጥታ ኃላፊው የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ሹም ሽር ማድረግ አይቻልም አሉ

ከ 5 ሰአት በፊት የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር የጸጥታ ቢሮ ኃላፊ ጄነራል ታደሰ ወረደ የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር ሹም ሽር እንዳያደርግ ከለከሉ። ጄነራል ታደሰ ትናንት ማክሰኞ ጳጉሜ 4/2016 ዓ.ም. በሰጡት መግለጫ በአቶ ጌታቸው ረዳ የሚመራው ጊዜያዊ አስተዳደር አመራሮችን “መሾምም ሆነ መሻር ማቆም አለበት” ብለዋል። በጊዜያዊ አስተዳደሩ ምክትል ፕሬዝዳንት ሆነው በማገልገል ላይ የሚገኙት ጄነራል ታደሰ፤ ጊዜያዊ አስተዳደሩ […]

በስለት የደረሰ ጥቃትን ተከትሎ ጀርመን የድንበር ጥበቃዋን ልታጠናክር ነው

ከ 7 ሰአት በፊት ባለፈው ነሐሴ ወር ጀርመን በስሎይንጋን ከተማ የደረሰውና ለሦስት ሰዎች ህልፈት ምክንያት የነበረውን የስለት ጥቃት ተከትሎ የድንበር ፍተሻና ጥበቃዋን ልታጠናክር ነው። ጥቃቱን እንዳደረሰ የተጠረጠረ ግለሰብ ሶርያዊ ዜግነት ያለው ሲሆን ያቀረበው የጥገኝነት ጥያቄ ወድቅ ተደርጎ ከጀርመን ተጠርዞ እየወጣ ነበር ተብሏል። በዚህም ሳቢያ የጀርመን መንግሥት የድንበር ጥበቃውን እንዲያጠናክር ጫና ሲደረግበት ነበር። አይ ኤስ የተባለው […]

እስራኤል ሰብዓዊ ቀጠና ተብሎ በተለየ ስፍራ ላይ ባደረሰችው ጥቃት 40 ሰዎች ተገደሉ

ከ 8 ሰአት በፊት የእስራኤል ጦር ሰብዓዊ ቀጣና ተብሎ በተለየ ስፍራ ላይ በፈጸመው የአየር ጥቃት 40 ሰዎች መገደላቸውን በሐማስ የሚመራው የፍልስጤም ጤና ሚኒስቴር አስታወቀ። የእስራኤል ጦር በበኩሉ የአየር ጥቃቱ ዒላማ ያደረገው በኽን ዩኒስ በሚገኘው የሐማስ ተዋጊዎች ማዕከል ላይ ነው ብሏል። በአካባቢው የነበሩ ነዋሪዎች ግን ሰብዓዊ ቀጣና ተብሎ በተከለለው ስፍራ ተፈናቃዮች ተጠልለው የነበሩበት ድንኳኖች ላይ ሦስት […]

የናይጄርያ ባለስልጣናት “የተፀለየበት” እየተባሉ የሚሸጡ ውሃዎችን ዜጎች እንዳይጠቀሙ አስጠነቀቁ

ከ 8 ሰአት በፊት የናይጄርያ መድሀኒት ቁጥጥር ባለሥልጣን “የተፀለየበት” ተብለው የሚሸጡ እና በናይጄርያዊው የቴሌቪዥን ወንጌል ሰባኪ፤ ጀርማያ ፉፌይን ቤተ እምነት በኩል የሚቀርቡ ምርቶችን ከመግዛት እንዲቆጠቡ ዜጎችን አስጠነቀቀ። ባለሥልጣኑ “የተፀለየበት ውሃ” እና “የዮርዳኖስ ወንዝ ውሃ” እየተባሉ ታሽገው የሚሸጡ ምርቶች መካን የሆኑ ሴቶች እንዲወልዱ ያደርጋሉ በሚል “በሐሰት” አንደሚሸጡ ገልጿል። መግለጫው አክሎም ምንም እንኳ የባለስልጣኑ ፈቃድ ባያገኝም ወንጌል […]

ከእስር ለተለቀቁ የኦነግ አመራሮች መንግሥት ይቅርታ እንዲጠይቅ እና ካሳ እንዲከፍል ተጠየቀ

ከ 5 ሰአት በፊት የኢትዮጵያ መንግሥት “በህገ ወጥ መንገድ” በእስር ላይ የቆዩ የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) አመራሮችን “ይቅርታ እንዲጠይቅ እና የጉዳት ካሳ እንዲከፍል” ዓለም አቀፉ የሰብዓዊ መብት ተሟጋቹ ሂውማን ራይትስ ዋች ጠየቀ። የሂውማን ራይትስ ዎች የአፍሪካ ቀንድ ዳይሬክተር ላቲሽያ ባደር በኤክስ ገጻቸው መንግሥት “በሕገ-ወጥ መንገድ” ለአራት ዓመታት አስሮ ላቆያቸው ፖለቲከኞች ይቅርታ የሚጠይቅበት እና ካሳ የሚከፍልበት […]

በ12ኛ ክፍል ፈተና ከ50 በመቶ በላይ ውጤት ያመጡ ተማሪዎች 5.4 በመቶ ብቻ ናቸው  – ኢትዮጵያ ኢንሳይደር

September 9, 2024 በቤርሳቤህ ገብረ የዘንድሮውን 12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተናን ከወሰዱ 674,823 ተፈታኞች ውስጥ፤ ከ50 በመቶ በላይ ውጤት ያስመዘገቡት ተማሪዎች 5.4 በመቶ ብቻ መሆናቸውን ትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ። ተማሪዎችን ካስፈተኑ ትምህርቶች ቤቶች መካከል 1,363 የሚሆኑት አንድም ተማሪ አለማሳለፋቸውን ሚኒስቴሩ ገልጿል። ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ይህንን የገለጸው የዚህን አመት የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ውጤት፤ ዛሬ ሰኞ […]