በተሽከርካሪዎች ለተጨናነቀችው አዲስ አበባ መፍትሄ ፍለጋ

September 24, 2024 – DW Amharic  በአንድ ወቅት የኮድ – 2 የግል ተሸከርካሪዎች በፈረቃ እንዲንቀሳቀሱ የሚል ውጥን በበርካቶች ቅሬታ ባነሳበት በአዲስ አበባ ከተማዋ አሁን ደግሞ ከትምህርት ቤቶች መከፈት ጋር ተያይዞ ሊፈጠሩ የሚችሉ የትራፊክ መጨናነቆችን ለመቀነስ የተወሰኑ የከተማዋ መስመሮች ለብዙሀን ትራንስፖርት አግልግሎት ብቻ ክፍት እንዲሆኑ የሚል ውሳኔ ብቅ ብሎ ነበር።… … ሙሉውን ለማየት ወይም ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ

የዓለም የምግብ መርሀ ግብር የኢትዮጵያ ተወካይ ጥሪ

September 24, 2024 – DW Amharic — Comments ↓ በ2024 7.5 ሚሊዮን ሰዎች ድጋፍ ለማድረግ ወጥነው አብዛኛውን ማሳካታቸውን የገለፁት ኃላፊው ሥራቸው ለሚያስፈልጋቸው ምግብ ማድረስ ቢሆንም ኢትዮጵያ ውስጥ በአሁኑ ወቅት ለሥራቸው ትልቁ የፀጥታ ሥጋት ያለበት አካባቢ አማራ ክልል ነው ብለዋል። የችግሩ ደረጃ ይለያይ እንጂ በሌሎች ክልሎችም ይሄው ፈተና የለም ለማለት እንደማይደፍሩ ገልፀዋል።… … ሙሉውን ለማየት ወይም ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ

የኢትዮጵያ ትራንስፖርት አሰሪዎች ፌዴሬሽን ማስጠንቀቂያ

September 24, 2024 – DW Amharic  ፕሬዝዳንቱ ፌዴሬሽኑ የሚጠበቅበትን ድጋፍ የማድረግ ኃላፊነቱንም መወጣቱን አስታውሰው “ሁሉም ወጪ ግን በኛ ብቻ ሊሸፈን አይገባም” በማለት ለትራንስፖርት ሚኒስቴር አቤት ማለታቸውንም ገልጸዋል፡፡በጭነት ተሸከርካሪዎች አገልግሎት ወደ 200 ሚሊየን ብር በህዝብ ማመላለሻም 100 ሚሊዮን ብር ገደማ አልተከፈለም ብለዋል፡፡… … ሙሉውን ለማየት ወይም ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ

የቀጠለዉ የትግራይ ፖለቲከኞች ዉዝግብ

September 24, 2024 – DW Amharic  ዶ/ር ደብረፅዮን ገብረ ሚካኤል፣ ጀነራል ፃድቃን ገብረትንሳኤን፥ ስልጣን ለመጠቅለል በማቀድ፣ የቆየ ቂም በመወጣት እና ሌሎች ከዚህ በፊት በይፋ ያልተሰሙ መረጃዎች በመግለፅ ሲተቹ ተደምጠዋል። ዶክተር ደብረፅዮን እርሳቸው የሚመሩት ህወሓት፣ ሰላም የማይፈልግ አድርጎ የማቅረብ የተሳሳተ ፍረጃ ከትግራይ ባለስልጣናት በኩል እየቀረበበት መሆኑ … ሙሉውን ለማየት ወይም ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት መርሕና 79ኛዉ ጉባኤ

September 24, 2024 – DW Amharic  አንዳዶች የሐገራት መሪዎች ኒዮርክ ቅምጥል ሆቴሎች ዉስጥ የሚንደላቀቁ፣ የሚቀብጡ፣ የሚገባበዙበት ዓመታዊ ድግስ ይሉታል።መሪዎች ላጭር ጊዜም ቢሆን ለዓለም የልባቸዉን የሚናገሩበት አጋጣሚ የሚሉትም አሉ።የደካማ-ድሆቹ ሐገራት መሪዎች የኃያላን-ሐብታሞቹን ድጋፍና ርጥባን ለማግኘት የሚሻሙበት ሥብሰባ ነዉ ባዮችም አሉ።ሌሎች ሌላ።ጉባኤዉ ሁሉንም ነዉ… … ሙሉውን ለማየት ወይም ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ

የስፖርት ዘገባ

September 24, 2024 – DW Amharic  በሳምንቱ መጨረሻ እጅግ ተጠባቂ በነበረው የማንቸስተር ሲቲ እና አርሰናል ፍልሚያ ሲቲ በሜዳው ጉድ ከመሆን የማታ ማታ ተርፏል ። አርሰናል ሙሉ ግማሽ የጨዋታ ክፍለ ጊዜውን አንድ ተጨዋች ጎድሎበትም አይበገሬነቱን ዐሳይቷል ። ቸልሲ እና በሻምፒዮንስ ሊጉም ድል የቀናው ሊቨርፑል በተመሳሳይ የግብ ልዩነት ተጋጣሚዎቻቸውን አሰናብተዋል ።… … ሙሉውን ለማየት ወይም ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ