ብልፅግና ያቋቋመው ሚስጢራዊ የጸጥታ ኮሚቴ ግድያዎችን እንዲያቆም ግፊት እንዲደረግ ተጠየቀ

March 12, 2024 – Konjit Sitotaw  ኦነግ፣ መንግሥት ያቋቋመው ሚስጢራዊ የጸጥታ ኮሚቴ ኦሮሚያ ክልል ውስጥ የሚፈጽማቸው ግድያዎች እንዲቆሙ ሕዝቡ፣ ዓለማቀፉ ኅብረተሰብና የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች ግፊት እንዲያደርጉ ጠይቋል። የጸጥታ ኮሚቴው አባላት ለፈጸሟቸው ተግባራት ተጠያቂ እንዲኾኑ እነዚኹ አካላት ጥረታቸውን እንዲቀጥሉም ኦነግ ጥሪ አድርጓል። ኦነግ ጨምሮም፣ በአብዛኞቹ የክልሉ ዞኖች ከፍርድ ውጭ የኾኑ ግድያዎች፣ የዘፈቀደ እስሮች፣ ስቃይ እና ምዝበራ እንደቀጠለ […]

ደቡብ አፍሪቃ ለመግባት በሚሞክሩ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ላይ የሞት አደጋ ተባብሷል

March 12, 2024 – Konjit Sitotaw  ደቡብ አፍሪቃ ለመግባት በሚሞክሩ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ላይ የሞት አደጋ ተባብሷል ወደ ደቡብ አፍሪቃ ለመግባት በሚሞክሩ ኢትዮጵያዊያን ፍልሰተኞች ላይ የሚደርሰው የሞት አደጋ እየተባባሰ መምጣቱን ከኬኒያ እና ታንዛኒያ እሥር ቤቶች ተለቀው ዛሬ በኢትዮጵያ ሞያሌ በኩል ወደ አገራቸው የገቡ ተመላሽ የአይን እማኝ ፍልሰተኞች መመልከታቸውን ዶይቼ ቬለ ዘግቧል። በስደት ጉዞና በእሥር ቆይታቸው አስቸጋሪ ፈተናዎችን ማለፋቸውን […]

ባይደን እና ትራምፕ በሚቀጥለው ምርጫ ለመፋጠጥ የሚበቃቸውን ድምፅ አገኙ

ከ 4 ሰአት በፊት የወቅቱ የአሜሪካ ፕሬዝደንት ጆ ባይደን እና የቀድሞው ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ በሚቀጥለው ምርጫ ለመፎካከር የሚያስችላቸውን ድምፅ አገኙ። የአሜሪካ ፕሬዝደንታዊ ምርጫ ከ8 ወራት በኋላ ኅዳር 2017 ዓ.ም. ይካሄዳል። አራት ግዛቶች፣ አንድ የአሜሪካ ክፍል እና በመላው ዓለም የሚኖሩ ዴሞክራቶች ማክሰኞ ዕለት ዕጯቸውን መርጠዋል። ይህ ማለት በአውሮፓውያኑ 2020 የተመለከትነው የባይደን እና ትራምፕ ፍጥጫ በ8 ወራት […]