በኢትዮጵያ በቀጣዮች ጥቂት ወራት ውስጥ አስከፊ የምግብ እጥረት የሚያጋጥማቸው ዜጎች ቁጥር ይጨምራል

February 3, 2024  የአደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን ኮሚሽነር ሽፈራው ተክለማርያም እና የተመድ የሰብዓዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ቢሮ የኢትዮጵያ ተወካይ ራሚዝ አላክባሮቭ በጋራ ባወጡት መግለጫ; በኢትዮጵያ በቀጣዮች ጥቂት ወራት ውስጥ አስከፊ የምግብ እጥረት የሚያጋጥማቸው ዜጎች ቁጥር እንደሚጨምር ገልጸዋል። በተለይም ከሰኔ መጨረሽ እስከ ነሐሴ ባሉት ጊዜያት ከፍተኛ የምግብ እጥረት የሚያጋጥማቸው ዜጎች ቁጥር 10 ነጥብ 8 ሚሊዮን ሊደርስ እንደሚችል […]

የጠቅላይ ሚኒስትሩን የፋዎ ሽልማት ለማስመለስ ያለመ የተቃውሞ ፊርማ መሰብሰብ ተጀመረ

February 3, 2024 – Konjit Sitotaw  ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ከዓለም የምግብና እርሻ ድርጅት ያገኙትን ሽልማት ለማስመለስ ያለመ የተቃውሞ ፊርማ በበይነ መረብ እየተሰበሰበ እንደሚገኝ ታወቀ። የተቃውሞ ፊርማው ‘ቼንጅ’ በተባል ድረ ገጽ ላይ ‘ዩኒቲ ፎር ኢትዮጵያ’ (Unity For Ethiopia) በተሰኘ ስብስብ አስጀማሪነርት እየተከናወነ መሆኑ ተረጋግጧል። ሽልማቱን በመቃወም የተሰባሰቡት አካላት “ሽልማቱ መሪዎች አገራቸውን በማረጋጋት እና የዜጎችን ሕይወት ለማሻሻል ላደረጉት […]

የሰላም ግንባታና ፍትህ በትግራይ ዓለም አቀፍ ጉባዔ

February 3, 2024 – DW Amharic «የሰላም ግንባታ እና ፍትሕ በድህረ ጦርነት ትግራይ» በሚል ርዕስ በዙም በተካሄደ ውይይት በኢትዮጵያ ትግራይ ክልል፣ ሰላም ፍትህና ተጠያቂነት ለማስፈን የዓለም አቀፍ የፍትህ አካላት ተሳትፎ እንዲኖር በውጭ የሚኖረው የክልሉ ማኀበረሰብ ግፊት እንዲያደርግ የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝደንት ጥሪ አቅርበዋል።… … ሙሉውን ለማየት ወይም ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ

ተፈናቃዮችን ለመመለስ በአማራና በኦሮሚያ ክልሎች እየተደረጉ ያሉ ጥረቶች

February 3, 2024 – DW Amharic  በተለያዩ ምክንያቶች ከቀያቸው የተፈናቀሉ ወገኖችን ለመመለስ የኦሮሚያና የአማራ ክልል መንግሥታት በጋራ እየሠሩ መሆናቸውን የአማራ ክልል መንግሥት አስታወቀ። ከሁለቱ ክልሎች የተውጣጣ ኮሚቴ በምሥራቅና ምዕራብ ወለጋ ዞኖች ጉብኝት ያደረገ ሲሆን አንዳንድ ተፈናቃዮች አስተማማኝ ሰላም ካለ ወደ አደጉባቸው አካባቢዎች ለመመለስ ዝግጁ መሆናቸውን ገልጸዋል።… … ሙሉውን ለማየት ወይም ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ

በሳምንት የአራት ቀን ስራ የሙከራ ፕሮጀክት በጀርመን

February 3, 2024 – DW Amharic  ከትናንት ጀምሮ ጀርመን ውስጥ የሚገኙ 45 ድርጅቶች በአንድ የሙከራ ፕሮጀክት መሳተፍ ጀምረዋል። ይኼውም ሰራተኞቻቸው እንደተለመደው በሳምንት አምስት ቀናት ሳይሆን አራት ቀናት ብቻ እየሰሩ ተመሳሳይ ደሞዝ ይከፈላቸዋል። የዚህ የሙከራ ፕሮጀክት ዓላማ ለሰራተኛው ተጨማሪ የዕረፍት ቀን መጨመር ብቻ ሳይሆን የድርጅቱንም ምርታማነት ማሳደግ ነው።… … ሙሉውን ለማየት ወይም ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ

የአቶ ደመቀ መኮንን ስንብት እና የጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ ሽልማት ጉዳይ

February 3, 2024 – DW Amharic የውጭ ጉዳይ እና ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ከብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚደንትነት መሰናበታቸው፤ ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አህመድ ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት የምግብ እና እርሻ ድርጅት ፋኦ ሽልማት መቀበላቸው ፤ እንዲሁም የኢትዮጵያ መንግስት በናፍታ የሚሰሩ ተሽከርካሪዎች ወደ ሀገር ውስጥ እንዳይገቡ መታገዳቸው… … ሙሉውን ለማየት ወይም ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ