መንግስት እና የህዝብ ተወካዮች በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ህጋዊነት እና ተመጣጣኝነት ላይ ማጤን አለባቸው – ኮሚሽነር ዳንኤል በቀለ

February 2, 2024 – Konjit Sitotaw  የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት እና መንግስት በተራዘመው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ህጋዊነት እና ተመጣጣኝነት ላይ ትኩረት ማድረግ እንደሚገባቸው የመብቶች ኮሚሽኑ ኮሚሽነር አሳሰቡ። የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ኮሚሽነር ዳንኤል በቀለ በይፋዊ የ’ኤክስ’ ገጻቸው ባሰፈሩት አጭር ጽሁፍ ኢሰመኮ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ መራዘም “እጅግ አሳስቦታል” ማለታቸውን ተመልክተናል። ዛሬ ረፋድ ልዩ ስብሰባ ያደረገው የኢትዮጵያ […]

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ከፓርላማ አባላት ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች፤ በመጪው ማክሰኞ ምላሽ ሊሰጡ ነው – ኢትዮጵያ ኢንሳይደር   

February 2, 2024 በተስፋለም ወልደየስ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ከፓርላማ አባላት ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች፤ በመጪው ሳምንት መጀመሪያ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በመገኘት ምላሽ እና ማብራሪያ እንደሚሰጡ ምንጮች ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ተናገሩ። የፓርላማ አባላቱ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ የሚቀርቡ ጥያቄዎችን አስገብተው ያጠናቀቁት በዚህ ሳምንት መጀመሪያ ነው። “ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ያነጋገረቻቸው ሶስት የፓርላማ አባላት፤ ጥያቄዎችን እንዲያቀርቡ የተሰጣቸው ቀናት ብዛት ሶስት ብቻ እንደነበር […]

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ለአራት ወራት ተራዘመ – ኢትዮጵያ ኢንሳይደር

February 2, 2024 ላለፉት ስድስት ወራት በዋነኛነት በአማራ ክልል ተፈጻሚ ሲደረግ የቆየው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ፤ ለተጨማሪ አራት ወራት እንዲራዘም የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ውሳኔ አስተላለፈ። የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ለመራዘም ለምክር ቤቱ የቀረበውን የውሳኔ ሃሳብ የጸደቀው፤ በሁለት የፓርላማ አባላት ተቃውሞ እና በሶስት ጽምጸ ተዐቅቦ ነው። የተወካዮች ምክር ቤት በሚኒስትሮች ምክር ቤት የቀረበለትን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ያጸደቀው […]

አስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ለተጨማሪ አራት ወራት ተራዘመ

2 የካቲት 2024, 11:11 EAT ላለፉት ስድስት ወራት በዋናነት በአማራ ክልል ላይ ተጥሎ የቆየው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ለተጨማሪ አራት ወራት እንዲራዘም የቀረበውን ሐሳብ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አጸደቀ። ምክር ቤቱ ዛሬ አርብ ጥር 24/2016 ዓ.ም. ባካሄደው ልዩ ስብሰባ ሐምሌ 28/2015 ዓ.ም. የሕዝብን ሰላም እና ደኅንነት ለማስጠበቅ ያወጣውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ቁጥር 6/2015 ለማራዘም የቀረበለትን የውሳኔ […]

በአማራ ክልል መርዓዊ ከተማ ከ50 በላይ ሰዎች መገደላቸውን የዐይን እማኞች ተናገሩ

2 የካቲት 2024, 15:05 EAT በአማራ ክልል በአዲሱ ሰሜን ጎጃም ዞን መርዓዊ ከተማ ሰኞ፣ ጥር 20/2016 ዓ.ም በተፈጸመ ጥቃት ከ50 በላይ ሰዎች መገደላቸውን ቤተሰቦች፣ ነዋሪዎች አና የዐይን እማኞች ለቢቢሲ ተናገሩ። ከክልሉ ዋና ከተማ ከባሕር ዳር በ35 ኪሎ ሜትር ገደማ ርቀት ላይ በምትገኘው መርዓዊ ከተማ በመከላከያ ሠራዊት እና በፋኖ ታጣቂዎች መካከል የተደረገ ውጊያን ተከትሎ በነዋሪዎች ላይ […]

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በሚቀጥለው ሳምንት ለተወካዮች ምክር ቤት ማብራሪያ ሊሰጡ ነው

2 የካቲት 2024, 17:38 EAT ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በቀጣይ ሳምንት በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቀርበው ከአባላት ለሚነሱላቸው ጥያቄዎች ምላሽ እና ማብራሪያ እንደሚሰጡ በተወካዮች ምክር ቤት የቢቢሲ ምንጮች ተናገሩ። በምክር ቤቱ አሠራር መሠረት የሕዝብ እንደራሴዎች ለጠቅላይ ሚኒስትሩ የሚያቀርቧቸውን ጥያቄዎች ባለፈው ሳምንት ቅዳሜ ለአፈ ጉባኤው ጽህፈት ቤት እንዲያስገቡ በአባላት የመልዕክት መለዋወጫ የቴሌግራም ገጽ አማካይነት ተጠይቀው እንደነበር […]