ብርቱ ርብርብ ቢደረግም ሊገታ ያልቻለው የካሊፎርኒያው ሰደድ እሳት

January 14, 2025 – VOA Amharic  በአሜሪካ ሎስ አንጀለስ ከተማ እና በአካባቢው የተቀሰቀሰውን የሰደድ እሳት መስፋፋት ለመግታትና ለማጥፋት እየተደረገ ካለው መጠነ ሰፊ ርብርብ በአንጻሩ፣ እስከ አሁን ለመቆጣጠር አልተቻለም። እንዲያውም ከፍተኛ ፍጥነት ባለው ነፋስ ደረቅ በመታገዝ እየተባባሰ ያለው የሰደድ እሳቱ፣ በየሰዓቱ የሚያደርሰው ውድመት አስከፊ እንደኾነ ነው የተገለጸው። የጠፋውም እሳት ቢኾን፣ ረመጡ በደረቁ ነፋስ ዳግም ሊቀ… … ሙሉውን ለማየት […]

ከታሪክ ማኅደር ፦  በኢትዮጵያ የዛሬ 40 ዓመት ከ400 የሚበልጡ ሰዎችን ሕይወት የቀጠፈው አሰቃቂ  የባቡር አደጋ

January 14, 2025 – VOA Amharic  ከድሬዳዋ  ወደ አዲስ አበባ በመጓዝ ላይ እያለ ወደ አዋሽ ከተማ ሲቃረብ  ሐዲዱን ስቶ በመገልበጥ ቁጥሩ ከ418 የሚበልጥ ሕይወት የጠፋበት የባቡር አደጋ የደረሰው  ከአርባ ዓመታት በፊት በ1977 ዓ.ም. በዛሬው ዕለት ነበር፡፡ የፈረንሳይ እና ኢትዮጵያ የባቡር መስመር ኩባኒያን ጠቅሶ  አሶሲየትድ ፕሬስ በዕለቱ ያስነበበው ዘገባ እንዳተተው በአደጋው ከሞቱት በተጨማሪ 559 ሰዎች ቆስለዋል፡፡ 1 … … ሙሉውን […]

ኦቪድ ሪል ስቴት ………… በዚህ ዘመን የህዝብን እውነት እና የሚድያን ስራ ማፈን አይቻልም።

January 14, 2025 ኤሊያስ መሰረት ይሁንና በዚህ ያልተደሰቱት ኦቪዶች ሁለት ነገር አደረጉ: አንደኛው የመሠረት ሚድያ ፕላስ (Meseret Media+) የዩትዩብ ቻናል ሞኒታይዜሽንን ሪፖርት አርገው አዘጉ፣ በሌላ በኩል እኔን አናገሩ። ቻናሉን ማዘጋታቸው ትክክል እንዳልሆነ ነግሬያቸው (እንዳዘጉ የተናገሩበት የድምፅ ቅጂ/ሪከርድ ሙሉው አለ) በዜናው ላይ ማንኛውም አይነት ቅሬታ እና ትክክል አይደለም ብለው የሚያስቡት ነገር ካለ ላኩት እና አጣርተን ስህተት […]

ከ450 በላይ የፊንጫ ስኳር ፋብሪካ ሠራተኞች መታሰራቸው ተገለጸ

January 14, 2025 – VOA Amharic  በሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞን ሱሉላ ፊንጫ ወረዳ በሚገኘው የፊንጫ ስኳር ፋብሪካ፣ ከ450 በላይ ቋሚ እና የኮንትራት ቅጥር ሠራተኞች መታሰራቸውን፣ ቤተሰቦቻቸው እና የፋብሪካው ሠራተኞች ለአሜሪካ ድምፅ ተናግረዋል። የሱሉላ ፊንጫ ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ ፋንታሁን ታዬ፣ ሠራተኞቹ የታሰሩት “በፋብሪካው ይዞታ ውስጥ በሕገ ወጥ መንገድ የግብርና ሥራ ላይ ተሰማርተው በመገኘታቸው ነው፤” ሲሉ ለአሜሪካ ድምፅ ተ… […]