በአሜሪካን የሚገኝ የትግራይ ተወላጆች ማህበር መንግስት ለኢሳት ቴሌቪዢን ምህረት ማድረጉን ተቃወመ!

02/06/2018 መቀመጫውን በሰሜን አሜሪካ ያደረገና የትግራይ ተወላጆች ማህበር የተሰኘ አንድ ድርጂት ኢሳት ቴሌቪዢን ላይ ተመስርቶ የነበረው የሽብርተኝነት ክስ መነሳቱ እንዳሳዘነው በመግለጽ ለጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ አህመድ ደብዳቤ ጽፏል። ማህበሩ በዚሁ ደብዳቤው ላይ እንዳሰፈረው መንግስት ኢሳት ቴሌቪዥን ወደ ሀገር ገብቶ መስራት እንዲችል ጥሪ ማቅረቡ አግባብ አይደለም ብሏል። ከሁለት አመታት በፊት ኢሳት ባሰራጨው አንድ ዘገባ በትግራይ ህዝብ ላይ […]

አሁን ነው ትልቁ ፈተና!! ከስሜት ህክምና ወደ ተቋማት ህክምና!!! (ሀብታሙ አያሌው)

02/06/2018  ዶ/ር አብይ አህመድ የተረከቧት ሀገር ላለፉት 27 ዓመታት የስሜትና የተቋማት ቁስለት የደረሰባትን ሀገር ነው። በመሆኑም፣ ዘመኑ የጣለባቸው ኃላፊነት የስሜትና የተቋማት ህክምና በማድረግ ልትፈርስ የነበረችውን ሀገር ማዳን ነው። ይሄ ምን ማለት ነው? የኢህአዴግ ፖለቲካ ከሚገለፅባቸው ባህሪዎቹ ውስጥ ድብቅነት፣ ሴረኛነት፣ አደርባይነት፣ ስግብግብነት፣ ግለኝነት፣ ትዕቢተኛነትና ማን አህሎኝነት ዋና ዋናዎቹ ናቸው። በእነዚህ ባህሪዎቹ የተነሳ የኢህአዴግ ፖለቲካ ሰብዓዊነት የማይሰማውና […]

ተቃዋሚዎች እና ዘጠኙ ቂሎች (ወሰን ሰገድ ገ/ኪዳን)

02/06/2018 ዶ/ር አቢይ የጠቅላይ ሚኒስትርነት ስልጣን ከተቆናጠጡ ዛሬ (ግንቦት 24) ስድሳ ቀን ሞላቸው፡፡ እኛም የዶ/ር አቢይን እርምጃ አንዳንዴ በጥርጣሬ፣ አንዳንዴ በመገረም፣ አንዳንዳንዴም በመደነቅ እየተመለከትንና እያስተዋልን 60 ቀናት ያህል በዝምታ ቆየን፡፡ አሁን የተቃዋሚዎች ቅዋሜ ደርዝ የለሽ እየሆነ መሄዱን በታዘብን ጊዜ ዝምታችንን ሰብረን ብቅ አልን፡፡ . እዚህ ላይ ዶ/ር አቢይ ወደ ሥልጣን ከመጡ ወዲህ የከወኑትን ደግመን አንዘረዝርም፡፡ […]

አማራዎች ይፈናቀላሉ፣ ልሂቃኑ ይጠላለፋሉ፣ የህወሓትን ግብ ያሳካሉ! | ስዩም ተሾመ

June 2, 2018  ባለፉት ሦስት ሳምንታት ከተለያዩ የኦሮሚያ አከባቢዎች ስለተፈናቀሉ የአማራ ተወላጆች ጉዳይ በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ በስፋት እየተነገረ ይገኛል። ብዙ ተስፋ የተጣለበት አዲሱ የዶ/ር አብይ አመራር፣ በተለይ ደግሞ ወደ ባህር ዳር በመሄድ በኢትዮጲያዊነት መንፈስ የኦሮሞና አማራ ሕዝቦች አንድነትና አብሮነት መልሶ እንዲያሰራራ ያደረጉት ኦቦ ለማ መገርሳ በፕረዜዳንትነት በሚመሩት ክልል ውስጥ የአማራ ብሔር ተወላጆች መፈናቀላቸው ለብዙ የአማራ […]

የህዋሓት በአዴን መሪዎች ለውጡ አይዋጥላችሁምን? በቃሬዛ ላይ ሆናችሁ ዘልኣለማዊ አገዝዝ ልትገዙን ነው ?

June 2, 2018 አስገደ ገብረስላሴ የህወሓት በአዴን መሪዎች ጠ/ ምኒስቴር አብይ አህመድ አሊ የእናንተ አባታውያን መሪዎች አጥር ሰብሮ ጥሶ ከወጣ እኖሆ ከ60 ቀናት በላይ አሰቆጥሯል ። በነዚህ 60 ቀናት ውስጥ ከኢህአደግ አባታዎውያን aመሪዎች አስተሳሰብ ያፈነገጠ የሚመስል ከገመቱት በላይ እጅግ ቡዙ አመርቂ ስራዎች ሰርቷል ።እነዚህ አመርቂ ሰራዏች ግን ለህወሓት ኢህአደግ ነባር መሪዎች ፣የነሱ ጥገኞች ተከታዮች አክራሪ […]

የለማ ገዱና አብይ ጉዳይ ድራማ ነው አውነት? ጉድ ፈላ! (ሰርፀ ደስታ)

June 3, 2018 የአገሬ ልጆች እንዴት ናችሁ?ኤጆሌ ቢያ አካም ጂርተን! ወደፊት ኦሮምኛ እንግዲህ ሌላው የፌደራል ቋንቋ መሆኑም አደለ ትንሽ ትሽ እንማራ  (ጢቆ ጢቆ/ጢኖ ጢኖ ሀበረኑካ)፡፡ ሰሞኑን ትንሽ ነገሮች የተደበላለቁ መሰለኝ፡፡ እስካሁን እነለማ ድራማ እየሰሩ ነው የሚሉ ብዙዎች ነበሩ፡፡ እንደሚመስለኝ እነለማ እያደረጉ ያለውን ሳያዩ ቀርተው ሳይሆን ሥራቸው ባይሳካ ስለሚመኙ ይመስላል፡፡ ከቀን ወደ ቀን ግን እነለማ አብይ […]

የወገራ አዉራጃ የቀድሞዉ አስተዳዳሪ የቢተወደድ አዳነ መኮነን ልጅ አቶ ግዛቸዉ አዳነ በህወሃት ተገደለ (አያሌው መንበር)

June 1, 2018 ዛ ግዛቸዉ አዳነ  በዘጠኝ ጥይት ተገደለ። የወገራ አዉራጃ የቀድሞዉ አስተዳዳሪ የቢተወደድ አዳነ መኮነን ልጅ አቶ   ግዛቸዉ አዳነ  መኮነን  በወልቃይት የአማራነት ማንነት እንቅስቃሴ አጋዥ ሚና ነበረዉ። ግድያዉ የተፈፀመዉ በህዉሓት ወታደሮች ነዉ። የወልቃይት የአማራነት ኮሚቴ ጥያቄያቸዉን ለፌዴሬሽን ምክርቤት ለሁለተኛ ጊዜ ማስገባታቸዉን ተከትሎ የወልቃይት አጀንዳ ዳግም አገርሽቷል። ጉዳዩን አስመልክቶ የአማራ ክልል መንግስት የሰጠዉ አስተያደት የለም።   ፋሽሽቱ የትግሬ ወያኔ አቶ […]

የመከላከያ ሰራዊቱን በአዲስ መልክ የማደራጀት ስራ ይፋ ተደረገ

June 1, 2018 ዋዜማ ራዲዮ- የመከላከያ ሰራዊት ከፍተኛ አመራሮችን በብቃት በትምህርትና ስልጠና ዝግጅት እንዲሁም የሀገሪቱን የብሄር ተዋፃኦ ባገናዘበ መልኩ ለማደራጀት አዲስ የምደባ መዋቅር መዘጋጀቱን ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አህመድ አስታወቁ። ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ ከመከላከያ ባለስልጣናት ጋር አርብ ዕለት ባደረጉት ውይይት በአዲሱ አደረጃጀትና ማሻሻያ የአመራር ለውጥ የሚደረግ ሲሆን ይህ ለውጥ ሀገሪቱ ያለችበትን ሁኔታ ባገናዘበ መንገድ እንደሚካሄድና ማንንም […]

የትግሉ ትኩረት በህወሃት/በረከት በሚመራው ቀልባሽ ቡድን ላይ ቢያነጣጥር (ፋሲል የኔአለም)

June 1, 2018 አብይ ከወታደራዊ አዛዦች ጋር ያደረገውን ሙሉ ውይይት ባልሰማውም የተሰሩ ዘገባዎችን አይቻለሁ። አብይ ከቅርንጫፍ ቆረጣ ወደ ስር ነቀላ እየተሸጋገረ መሆኑን የሚያመለክት ነው። አልጋው እየረጋ በራስ መተማመኑም እየጨመረ ይመስላል። በሚቀጥሉት ሁለት ወራት በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ የሞት ሽረት ትግል ይካሄዳል። ቀልባሹ ሃይል የባቡሩን ጉዞ ለማደናቀፍ ያለ የሌለ ሃይሉን እያሰባሰበ ነው። ቀልባሾች ስር የሰደደ ህዝባዊ ድጋፍ […]