የአገዛዙን ሸፍጥ ልብ ብላቹህ እየተከታተላቹህት ነው??? (አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው)

2019-05-18 የአገዛዙን ሸፍጥ ልብ ብላቹህ እየተከታተላቹህት ነው???አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው* ዐቢይና ለማ ምን እያሉ ሿሿ እንደሠሯቹህና በኋላ ላይ እነማን ሆነው እንደተገኙ የቅርብ ጊዜ ትዝታ ነውና የምትረሱት አይመስለኝም፡፡  አስገራሚው ነገር እስከ አሁኗ ዕለት ድረስ ዐቢይ እና ለማ ሕዝብን ባጃጃሉበት መንገድ በተደጋጋሚ እየተጃጃልን መገኘታችን ነው፡፡ ለወትሮው “ሞኝን ሁለት ጊዜ እባብ ይነድፈዋል የመጀመሪያውን ሳያይ ሁለተኛውን ሲያሳይ!” ይባል ነበር፡፡ የሀገሬ […]

የከተሞቻችን ፅዳት እንዲህ ከሆነ መሰልጠን መገለጫው ምን ይሆን? – ሙሉጌታ ገዛኸኝ

May 17, 2019 Source: https://www.zehabesha.com/amharic/archives/95357 በ ሙሉጌታ ገዛኸኝ gezahegn.mulu@yahoo.com ለዛሬው ማኅበራዊ ትችት መነሻየ መሰልጠን በምን ይገለፅ? የጠፋው የሰለጠነ ሰው ወይስ ቴክኖሎጂው? ጥቂት እያነሳን ብንጥል ምን ይለናል? የሀገራችን ባሕልና ታሪክ ሲዳሰስ የጥንታዊ ስልጣኔ ባለቤት ከሆኑት እጅግ ጥቂት አገሮች አንዷ መሆኗን ያስረዳል፡፡ የተፈጥሮ ፀጋ የተላበሰችው ኢትዮጵያ በርካታ መስህቦችም አሏት፡፡ በተለይም የሰው ዘር መገኛ፣ የቡና መገኛ፣ የአባይ ወንዝ፣ […]

የወላይታ ህዝብ ክልል የመሆን ጥያቄ ይመለስ በሚል ሰላማዊ ሰልፍ ተካሄደ

ሰልፍ ተካሄደ May 17, 2019 Source: https://fanabc.com አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 9 ፣ 2011 (ኤፍ ቢ ሲ) የወላይታ ህዝብ ክልል የመሆን ጥያቄው ይመለስ በሚል ሰላማዊ ሰልፍ ተካሄደ። ሰላማዊ ሰልፉ በወላይታ ሶዶ ከተማ የተካሄደ ሲሆን፥ የወላይታ ዞን ራሱን በክልል የማስተዳደር መብቱ ይከበር ዘንድ የተጠየቀበት ነው። በሰልፉ የወላይታ ህዝብ የክልል ጥያቄ ይመለስ፣ ሀገራዊ ለውጡ ተጠናክሮ እንዲቀጥል የህግ […]

የትልልቅ ተቋማት ሽያጭና የኢትዮጵያዊያን እጣ ፈንታ!

May 17, 2019 Source: http://ethiodigest.org በመቅደስ አስራት May 17, 2019ተስፋና ስጋት! በዚህ ሳምንት ግንቦት 7 እና 8 እዚህ ዋሽንግተን ዲሲ በኢትዮጵያ ኤምባሲና በ US Department of State በተዘጋጀው “Ethiopian Partnerships Forum” የመገኘት ዕድል ገጥሞኝ ነበር:: የዝግጅቱ ዋና ዓላማ በተለያዩ የንግድና ኢንቨስትመንት ዘርፎች የሚንቀሳቀሱ ድርጅቶችን፦ አሜሪካዊያንና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን ባለሃብቶችን መዋዕለ ነዋያቸውን ኢትዮጵያ ላይ እንዲያፈሱ በኢንቨስትመንትና በፕራይቬታይዘሽን […]

ታሪክ ሊቀይር ተነስቶ ታሪክ የሆነው የግንቦት ስምንቱ መፈንቅለ መንግስት ሙከራ…!!! (ቢቢሲ አማርኛ)

2019-05-17 ታሪክ ሊቀይር ተነስቶ ታሪክ የሆነው የግንቦት ስምንቱ መፈንቅለ መንግስት ሙከራ…!!! ቢቢሲ አማርኛ* ግንቦት 8፣ የነፍስ ውጭ፣ ነፍስ ግቢ ዕለት * ግንቦት 8 የኾነው በትክክል ምንድነው? * የኮ/ል መንግሥቱ አውሮፕላን ለምን አልጋየም?* ጄኔራሎቹ ራሳቸውን ለምን አጠፉ?* ጄኔራል አበራ እንዴት አመለጡ? ለምን አመለጡ ? —የዛሬ 30 ዓመት፣ ማክሰኞ’ለታ የወጣችው ጨረቃ “ጤፍ ታስለቅም ነበር”። ሌ/ኮ ካሳዬ ታደሰ ናቸው […]

“የወሰንና የማንነት ጉዳዮች ኣጣሪ ኮሚሽን” ኣስመልክቶ ከሳልሳይ ወያነ ትግራይ የተሰጠ መግለጫ

2019-05-17 “የወሰንና የማንነት ጉዳዮች ኣጣሪ ኮሚሽን” ኣስመልክቶ ከሳልሳይ ወያነ ትግራይ የተሰጠ መግለጫ* ግዛታዊ ኣንድነት ለትግራይ ህዝብ ህልውና የማስቀጠል ጉዳይ ነው!! ኣንድ ብሄር በቋንቋው ለመማር፣ ለመዳኘትና ለመተዳደር እንዲሁም  ቋንቋው፣ ባህሉ፣ ታሪኩ፣ ፍልስፍናው፣ ስነ ጥበቡ ወዘተ ለመጠቀም፣ ለማበልፀግና ለመጠበቅ የራሱ ግዛት ያስፈልገዋል፡፡ ለዚህም ነው የትግራይ ህዝብ ማህበራዊ መሰረቱ በማጥበብና ስትራቴጂካዊ ቦታዎችን በማሳጣት ፖለቲካዊ እና ኢኮኖሚያዊ ተወዳዳሪነቱን ለማዳከም […]

ትራምፕ አዲስ የስደተኞች ዕቅድ ይፋ አደረጉ

May 17, 2019 Source: https://fanabc.com አዲስ አበባ፣ ግንቦት 9፣ 2011 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ወደ ሀገሪቱ የሚገቡ ስደተኞችን የሚመለከት አዲስ ዕቅድ ይፋ አደረጉ። ትራምፕ ትናንት ማምሻውን እንዳስታወቁት፥ ከዚህ በኋላ ወደ አሜሪካ የሚገቡ ስደተኞች የተማሩ፣ ወጣቶች፣ እንግሊዝኛን መናገር የሚችሉ እና የሚሰጣቸውን የስነዜጋ ፈተና የሚያልፉ መሆን አለባቸው። እንዲሁም አብዛኛዎቹ ወደ አሜሪካ የሚገቡ ስደተኞች በቤተሰብ አማካኝነት እንደሚመጡ […]

ቦይንግ የ737 ማክስ ሶፍትዌርን አሻሽያለሁ አለ – ቢቢሲ /አማርኛ

ቦይንግ 737 ማክስ ሶፍትዌር ላይ እያደረገ የነበረውን ማሻሻያ መጨረሱን ይፋ አድርጓል። ባለፉት አምስት ወራት ብቻ ኢትዮጵያ ውስጥ የተከሰከሰውን አውሮፕላን ጨምሮ በ737 ማክስ ሁለት የከፉ አደጋዎች መድረሳቸው ይታወሳል። ቦይንግ የሶፍትዌር ማሻሻያ ባደረገባቸው 737 ማክስ አውሮፕላኖች 207 በረራ ማድረጉን አሳውቋል። • “አደጋውን ስሰማ በረራው ጠዋት እንዳልሆነ ራሴን አሳመንኩኝ” የረዳት አብራሪው ጓደኛ አብራሪዎች አውሮፕላኑን ስለሚቆጣጠሩበት መንገድ ለፌደራል አቪዬሽን […]

ፌስቡክ አፍሪካ ላይ የተቃጡ ገጾችን ዘጋ – ቢቢሲ /አማርኛ

ፌስቡክ በመቶዎች የሚቆጠሩና አፍሪካ ላይ አነጣጥረዋል ያላቸውን ገጾችና አንድ የእስራኤል ተቋምን ማገዱን ይፋ አድርጓል። ፌስቡክ ሀሰተኛ ናቸው ያላቸው ገጾች በተለያዩ ሀገሮች ስለሚካሄዱ ምርጫዎችና ስለሌሎችም ፖለቲካዊ ጉዳዮች መረጃ የሚሰራጭባቸው ነበሩ ተብሏል። • ፌስቡክ የሞቱ ሰዎችን ገፅ ለማስተዳደር አዲስ አሰራር ቀየሰ ፌስቡክ ያስወገዳቸው 265 ገጾች መነሻቸው እስራኤል ሲሆን፤ በሴኔጋል፣ በቶጎ፣ በአንጎላ፣ በኒጀር፣ በቱኒዝያ እንዲሁም በላቲን አሜሪካና ደቡብ […]