የአዲስ አበባ ፖሊስን ማን ሊያስተዳድረው ይገባል የሚለው ጉዳይ እያወዛገበ ነው…ሪፖርተር

15 January 2020 ዮሐንስ አንበርብር ‹‹ደመወዝ እንከፍላለን እንጂ እኛ የአዲስ አበባ ፖሊስን አናስተዳድርም›› ምክትል ከንቲባ ታከለ ኡማ ‹‹ለሕዝባችን ደኅንነት ሲባል ከአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ጋር ተቀራርበን እንድንሠራ ሊደረግ ይገባል›› የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጄኔራል እንደሻው ጣሰው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለፌዴራል መንግሥት ተጠሪ በሆነችው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ውስጥ አልፎ አልፎ ለሚያደርገው ቁጥጥር የከተማ አስተዳደሩ አመራሮችን […]
የቀድሞ የኦነግ ጦር መሪ ጃል መሮ ከሕወሃት ጋር እየሠራ ነው?…BBC

በምዕራብ ኦሮሚያ በሚገኙ አራት ዞኖች የስልክ እና ኢንተርኔት አገልግሎት ተቋርጦ እንደሚገኝ ይታወቃል። በአራቱም የወለጋ ዞኖች ማለትም፤ ቄለም ወለጋ፣ ሆሮ ጉዱሩ ወለጋ፣ ምዕራብ ወለጋና ምስራቅ ወለጋ የኢንተርኔት አገልግሎት ሙሉ በሙሉ የተቋረጠ ሲሆን፤ የስልክ አገልግሎት የሌለባቸው ደግሞ ምዕራብ ወለጋና የቄለም ወለጋ ዞኖች ናቸው። የቴሌኮም አገልግሎቶች መቋረጥን አስመልክቶ ከኢትዮ ቴሌኮምም ይሁን ከመንግሥት የተሰጠ በቂ ምላሽ ማግኘት አልተቻለም። ይህ […]
ምርጫውን ነሃሴ 10 የማካሄድ ሃሳብ ቅሬታ ተነሳበት….BBC

የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ የዘንድሮው ምርጫ የድምፅ መስጫ ቀን ነሃሴ 10/2012 እንዲሆን ሃሳብ አቅርቧል። ቦርዱ የድምፅ መስጫ ቀንና ሌሎች ከምርጫ ጋር የተገናኙ ክስተቶች የሚከወኑበትን የጊዜ ሰሌዳ ለውይይት ክፍት አድርጓል። ቦርዱ፤ የፓለቲካ ፓርቲዎች፣ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት አስተያየትና ግብዓት እየሰጡበት የሚገኝ ሲሆን፤ በውይይቱ እየተሳተፉ የሚገኙት ባለድርሻ አካላት ምርጫው በነሃሴ ወር እንዲካሄድ መታቀዱ ትክክል አይደለም […]
’’ኢህአዲግ እንደማያሸንፍ በእናንተ ስም ቃል ገብቼ ነው የመጣሁት.’’…የእስክንድር ነጋ የአቀባበል ፕሮግራም

2020-01-10
ለሰላሳ አመታት የታገልንለት ለውጥ ኢህአዴግን በህዝብ ድምጽ ከስልጣን በማሰናበት ፍሬ አፍርቶ እናያለን!!!! (የአዲስ አበባ ባለ አደራ ምክር ቤት – D.W)

2020-01-10 ለሰላሳ አመታት የታገልንለት ለውጥ ኢህአዴግን በህዝብ ድምጽ ከስልጣን በማሰናበት ፍሬ አፍርቶ እናያለን!!! D.W ሠለሞን ሙጬ የአዲስ አበባ ባለ አደራ ምክር ቤት በቀጣዩ ምርጫ እጩዎቹ በአዲስ አበባ የሚሳተፉ ቢሆንም ፣ከአዲስ አበባ ውጪ ከሚንቀሳቀሱ ሃገር አቀፍ የፖለቲካ ድርጅቶች ጋር ተጣምሮ ሃገራዊ አማራጭ የሚሆን ጥምረት እና ቅንጅት ይዞ ምርጫውን በሙሉ ልብ እና ሃይል እንደሚገባበት አስታውቋል። የምክር ቤቱ […]
መንግሥት በአማራ ተማሪዎች ላይ ለሚደረገው ጥቃት የሚያሳየውን ቸልተኝነት የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) ያወግዛል!

2020-01-10 መንግሥት በአማራ ተማሪዎች ላይ ለሚደረገው ጥቃት የሚያሳየውን ቸልተኝነት የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) ያወግዛል! *** በተለያዩ የአገራችን ዩኒቨርስቲዎች በተለይም በኦሮሚያ ክልል ባሉ ዩኒቨርስቲዎች በሚማሩ የአማራ ተማሪዎች ላይ የሚደርሱ ሁሉን አቀፍ ጥቃቶች በጊዜ እንዲታረሙ ንቅናቄያችን በተለያየ ጊዜ መንግሥትን ሲያሳስብና ስለችግሩ ግዝፈትም በተለያዩ መንገዶች ለሕዝብ ሲገልፅ መቆየቱ ይታወሳል፡፡ ይሄ ማንነታቸውን መሰረት አድርጎ በተለይ በኦሮሚያ ክልል ባሉ ዩኒቨርስቲዎች […]
እነ አሕመዲን ጀበል ለመንጋቸው ከማይነግሯቸው የቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ታሪካዊ እውነቶች መካከል!!! [ክፍል ፫ አቻምየለህ ታምሩ]

2020-01-10 እነ አሕመዲን ጀበል ለመንጋቸው ከማይነግሯቸው የቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ታሪካዊ እውነቶች መካከል!!! ክፍል ፫ አቻምየለህ ታምሩ ባለፉት ክፍሎች ባቀረብናቸው ታሪኮች እነ አሕመዲን ጀበል ለመንጋቸው ከማይነግሯቸው የቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ እውነታዎች መካከል በመንበረ ዳዊት የተቀመጡ፣ በሃይማኖታቸው ክርስቲያንና የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን የበላይ ጠባቂ የሆኑት ንጉሠ ነገሥት መስጂድ በገንዘባቸው ያሰሩ፣ ሙስሊም ዜጎቻቸው በቋንቋቸው ሃይማኖታቸውን እንዲማሩ ቁርኣንን በገንዘባቸው ከአረብኛ ወደ […]
የአዲስ አበባ ባለ አደራ ምክር ቤት ከሌሎች ሐገር አቀፍ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር ሐገራዊ አማራጭ የሚሆን ጥምረት ወይም ቅንጅት ይመሰርታል ተባለ

January 11, 2020 Source: https://mereja.com/amharic/v2/198127https://radiodownloaddw-a.akamaihd.net/Events/dwelle/dira/mp3/amh/318511A2_2_dwdownload.mp3 DW : የአዲስ አበባ ባለ አደራ ምክር ቤት ወደ ፖለቲካ ፓርቲነት በይፋ መለወጡን የምክር ቤቱ ሰብሳቢ እስክንድር ነጋ አስታወቁ።አቶ እስክንድር ነጋ እንዳስታወቁት አምና መጋቢት የተመሠረተዉ ምክር ቤት የፊታችን ሰኞ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የፓርቲነት እዉቅ እንዲሰጠዉ ይጠይቃል። አቶ እስክንድር ለጋዜጠኞች እንደነገሩት ፓርቲያቸዉ በሚቀጥለዉ ምርጫ አዲስ አበባ ዉስጥ የሚወዳደሩ ዕጩዎችን ያቀርባል፤ ከሌሎች […]
ህወሓት፣ ባይቶና እና ሳልሳይ ወያነ አረናንና ሌሎች የትግራይ ፓርቲዎችን ያላካተተ ፎረም መሰረቱ

January 11, 2020 Source: https://mereja.com/amharic/v2/198131https://radiodownloaddw-a.akamaihd.net/Events/dwelle/dira/mp3/amh/01FE4931_2_dwdownload.mp3 DW : በትግራይ የሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ ሲቪክ ተቋማት፣ የሙያ ማሕበራትና ሌሎች ድርጅቶችን ያቀፈ «የትግራይ ፓርቲዎችና ማሕበራት ፎረም» የተሰኘ የዉይይት መድረክ ተመሰረተ፡፡ በትግራይ ‘የጋራ አጀንዳዎች ‘ ላይ ይሰራል የተባለው መድረክ 3 የፖለቲካ ፓርቲዎችን ጨምሮ 16 ማሕበራትን ያቀፈ ነው፡፡ ከፖለቲካ ፓርቲዎች፣- የትግራይ ገዢ ፓርቲ ህወሓት፣ተቃዋሚዎቹ ባይቶና እና ሳልሳይ ወያነ ትግራይ የስብስቡ አባላት […]
በወለጋ ደምቢዶሎ የታገቱት ተማሪዎች ጉዳይ አነጋጋሪ ሆኗል

January 11, 2020 Source: https://mereja.com/amharic/v2/198122https://radiodownloaddw-a.akamaihd.net/Events/dwelle/dira/mp3/amh/5C3275B9_2_dwdownload.mp3 DW : ቄለም ወለጋ ዞን የዶምቢዶሎ ዩኒቨርሲቲ መሆናቸው የተገለጸ ተማሪዎች መታገታቸው እየተነገረ ነው። ዩኒቨርሲቲው መረጃው እንደደረሰው እና ጉዳዩ ለሚመለከታቸው የፀጥታ እና የትምህርት ዘርፍ አካላት ማሳወቁን ለዶቼ ቬለ ገልጿል። የሳይንስ እና የከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴርም ጉዳዩን እየተከታተልኩ ነው ብሏል። ታገቱ የተባለው የደምቢዶሎ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ቁጥር በውል የታወቀ አይመስልም። ገሚሱ 17 ፤ ሌላው […]