ኮቪድ19 – ክትባት ለወራት ላይደርስ ይችላል

ለመጨረሻ ጊዜ የታደሰ መስከረም 05, 2020 ቪኦኤ ዜና ኢትዮጵያ ውስጥ ይህ ዘገባ እስከተጠናቀረ ባለፉት ሃያ አራት ሰዓታት ውስጥ ዘጠኝ መቶ ሃምሣ ሰው ለኮሮናቫይረስ መጋለጡ መረጋገጡን የጤና ሚኒስቴር ባወጣው የክትትል ሪፖርት አስታውቋል። አዲስ አበባ፤ ዋሺንግተን ዲሲ፤ ጄኔቫ —  ኢትዮጵያ ውስጥ ይህ ዘገባ እስከተጠናቀረ ባለፉት ሃያ አራት ሰዓታት ውስጥ ዘጠኝ መቶ ሃምሣ ሰው ለኮሮናቫይረስ መጋለጡ መረጋገጡን የጤና […]

የፌዴሬሽን ምክር ቤት ስለ ትግራይ ምርጫ

September 5, 2020 – VOA Amharic ለመጨረሻ ጊዜ የታደሰ መስከረም 05, 2020 መለስካቸው አምሃ ሙሉጌታ አጽብሃ የትግራይ ብሄራዊ ክልላዊ መንግሥት፣ የሥራ አስፈፃሚ አካላትና የምርጫ ኮሚሽን ምርጫን በሚመለከት ያወጣው የምርጫ አዋጅ፣ ያሳለፏቸው ውሣኔዎችና የፈፀሟቸው ተግባራት “ከህገመንግሥቱ ጋር የሚቃረኑ” መሆናቸውን የፌዴሬሽን ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው አስቸኳይ ጉባዔ በየነ። አዲስ አበባ፤ መቀሌ — የትግራይ ብሄራዊ ክልላዊ መንግሥት፣ የሥራ አስፈፃሚ […]

በሀገሪቱ ያለው እውነታ ኢትዮጵያዊነት ጠፍቷል፤ ዘረኝነት ነግሷል በሚባል ደረጃ የሚሰላ አይደለም – አቶ አንዷለም አራጌ

September 5, 2020 “የኢትዮጵያዊነት አስተሳሰብ አሁን ላይ ፀጥ እንዳለ ባህር ሆኗል” – አቶ አንዷለም አራጌ የኢዜማ ምክትል ሊቀመንበር – (ኢፕድ) — የኢትዮጵያዊነት አስተሳሰብ አሁን ላይ ፀጥ እንዳለ ባህር ይምሰል እንጂ በሀገሪቱ ያለው እውነታ ኢትዮጵያዊነት ጠፍቷል፤ ዘረኝነት ነግሷል በሚባል ደረጃ የሚሰላ እንዳልሆነ የኢዜማ ምክትል ሊቀመንበር አቶ አንዷለም አራጌ አመለከቱ።የኢዜማ ምክትል ሊቀመንበር አቶ አንዷለም ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ […]

ኮሮናቫይረስ፡ የሩሲያ የኮቪድ-19 ክትባት በሽታ የመከላከል አቅምን ከፍ ያደርጋል ተባለ – ቢቢሲ / አማርኛ

5 መስከረም 2020 የሩሲያ ሳይንቲስቶች ለኮሮረናቫይረስ በተሰራው ክትባት ዙሪያ የመጀመሪያ ሪፖርታቸውን አቅርበዋል። በክትባቱ ላይ የተደረጉ ምርምሮችን መሠረት በማደረግ ክትባቱ የሰዎችን የበሽታ የመከላከል አቅምን ከፍ እንደሚያደርግ ደርሰንበታል ብለዋል ተመራማሪዎቹ። ሪፖርቱ ዘ ላንሴት በተሰኘው ሜዲካል ጆርናል ላይ ነው የወጣው። በሪፖርቱ ላይም ሁሉም የጥናቱ ተሳታፊዎች ክትባቱ ከተሰጣቸው በኋላ ቫይረሱን ለመዋጋት የሚያስችላቸው አንቲቦዲ ማዳበራቸውን እና የከፋ የጎንዮሽ ጉዳት እንዳልታየባቸው […]

አዲስ አበባ ወደ ራስ ገዝ አስተዳደርነት እንድታድግ ባልደራስ ትግሉን ከፍ ወዳለ ምእራፍ አሳደገ

September 5, 2020 – Konjit Sitotaw ዜና ባልደራስ! – አዲስ አበባ ወደ ራስ ገዝ አስተዳደርነት እንድታድግ ባልደራስ ትግሉን ከፍ ወዳለ ምእራፍ አሳደገ! – አዲስ አበባ ራስ ገዝ ( ክልል በአሁኑ አጠራር) እንድትሆን ባልደራስ በፕሮግራሙ ላይ አስቀምጦ እየታገለ መሆኑ ይታወቃል:: ይህንን ዓላማውን ተግባራዊ ለማድረግ ስራ አስፈፃሚው አንድ ግብረ ሃይል በማቋቋም እንቅስቃሴዎች እንዲጀመሩ ወስኗል። – ዝርዝር ጉዳዮችን […]

ትግራይ ፡ ምርጫው “እንዳልተደረገ የሚቆጠር፣ የማይጸናና ተፈጻሚነት የሌለው ነው” የፌዴሬሽን ምክር ቤት – ቢቢሲ / አማርኛ

5 መስከረም 2020, 18:03 EAT በትግራይ ክልል በመጪው ረቡዕ ሊካሄድ የታቀደው ምርጫ ከአገሪቱ ሕገ መንግሥት ጋር የሚቃረን በመሆኑ “እንዳልተደረገ የሚቆጠር፣ የማይጸናና ተፈጻሚነት የሌለው ነው” ሲል የፌዴሬሽን ምክር ቤት በሙሉ ድምጽ መወሰኑ ተገለጸ። ምክር ቤቱ ዛሬ [ቅዳሜ] ባደረገው አስቸኳይ ስብሰባው ላይ በትግራይ ክልል የሚካሄደውን የምርጫ እንቅስቃሴን በተመለከተ የሕገ መንግሥት ትርጉምና የማንነት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ባቀረበለት የውሳኔ […]

ስድስት የኮንግረስ አባላት ለኢትዮጵያ የሚደረገው ድጋፍ መቋረጡን ተቃወሙ – ቢቢሲ / አማርኛ

5 መስከረም 2020, 10:18 EAT ስድስት የአሜሪካ ኮንግረስ አባላት አሜሪካ ለኢትዮጵያ የምታደርገው ድጋፍ እንዲቀነስ መደረጉን በመቃወም ለአሜሪካው የውጪ ጉዳይ ሚንስትር ማይክ ፖምፔዮ እና ለግምጃ ቤት ኃላፊው ስቲቭ ሙንሽን ደብሳቤ ጻፉ። የኮንግረስ አባላቱ በጻፉት ደብዳቤ ላይ “አሜሪካ ለኢትዮጵያ የምታደርገው ድጋፍ እንዲቀነስ መደረጉ እጅጉ አሳስቦናል” ብለዋል። “ይህ የውጪ ድጋፍ እንዲቀነስ መደረጉ ታማኝ ከሆነች አጋራችን ጋር ያለንን ግንኙነት […]

የኢያሪኮ መንገደኛ…!!! (በዲያቆን ብርሃኑ አድማስ)፤

2020-09-05 የኢያሪኮ መንገደኛ…!!! (በዲያቆን ብርሃኑ አድማስ)፤   አቤቱ በእኔ በኵል እለፍ…!        ጌታዬ ሆይ አቤቱ በአዲስ ዘመን ዋዜማ በአጠገቤ እለፍና አንሣኝ፡፡ ዘይትና ወይን ባልካቸው የመሥዋዕት ደምህ ቁስሌን ጥረግልኝ፡፡ ጨርቅ በተባለ ፍቅርህም ግጥም አድረገህ እሰርለኝና ከጥላቻ፣ ከከንቱነት፣ ከግብዝነት፣ ከለፍላፊነት፣ ከኩራትና ከትዕቢት፣ ከዝሙትና ከርኩሰት ቁስሌ ማገገምን ስጠኝ፡፡ በአገልጋይህ በኩል ስበህ የእንግዶች ማደሪያ ወዳልካት ቤትህ አስጠጋኝ፡፡ ጌታዬ […]

ባለፉት 24 ሰዓት 950 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ሲረጋገጥ የ17 ሰዎች ህይወት አልፏል።

September 5, 2020 ባለፉት 24 ሰዓት በተደረገው 24,544 የላብራቶሪ ምርመራ 950 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ሲረጋገጥ የ17 ሰዎች ህይወት አልፏል። በተጨማሪ በትላንትናው ዕለት 164 ሰዎች አገግመዋል። በአጠቃላይ በሀገራችን በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች 57,466 የደረሱ ሲሆን የሟቾች ቁጥር 897 ደርሷል ፤ ከበሽታው ያገገሙ አጠቃላይ ሰዎች ቁጥር ደግሞ 20,776 ደርሷል።