ህወሓት ችግሩን ካልፈታ ፌደራል መንግሥት ክልሉን እንደሚረከብ መግለጹን አቶ ጌታቸው ተናገሩ

November 26, 2024 – VOA Amharic  የህወሓት አመራሮች በውስጣቸው ያለውን በመፍታት ያዋጣል የሚሉትን መንገድ የማያቀርቡ ከኾነ፣ ብልጽግና የክልሉን አስተዳደር ራሱ ሊይዘው እንደሚችል ማሳሰቢያ መስጠቱን፣ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት ጌታቸው ረዳ ተናገሩ። ትላንት እሁድ ለክልሉ ብዙኅን መገናኛ በሰጡት መግለጫ፣ በክልሉ ባለፉት ሦስት ወራት ተኩል ከ28 ኩንታል በላይ ወርቅ ወደ ፌዳራል መንግሥት ገቢ የገለጹት አቶ … … ሙሉውን […]

በደቡብ ሱዳን ከ2 ሚሊዮን በላይ ህጻናት ለከፍተኛ የምግብ እጥረት ተጋልጠዋል

November 26, 2024 – VOA Amharic  በደቡብ ሱዳን 2 ሚሊዮን የሚደርሱ ህጻናት እና 1 ሚሊዮን ነፍሰ ጡር እና የሚያጠቡ እናቶች ለከፋ የምግብ እጦት እየተጋለጡ መሆኑን ገልጾ ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ አስጠንቅቋል። ደካማ የንፁህ የመጠጥ ውሃ አቅርቦት፣ የንፅህና አጠባበቅ እና የበሽታ መስፋፋት ቀውሱን ማባባሱን ቀጥሏል። ሺላ ፖኒ ከጁባ ከደቡብ ሱዳን ያጠናቀረችውን ዘገባ ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ። … … ሙሉውን ለማየት […]

በጀልባ መገልበጥ አደጋ ከ20 በላይ ፍልሰተኞች ማዳጋስካር የባህር ዳርቻ ላይ ሞቱ

November 26, 2024 – VOA Amharic  ፍልሰተኞች የያዙ ሁለት ጀልባዎች ማዳጋስካር ባህር ዳርቻ ላይ ተገልብጠው 24 ፍልሰተኞች ህይወታቸው ማለፉን የሶማሊያ ማስታወቂያ ሚኒስትር ዳውድ አዌይስ አስታወቁ። ከሟቾቹ መካከል አብዛኞቹ ሶማሊያውያን መኾናቸው ተገልጿል፡፡ በሃሩን ማሩፍ የተጠናቀረውን ዘገባ ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ። … … ሙሉውን ለማየት ወይም ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ

ዓለም ለትረምፕ የንግድ ጦርነት ተጽእኖ ዝግጅት ላይ ነው

November 26, 2024 – VOA Amharic  ተመራጩ ፕሬዝደንት ዶናልድ ትረምፕ፣ በተለይም በቻይና ላይ ከፍተኛ ታሪፍ ለመጣል በመዛታቸው ምክንያት፣ በመላው ዓለም የሚገኙ ሃገራት የኢኮኖሚ አለመረጋጋት ሊከተል ይችላል በሚል ስጋት በሚል ዝግጅት ላይ ናቸው። መንግሥታትና የንግድ ድርጅቶች ለሁኔታው በምን መልኩ ምላሽ እንደሚሰጡ ግራ የተጋቡ ይመስላል። የቪኦኤው ቢል ጋሎ ከሶል፣ ደቡብ ኮሪያ ያጠናቀረውን ዘገባ ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ። … … ሙሉውን […]

መስከረም አበራ የአንድ ዓመት ከ4 ወር እስር ተፈረደባት

November 25, 2024 – VOA Amharic  የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ዛሬ በዋለው ችሎት በመስከረም አበራ ላይ የ1 ዓመት ከ4 ወር እስር መፍረዱን ጠበቃዋ ለአሜሪካ ድምፅ ገልጸዋል፡፡ “በኮምፒውተር ተጠቅማ በኅብረተሰብ መካከል አመጽ፣ ሁከት እና ግጭት ለማነሳሳት ሞክራለች” በሚል ጥፋተኛ በተባለችባቸው ሁለት ወንጀሎች እንደተፈረደባት ጠበቃዋ ተናግረዋል። ዛሬ የቅጣት ውሳኔው ከተሰጠበት የክስ መዝገብ ሌላ፣ በአማራ ክልል ካለው የፀ… … ሙሉውን […]

ሦስት የሲቪክ ድርጅቶች ታገዱ

November 25, 2024 – DW Amharic  ከተሰጣቸው ፈቃድ ውጪ ተንቀሳቅሰዋል የተባሉ በሰብአዊ መብት ጥበቃ ዙሪያ ይሠሩ የነበሩ ሦስት የሲቪክ ድርጅቶች ከሥራቸው ታገዱ። በኢትዮጵያ ሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ባለሥልጣን እግድ የተጣለባቸው ድርጅቶች የመብቶች እና ዴሞክራሲ ዕድገት ማዕከል (ካርድ)፣ የሕግ ባለሙያዎች ለሰብአዊ መብቶች እና ስብስብ ለሰብአዊ መብቶች ኢትዮጵያ ናቸው።… … ሙሉውን ለማየት ወይም ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ

አራት የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅት መሪዎች በፀጥታ አካላት ጫና እና ዛቻ መሰደዳቸው ተነገረ

ከ 2 ሰአት በፊት አራት የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅት መሪዎች በመንግሥት የፀጥታ አካላት በደረሰባቸው ዛቻ እና ወከባ ምክንያት ከአገር መሰደዳቸውን ተነገረ። የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ተሟጋቾች ማዕከል ባወጣው መግለቻ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅት መሪዎች በፀጥታ ኃይሎች “ተደጋጋሚ ማስፈራሪያ እና ወከባ” እየደደረሰባቸው እንደሆነ አስታውቋል። በዚህም ሳቢያ በአገሪቱ ያለው የሲቪል ምኅዳር ሊጠብ እና አደጋ ላይ ሊወድቅ እንሚችል ምክልቶች እየተስተዋሉ ነው […]

የሱዳኑ ጄኔራል አልቡርሃን እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትራቸው ጉብኝት በአሥመራ እና በአዲስ አበባ

ከ 3 ሰአት በፊት የሱዳን ሉዓላዊ ምክር ቤት ሊቀመንበር ጄኔራል አብደል ፋታህ አል ቡርሃን ወደ ኤርትራ ሲያቀኑ፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትራቸው አምባሳደር አሊ ዩሴፍ አህመድ አል-ሻሪፍ ደግሞ በኢትዮጵያ ጉብኝት እያደረጉ ነው። ሁለት ዓመት ሊሞላው በተቃረበ ከአገሪቱ ፈጥኖ ደራሽ ኃይል ጋር በሚካሄደው የእርስ በርስ ጦርነት ውስጥ የሚገኘው የሱዳን ጦር ኃይልን የሚመሩት ጄኔራል አል-ቡርሃን ዛሬ ማክሰኞ ረፋድ ላይ […]

ከሀገር የሸሸው የቀድሞው የሩሲያ የኒውክሌር ጣቢያ ጠባቂ ምን ይላል?

ከ 7 ሰአት በፊት በአውሮፓውያኑ የካቲት 20222 ሩሲያ ዩክሬን ላይ ጦርነት ስታውጅ አንቶን የሚያገለግልበት የኒውክሌር ጦር መሣሪያ ጣቢያ በተጠንቀቅ ቆሞ ነበር። “ከዚያ ቀደም ልምምድ ብቻ ነበር የምናደርገው። ነገር ግን ጦርነቱ የተጀመረ ቀን፤ የጦር መሣሪያዎቹ በተጠንቀቅ ቆሙ” ይላል የቀድሞው የሩሲያ የኒውክሌር ኃይል መኮንን። “የጦር መሣሪያዎቹን ወደ ባሕር እና ወደ አየር ለመተኮስ ዝግጁ ነበርን። በመርኅ ደረጃ የኒውክሌር […]

ሰሜን ኮሪያውያን ከዩክሬን ጎን ተሰልፈው ከሩሲያ ጋር መዋጋት ለምን ፈልጉ?

26 ህዳር 2024 በደቡብ ኮሪያ የሚገኙ የሰሜን ኮሪያውያን ኮብላዮች ድፍረት የተሞላበት እና ከዚህ በፊት ታይቶ የማይታውቅ ተልዕኮ ለመወጣት ሐሳብ እያቀረቡ ነው። ሐሳባቸው ከተሳካ የዩክሬንን ጦር በመደገፍ ወደ ግንባር ተጉዘው በሩሲያ በኩል የተሰለፉትን የሰሜን ኮሪያ ወታደሮችን ለማስኮብለል ነው ትኩረታቸው። የሰሜን ኮሪያን ጦር አስተሳሰብ እና አረዳድ በተመለከተ ልዩ ግንዛቤ አለን ይላሉ። ይህ ደግሞ “በክብር” ለመሞት ዝግጁ ሆነው […]