የሱዳን ጦር ካርቱምን ሙሉ በሙሉ መቆጣጠሩን ገለፀ

ከ 5 ሰአት በፊት የሱዳን ጦር ኃይሎች አዛዥ፣ አብደል ፈታህ አል ቡርሃን ጦራቸው በካርቱም የሚገኘውን ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ከፈጥኖ ደራሽ ኃይሉ ካስለቀቀ ከጥቂት ሰዓታት በኋላ “ካርቱም ነጻ ናት” ሲሉ አወጁ። ጄነራል አብዱልፈታህ አል ቡርሃን ጦሩ በካርቱም የሚገኘውን የአገሪቱን ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ከተቆጣጠረ ከጥቂት ሰዓታት በኋላ በስፍራው የደረሱ ሲሆን፣ፕሬዚዳንታዊ ቤተ መንግሥቱንም ጎብኝተዋል። ፕሬዝዳንቱ በስፍራው […]

የደቡብ ሱዳን ምክትል ፕሬዝዳንት ሪክ ማቻር በቁም እስር ላይ መሆናቸውን ፓርቲያቸው አስታወቀ

ከ 43 ደቂቃዎች በፊት የደቡብ ሱዳን ፕሬዝዳንት ሳልቫ ኪር የረጅም ጊዜ ተቀናቃኝ የሆኑት የአገሪቱ ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዝዳንት ሪክ ማቻር በቁም እስር ላይ እንደሚገኙ ፓርቲያቸው አስታወቀ። በአገሪቱ የመከላከያ ሚኒስትር እና ከፍተኛ የደህነት ኃላፊዎች የተመራ ቡድን ትናንት ረቡዕ በዋና ከተማዋ ጁባ ወደሚገኘው የሪክ ማቻር መኖሪያ ቤት መግባቱን እና የምክትል ፕሬዝዳንቱን ጠባቂዎች ትጥቅ ማስፈታቱን ተቃዋሚው የሱዳን ሕዝቦች ነጻነት […]

በደብረፅዮን የሚመራው የህወሓት ክንፍ፤ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የእጩ ጥቆማ ጥሪ “የፕሪቶሪያውን ስምምነት የሚጥስ” ነው አለ

ከ 2 ሰአት በፊት በዶ/ር ደብረፅዮን ገብረሚካኤል የሚመራው የህወሓት ክንፍ፤ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ለትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት መረጣ ያቀረቡትን የእጩ ጥቆማ ጥሪ፤ “የፕሪቶሪያውን ስምምነት የሚጥስ አካሄድ” እንደሆነ በመግለጽ ተቃወመ። የፌደራል መንግሥት “የትግራይን ህልውና የሚፈታተኑ ሁካታ እና ግጭትን የሚፈጥሩ ስራዎችን” እያከናወነ ነው ሲልም ከስሷል። ክንፉ፤ ትናንት ረቡዕ መጋቢት 17/2017 ዓ.ም. ምሽት ባወጣው መግለጫ፤ የኢትዮጵያ […]

ቻይና በቲክቶክ ሽያጭ ላይ እንድትስማማ አሜሪካ የታሪፍ ቅናሽ ልታደርግ እንደምትችል ትራምፕ ተናገሩ

ከ 3 ሰአት በፊት የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በባይትዳንሰ ባለቤትነት የተያዘው ቲክቶክን ለመሸጥ ከስምምነት ለመድረስ ለቻይና የታሪፍ ቅናሽ ሊያደርጉ እንደሚችሉ ተናገሩ። ትራምፕ ቻይናዊ ያልሆኑ ገዢዎችን ለማግኘት በሚል መጋቢት 27 2017 ዓ.ም. ድረስ ተቀምጦ የነበረውን ቀነ ገደብ ለማራዘም ፈቃደኛ መሆናቸውንም ተናግረዋል። ፕሬዝደንቱ ወደ ስልጣን እንደመጡ በጆ ባይደን አስተዳደር ቲክቶክን ለማገድ ወጥቶ የነበረው ሕግ ተግባራዊነቱ እንዲዘገይ አድርገው […]

ዜሌንስኪ ለሩሲያ ቅድመ ሁኔታ አሜሪካ ‘ጠንካራ ምላሽ’ እንደምትሰጥ ተስፋ እንዳላቸው ገለፁ

ከ 3 ሰአት በፊት ፕሬዝደንት ቮሎዲሚር ዜሌንስኪ ሩሲያ በጥቁር ባሕር ላይ የተደረሰውን የተኩስ አቁም ስምምነት ለማክበር ማዕቀብ ይነሳልኝ ስትል ያቀረበችውን ቅድመ ሁኔታ በመቃወም፣ አሜሪካ በእነዚህ ፍላጎቶች ፊት “ጠንካራ ሆና ትቆማለች” የሚል እምነት እንዳላቸው ተናገሩ። ሞስኮው የንግድ መርከቦች ደህንነቱ የተጠበቀ እንቅስቃሴን እንዲያደርጉ ለመፍቀድ ማክሰኞ ዕለት የተደረሰው የባሕር ላይ ስምምነት ተግባራዊ የሚሆነው የምዕራቡ ዓለም በሩሲያ የምግብ እና […]

የማጭበርበር ወንጀል ከሚፈጸምባቸው ካምፖች ጋር በተያያዘ እና ለቻይና በመሰለል የተወነጀለችው ከንቲባ

ከ 5 ሰአት በፊት እአአ በ 2022 መጀመሪያ ላይ ከማኒላ በስተሰሜን በምትገኘው ባምባን የፊሊፒንስ የገጠር ከተማ ነዋሪዎች አሊስ ሌል ጉኦ ለተባለች ወጣት ሴት ለከንቲባነት ለምታደርገው የምረጡኝ ዘመቻ ተሰብስበዋል። ደጋፊዎቿ ለምርጫ ቅስቀሳ የምትጠቀምበትን ሮዝ ቀለም ያለው ልብስ ለብሰው መምጣትዋን በጉጉት ይጠባበቃሉ። ከዚያም ጉኦን የጫነው ሂሊኮፕተር በአካባቢው ሲደርስ ደጋፊዎቿ ስሟን እየጠሩ በጋራ የድጋፍ ድምጻቸውን አሰሙ። የ31 ዓመቷ […]

ፖላንድ የስደተኞች ጥገኝነት የመጠየቅ መብትን ልታግድ ነው

ከ 5 ሰአት በፊት የፖላንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶናልድ ቱስክ መንግሥታቸው በቤላሩስ ድንበር በኩል ወደ ፖላንድ የሚገቡ ስደተኞችን ጥገኝነት የመጠየቅ መብት ለጊዜው እንደሚያግድ ገለፁ። ቱስክ ይህን ያስታወቁት የፖላንድ ባለስልጣናት ጥገኝነት የመጠየቅ መብትን እስከ 60 ቀናት ድረስ እንዲያግዱ የሚፈቅደው አወዛጋቢ ሕግ በፕሬዚደንት አንድርዜጅ ዱዳ ከተፈረመ በኋላ ነው። ጠቅላይ ሚኒስትር ቱስክ መንግሥታቸው ሕጉን “ያለ ምንም መዘግየት” እንደሚያፀድቅ ሲናገሩ፣ […]