በወጣቷ ላይ የደረሰው ሰቆቃ በቅርብ ጊዜያት በአገራችን ለተፈጸሙ ግፎች በቂ ማሳያ ነው! – መኢአድ፣ ኢሕአፓ፣ ዐማራ ግዮናዊ ንቅናቄና እናት ፓርቲ

ለግፏአን በወቅቱ ድምጽ መሆን እጅግ አስፈላጊም ተገቢም ነው ኢሕአፓ/eprp  በወጣቷ ላይ የደረሰው ሰቆቃ በቅርብ ጊዜያት በአገራችን ለተፈጸሙ ግፎች በቂ ማሳያ ነው! *በወቅታዊ ጉዳይ ላይ ከመኢአድ፣ ኢሕአፓ፣ ዐማራ ግዮናዊ ንቅናቄና እናት ፓርቲ የተሰጠ መግለጫ* ከምትማርበት ዩኒቨርስቲ ከዓመታት በፊት ከሌሎች ጓደኞቿ ጋር ታፍና ተወስዳ እጅግ አሰቃቂ በደል ከደረሰባቸው አንዷ እንደሆነች የገለጸችው ወጣት ብርትኳን ተመስገን የደረሰባትን ግፍና አኹን […]

ፕሮፌሰር ኤልሳቤጥ ወልደጊዮርጊስ፡ የኢትዮጵያ ዘመናዊ ሥነ-ጥበብ ጥናት አድባር

የጽሁፉ መረጃ የኢትዮጵያ ጥናት እና ምርምር መርከብ ቢሆን ካፒቴኗ ፕሮፌሰር ኤልሳቤጥ ወልደ ጊዮርጊስ ይሆናሉ። ፕ/ር ኤልሳቤጥ በኢትዮጵያ ዘመናዊ ስነ ጥበብ እና ኪነ ጥበብ ሂስ አንቱታን አትርፈዋል። ወዳጆቻቸው እና ጓደኞቻቸውን ጨምሮ ብዙዎች ፕ/ር ኤልሳቤጥን ‘አንቺ’ ስለሚሏቸው እኛም በዛው እንቀጥል። “ወንዳዊ፣ ሰሜናዊ እና ተዋረዳዊ የኃይል ግንኙነት (hierarchical power relation) ላይ የተመሰረተ” የምትለውን እና ብዙዎች ያለ ጥያቄ እና […]

ለትግራይ ከሌሎች ክልሎች “በተለየ ሁኔታ” ላለፉት 11 ቀናት ነዳጅ እንዳይጫን መደረጉ ተገለጸ

ከ 59 ደቂቃዎች በፊት የትግራይ ክልል ንግድ እና ኤክስፖርት ቢሮ ላለፉት 11 ቀናት ከሌሎች ክልሎች “በተለየ ሁኔታ” ወደ ትግራይ ክልል ነዳጅ ምንም አይነት ነዳጅ አለመጫኑን ገለጸ። የኢትዮጵያ ነዳጅ አቅራቢ ድርጅት ለሁሉም ክልሎች የሚያጋራው የነዳጅ ስርጭት መረጃ፤ የነዳጅ አቅርቦት ሙሉ ለሙሉ የቆመው “በትግራይ ክልል ብቻ” እንደሆነ እንደሚያመለክት በቢሮው የሸማቾች ጥበቃ ዳይሬክተር አቶ ካሳሁን ክንደያ ለቢቢሲ ተናግረዋል። […]

ጠ/ሚ ዐቢይ ለሚሾሙት ጊዜያዊ ፕሬዚዳንት የትግራይ ህዝብ ዕጩዎችን እንዲጠቁም ጥሪ አቀረቡ

ከ 3 ሰአት በፊት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ እርሳቸው ለሚሾሙት ጊዜያዊ የትግራይ ክልል ፕሬዚዳንት የክልሉ ህዝብ ዕጩዎችን እንዲጠቁማቸው ረቡዕ፣ መጋቢት 17/ 2017 ዓ.ም በኤክስ ገፃቸው ጥሪ አቀረቡ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሁለት ዓመት ቆይታው የተጠናቀቀው የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ለቀጣዩ አንድ ዓመት እንደሚቀጥል እና “በግለሰቦች ረገድ ለውጥ ሊደረግ እንደሚችል” በቅርቡ ለፓርላማው ማብራሪያ ከሰጡ በኋላ ነው ይህንን የፕሬዚዳንት […]

የሱዳን ጦር በዳርፉር ገበያ ላይ ባደረሰው ጥቃት በመቶዎች መገደላቸው ተነገረ

ከ 4 ሰአት በፊት የሱዳን ጦር በአገሪቱ ምዕራባዊ ዳርፉር ግዛት በገበያ ላይ ባደረሰው ጥቃት በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች መግደሉን በሱዳን ጦርነት የሚፈጸሙ ጥሰቶችን የሚከታተል ቡድን አስታወቀ። ቱራህ ገበያ ላይ የተፈጸመው የቦምብ ጥቃት “አሰቃቂ ጭፍጨፋ ነው” ሲል በሱዳን ጦርነት በሁለቱ ተፋላሚዎች እየደረሰ ያለውን ጥሰት እየሰነደ ያለው የአስቸኳይ ጊዜ የጠበቆች ቡድን ገልጿል። በዚህ ጥቃት ከሞቱት በተጨማሪ በመቶዎች የሚቆጠሩ […]

ሩሲያ እና ዩክሬን ጥቁር ባሕር ላይ የተኩስ አቁም ለማድረግ ተስማሙ

ከ 6 ሰአት በፊት ሩሲያ እና ዩክሬን ጥቁር ባሕር ላይ የሚያደርጉትን ጦርነት የሚያስቆም የተኩስ አቁም ስምምነት ፈርመዋል። ሀገራቱ ሳዑዲ አራቢያ ውስጥ በየግላቸው ከዩናይትድ ስቴትስ ጋር ባደረጉት ስምምነት ነው የተኩስ አቁም ለማድረግ የወሰኑት። ዋሺንግተን ስምምነቱን አስመልክቶ ባወጣው መግለጫ ሁሉም ወገኖች “አስተማማኝ እና ዘላቂ ሰላም ለማምጣት” ይሠራሉ፤ አስፈላጊ የሆነው የንግድ መተላለፊያም ይከፈታል ብሏል። ዋይት ሐውስ በመግለጫው ሁለቱ […]

አብዛኞቹ ነዋሪዎቿ ዩቲዩበር የሆኑባት መንደር

ከ 8 ሰአት በፊት ቱልሲ በሕንድ የምትገኝ መንደር ናት። ነዋሪዎቿ በአብዛኛው ዩቲዩበር ሆነዋል። የ32 ዓመቱ ጃቪ ቨርማ ከነዋሪዎቹ አንዱ ነው። በሕንድ ባህላዊ ልብስ ሳሪ የተዋቡ ሴቶችን ቪድዮ ይቀርጻል። አንድ አዛውንት በወጣቶቹ መካከል ተቀምጠዋል። ከወጣቶቹ አንዷ የአዛውንቷን እግር ትነካለች። ሌላዋ ውሃ ታቀርብላቸዋለች። ጃቪ ሥራውን ይወደዋል። የሚቀርጻቸው ሴቶችም ደስተኛ ናቸው። ዩቲዮብ ላይ ቪድዮዎቹ ተወዳጅነት እያገኙ ነው። ከጃቪ […]

አውሮፓ ውስጥ ለሩስያ ሲሰልሉ የነበሩ ሁለት ሴቶችን ቢቢሲ በምርመራ አጋለጠ

ከ 8 ሰአት በፊት በዜግነት ቡልጋሪያዊ ናቸው። ስቪትላና ጌኔችቫ እና ትስቬታንካ ዶንቼቫ ይባላሉ። የሩስያ የስለላ ሕዋስ አባል ሆነው ከዩናይትድ ኪንግደም ይሠሩ እንደነበር የቢቢሲ ምርመራ አጋልጧል። ሁለቱም ሴቶች ከቢቢሲ አስተያየት እንዲሰጡ ተጠይቀው ምላሽ አልሰጡም። ስቪትላና አየር መንገድ ውስጥ ነው የምትሠራው። ቢቢሲ ስልክ ሲደውልላት ስልኩን ዘግታዋለች። ደብዳቤ ሲላክላት አስተያየት መስጠት አልፈልግም ብላለች። ትስቬታንካ ኦስትሪያ፣ ቬየና ያለ ቤቷ […]

ትራምፕ እና የደኅንነት ተቋማት ኃላፊዎቻቸው ምስጢራዊ መረጃ በሲግናል ተልኳል መባሉን አጣጣሉ

ከ 5 ሰአት በፊት የአሜሪካው ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ እና የደኅንነት ተቋማት ኃላፊዎቻቸው ሲግናል በተባለው የመልዕክት መላላኪያ አማካይነት ምስጢራዊ መረጃ ተልኳል መባሉን አጣጥለዋል። አንድ ጋዜጠኛ የደኅንነት ኃላፊዎች የሚነጋገሩበት ቡድን ውስጥ መግባቱ የደኅንነት ስጋት እንዳልሆነ ባለሥልጣናቱ ተናግረዋል። ዘ አትላንቲክ የተባለው መፅሔት ዋና አርታኢ የአሜሪካ ከፍተኛ የደኅንነት ባለሥልጣናት የሚነጋገሩበት የሲግናል ግሩፕ ውስጥ ገብቶ መረጃ መስማቱን ተከትሎ የትራምፕ አስተዳደር […]

በፍልስጤም ድጋፏ ከአሜሪካ ትባረራለች የተባለችው የኮለምቢያ ዩኒቨርስቲ ተማሪ ትራምፕን ከሰሰች

ከ 5 ሰአት በፊት ገና በሰባት ዓመቷ ወደ አሜሪካ የመጣችው እና በፍልስጤም የድጋፍ ሰልፍ ላይ በመሳተፏ ከአገር ለማባረር ባለስልጣናቱ ሞክረዋል ያለችው የኮለምቢያ ዩኒቨርስቲ ተማሪ የትራምፕን አስተዳደር ከሰሰች። በአሜሪካ ቋሚ ነዋሪ የሆነችው የደቡብ ኮሪያዋ ተወላጅ የ21 ዓመቷ ዩንሴኦ ቹንግ የኢሚግሬሸን ባለስልጣናት የመኝታ ክፍሏን ጨምሮ በተለያዩ የኮለምቢያ ተቋማት ፍተሻ አካሂደዋል ብላለች። ተማሪዋ በትራምፕ አስተዳደር ላይ ያቀረበችው ክስ […]