የምርጫ 97 ትውስታ!

ተሟገት የምርጫ 97 ትውስታ! ቀን: June 2, 2024 (ክፍል ሁለት) በበቀለ ሹሜ የመጨረሻው የዋንጫ ግጥሚያ የቅንጅትና የኅብረቱ በድምፅ ለመታጋገዝና የትብብር/ጥምር መንግሥት ለመመሥረት መስማማት ለኢሕአዴግ ሌላ ራስ ምታት ነበር፡፡ በተቃዋሚዎቹ የሥልጣን እሽቅድምድም ለመጠቀም የነበረውን ቀዳዳ የሚዘጋ ሆነ፡፡ ይህን መበለጥ ለማካካስ፣ አፈናና እስራቱን እንደ ልብ አይለቀቅበት ነገር ሕዝብ በየአካባቢው በርትቷል፡፡ የአሜሪካ መንግሥት የምርጫውን ዴሞክራሲያዊነት ተቃዋሚዎች በሚያገኙት ወንበር […]

ወላጆች ከጤና ተቋም ውጪ የሚወለዱ ሕፃናትን ለሲቪል ምዝገባ እንዲያሳውቁ የሚያስገድድ ረቂቅ ሕግ ተዘጋጀ

ማኅበራዊ ወላጆች ከጤና ተቋም ውጪ የሚወለዱ ሕፃናትን ለሲቪል ምዝገባ እንዲያሳውቁ የሚያስገድድ ረቂቅ ሕግ… ሲሳይ ሳህሉ ቀን: June 2, 2024 ከጤና ተቋም ውጪ የሚወለዱ ሕፃናትን ወላጆች ለሲቪል ምዝገባ ጽሕፈት ቤት እንዲያስታውቁ የሚያስገድድ ሕግ ለፓርላማ ቀረበ፡፡ በዝቅተኛው እርከን ላይ ያለው የመዋቅር ወይም የጤና ባለሙያ አግባብ ያላቸውን መረጃዎች የያዘ ቅጽ ሞልቶ፣ ውልደቱ የተከሰተበት ቦታ ለሚገኝ የሲቪል ምዝገባ አስተዳደር […]

ፕላንና ልማት ሚኒስቴርንና ተጠሪ ተቋማትን ለሙስና የሚያጋልጡ ክፍተቶች ይፋ ተደረጉ

የሙስና ሥጋት ተጋላጭነት ጥናት ይፋ በተደረገበት ወቅት ዜና ፕላንና ልማት ሚኒስቴርንና ተጠሪ ተቋማትን ለሙስና የሚያጋልጡ ክፍተቶች ይፋ ተደረ ሲሳይ ሳህሉ ቀን: June 2, 2024 የሥነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን በፕላንና ልማት ሚኒስቴርና በሚቆጣጠራቸው ተቋማት ውስጥ፣ ለሙስና ተጋላጭ የሚያደርጉ የአሠራር ክፍተቶችና ከሕግ ውጪ የሚደረጉ በርካታ የሕግ ጥሰቶችን ይፋ አደረገ፡፡ ኮሚሽኑ የፕላንና ልማት ሚኒስቴርና በውስጡ ያሉ የዘርፍ […]

ጥናት ሳይደረግ የተገነባው የያዩ ማዳበሪያ ፕሮጀክት የአገር ሀብት እንደባከነበት ተገለጸ

የማዕድን ሚኒስትሩ ሀብታሙ ተገኝ (ኢንጂነር) ዜና ጥናት ሳይደረግ የተገነባው የያዩ ማዳበሪያ ፕሮጀክት የአገር ሀብት እንደባከነበት ተገለጸ ፅዮን ታደሰ ቀን: June 2, 2024 በኦሮሚያ ክልል ኢሉባቦር ዞን ውስጥ ተገንብቶ የነበረው ያዩ የማዳበሪያ ፕሮጀክት ለፋብሪካው የሚሆን በቂ ሀብት መኖሩ ጥናት ሳይደረግበት ግንባታው በመጀመሩ፣ የአገር ሀብት እንደባከነበት ተገለጸ፡፡  የማዕድን ሚኒስቴር የዘጠኝ ወራት ዕቅድ አፈጻጸም ግንቦት 22 ቀን 2016 […]

‹‹በሁለት ጦር መካከል ተቀስፎ ያለ ተቋም ቢኖር አገራዊ የምክክር ኮሚሽን ነው›› አቶ ዘገየ አስፋው፣ የአገራዊ የምክክር ኮሚሽን ኮሚሽነር

ናርዶስ ዮሴፍ June 2, 2024 ቆይታ በኢትዮጵያ ሰሜናዊ ክፍል የተነሳው ግጭት በተጋጋለበት ወቅት በ2014 ዓ.ም. በአገሪቱ መሠረታዊ በሆኑ ጉዳዮች ላይ ለተፈጠሩ ልዩነቶችና አለመግባባቶች ወሳኝ ምክንያቶችን በጥናትና በሕዝባዊ ውይይቶች በመሰብሰብ፣ በተለዩ አጀንዳዎች ላይ አገራዊ ምክሮችን በማካሄድ፣ ምክረ ሐሳቦችን በማቅረብና ለተግባራዊነቱም የመከታተያ ሥርዓት በመዘርጋት ለአገራዊ መግባባት ምቹ ሁኔታ መፍጠር በተቋቋመው አገራዊ የምክክር ኮሚሽን ከተሾሙት 11 ኮሚሽነር መካከል አንዱ አቶ ዘገየ አስፋው ናቸው። በሕግ የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ፣ እንዲሁም የማስተርስ ዲግሪያቸውን በሕግ በአሜሪካ ከሚገኘው ከዊስኮንሲ ሜዲሲን ዩኒቨርሲቲ አግኝተዋል፡፡ አቶ ዘገየ በሙያቸው ጠበቃ ሲሆኑ፣ ከቀዳማዊ አፄ ኃይለ ሥላሴ ዘመን አንስቶ […]