ሰላማዊ ሰልፍ በማስተባበራቸው በአዋሽ አርባ ታስረው ከቆዩ እስረኞች የተወሰኑት ወደ አዲስ አበባ ተዘዋወሩ – ኢትዮጵያ ኢንሳይደር)

June 9, 2024 በሙሉጌታ በላይ ባለፈው ህዳር ወር መጨረሻ በአዲስ አበባ ከተማ ሊካሄድ የነበረን ሰላማዊ ሰልፍ ሲያስተባብሩ ከነበሩ ግለሰቦች መካከል አራቱ፤ ለሁለት ወር ገደማ በእስር ላይ ከቆዩበት ከአዋሽ አርባ ወታደራዊ ካምፕ ከትላንት በስቲያ አርብ አመሻሽ ወደ አዲስ አበባ መዘዋወራቸውን ምንጮች ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ገለጹ። ከሰልፉ አስተባባሪዎች አንዱ የነበሩት እና ላለፈው አንድ ሳምንት በአዲስ አበባ ፖሊስ ቁጥጥር […]

ግጭት ባለባቸው የሰሜን ጎጃም እና ምዕራብ ጎጃም ዞኖች የ6ኛ እና የ8ኛ ክፍል ተማሪዎች ለብሔራዊ ፈተና አይቀመጡም

June 9, 2024 – DW Amharic  በሰሜን ጎጃም እና በምዕራብ ጎጃም ዞኖች የሚገኙ የ6ኛ እና የ8ኛ ክፍል ተማሪዎች የዘንድሮውን ብሔራዊ ፈተና እንደማይወስዱ የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ሙሉነሽ ደሴ ተናገሩ። አካባቢዎቹ የመንግሥት ኃይሎች እና የፋኖ ታጣቂዎች የሚዋጉባቸው ናቸው። በክልሉ ከ350 ሺህ በላይ ተማሪዎች ለፈተና የሚቀጠመጡ ቢሆንም ዕድሉን ያላገኙ ብዙ ናቸው።… … ሙሉውን ለማየት ወይም ለማንበብ እዚህ ላይ […]

በኦሮሚያ ክልል ሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞን ሁለት ወረዳዎች በግጭት ከመኖሪያቸው የተፈናቀሉ ዜጎች አስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ እንደሚኖሩ ተናገሩ

June 9, 2024 – DW Amharic  በኦሮሚያ ክልል ሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞን ሁለት ወረዳዎች በግጭት የተፈናቀሉ ዜጎች መቸገራቸውን ገለጹ። ለስድስት ቀናት ገደማ ጫካ ውስጥ መቆየታቸውን የሚናገሩ አንዲት እናት ልጆች ለረሐብ እና ለውኃ ጥም መጋለጣቸውን ገልጸዋል። ቤቶች መቃጠላቸውን፣ ንብረት መዘረፉን የገለጹት እናት “የደራሽ ያለህ እያልን ነው፤ በጣም ከብዶብናል” ሲሉ ተናግረዋል… … ሙሉውን ለማየት ወይም ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ

የአፍሪቃን የኤልክትሮኒክ ግብይት አቅምን መክፈት

June 9, 2024 – DW Amharic  በኤሌክትሮኒክ የሚፈፀም ግብይት በአፍሪቃ እስከ ጎርጎረሳዉያኑ 2025ዓ.ም ድረስ እስከ 75 ቢሊዮን ዶላርዕድገት ያስገኛል ተብሎ ተገምቷል። በአፍሪቃ በኤሌክትሮኒክ ገበያ ላይ፤ እንደ አማዞን ያሉ ግዙፍ ኩባንያዎች ወደ መድረክ እየወጡ ነው። በአፍሪቃ የኦንላይን ግብይት ቀጣይ የእድገት ርምጃ ወዴት ይሆን?… … ሙሉውን ለማየት ወይም ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ

የሱዳን ቀውስ፡ የዘር ማጥፋት አደጋዉ ጠንክሯል

June 9, 2024 – DW Amharic እየተባባሰ ባለዉ የሱዳን ቀዉስ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሰዎች ተፈናቅለዋል፤ በመቶዎች የሚቆጠሩ ደግሞ ተገድለዋል። በሃገሪቱ የሚገኙ ተዋጊ ቡድኖች ለሰላም ብዙም ፍላጎት ያላቸዉ አይመስልም። የተመድ እና ግብረሰናይ ድርጅቶች በጋር ይፋ ባደረጉት መግለጫ “በሱዳን ለሚኖሩ ጠኔ አፋፍ ላይ ለሚገኙ በሚሊዮን ለሚቆጠሩ ሰዎች ጊዜው አሳሳቢ እና እያበቃ ነዉ።… … ሙሉውን ለማየት ወይም ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ