በቦኮሃራም የታገተችው ናይጄሪያዊት ተማሪ ከ10 ዓመት በኋላ ሦስት ልጆችን ወልዳ ነጻ ወጣች

ከ 2 ሰአት በፊት ከአስር ዓመት በፊት በቦኮሃራም ታጣቂዎች ታግተው ከነበሩ ሴቶች መካከል አንዷ የሦስት ልጆች እናት ሆና በናይጄሪያ መንግሥት ወታደሮች ነጻ ወጣች። በአውሮፓውያኑ ሚያዝያ 2014 ቦርኖ ከምትባለው ከተማ የቦኮ ሃራም ታጣቂዎች 276 ተማሪ ሴቶችን ከሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤታቸው አፍነው መውሰዳቸው ይታወሳል። እነዚህ የቺቦክ ትምህርት ቤት ሴት ልጆች መታገት መላው ዓለምን አስደንግጦ በወቅቱ የአሜሪካ ቀዳማዊ […]

እስራኤል በኢራን ላይ የአጸፋ ጥቃት ፈጸመች

ከ 4 ሰአት በፊት እስራኤል ባለፈው ቅዳሜ ኢራን ለፈጸመችባት የድሮን እና የሚሳኤል ጥቃት ዛሬ ማለዳ ላይ የአጸፋ ጥቃት መፈጸሟን የኢራን መገናኛ ብዙኃን እና የአሜሪካ ባለሥልጣናት አስታወቁ። ዛሬ አርብ ጎህ ከመቅደዱ በፊት በማዕከላዊቷ የኢራን ከተማ ኢስፋሃን ፍንዳታዎች መሰማታቸውን የኢራን የመገናኛ ብዙኃን የዘገቡ ሲሆን፣ የአሜሪካ ባለሥልጣናትም ይህን አረጋግጠዋል። እስራኤል በኢራን ላይ የሚሳኤል ጥቃት መፈጸሟን የዩናይትድ ስቴትስ ባለሥልጣናት […]

የብልፅግና ፓርቲ ‘የሚዲያ ሠራዊት’ አባላት በሐሰተኛ መረጃ ሥርጭት እና አሳሳች የፌስቡክ ዘመቻዎች ላይ መሳተፋቸውን የቢቢሲ ምርመራ አረጋገጠ

የጽሁፉ መረጃ በገዢው ብልፅግና ፓርቲ በተለይም በአዲስ አበባ ከተማ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት ስር የሚንቀሳቀሱ እና ‘የሚዲያ ሠራዊት’ የሚል መጠሪያ ያላቸው የፓርቲው አባላት፤ መንግሥትን በሚተቹ እና በሚቃወሙ ግለሰቦች ላይ በፌስቡክ በተደረጉ የሐሰተኛ መረጃ እንዲሁም ‘የጥላቻ ንግግር’ ተብለው ሊቆጠሩ የሚችሉ ጽሑፎች እና ምስሎች ሥርጭት ላይ እንደተሳተፉ ቢቢሲ ያደረገው ምርመራ አረጋገጠ። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የወረዳ አመራሮችም በፓርቲው […]

ኢትዮጵያ፡ 56 በመቶ የሚሆኑ የሁለተኛ እና ሦስተኛ ክፍል ተማሪዎች ፊደል መለየት እንደማይችሉ ጥናት አመለከተ

ከ 3 ሰአት በፊት በኢትዮጵያ ከሚገኙ የሁለተኛ እና ሦስተኛ ክፍል ተማሪች 56 በመቶዎቹ ምንም ዓይነት ቃል ማንበብ እንደማይችሉ ሀገር አቀፍ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ባደረገው ጥናት አመልክቷል። አገልግሎቱ በጥናቱ ተሳተፊ ካደረጋቸው የሁለተኛ ክፍል ተማሪዎች መካከል ቢያንስ አንድ ቃል ማንበብ የሚችሉ 37 በመቶ የሚሆኑት ብቻ እንደሆኑ በአገልግሎቱ የትምህርት ምዘናና ምርምር መሪ ስራ አስፈጻሚ ኤፋ ጉርሙ (ዶ/ር) […]

በኬንያ በደረሰ የሄሊኮፕተር አደጋ የአገሪቱ ኢታማዦር ሹም እና ሌሎች መኮንኖች ሞቱ

ከ 4 ሰአት በፊት የኬንያ ጦር አዛዥ ጄኔራል ፍራንሲስ ኦሞንዲ ኦጎላ በምዕራብ የአገሪቱ ክፍል ይበሩበት የነበረው ወታደራዊ ሄሊኮፕተር ተከስክሶ ሕይወታቸው ማለፉን ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ አስታወቁ። ኦጎላ ከሌሎች 11 ወታደራዊ መኮንኖች ጋር ሆነው በሄሊኮፕተሩ ሲጓዙ ነው አደጋው የደረሰው። ከአደጋው የተረፉት ሁለት ሰዎች ብቻ ናቸው። ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ ሐሙስ ምሽት በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ አደጋው ለአገሪቱ “ትልቅ ሐዘን” […]

የዩክሬን ፕሬዝዳንትን ለመግደል ከሩሲያ ጋር ሲያሴር ነበር የተባለ ግለሰብ ፖላንድ ውስጥ ተያዘ

ከ 4 ሰአት በፊት የዩክሬን ፕሬዝዳንት ቭሎድሚር ዜሌንስኪን ለመግደል ከሩሲያ የደኅንነት አገልግሎት ጋር አሲሯል የተባለ ግለሰብ ፖላንድ ውስጥ በቁጥጥር ስር ዋለ። የፖላንድ ዐቃቤ ሕግ ፓዌል ኬ የተባለው ግለሰብ የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ፖላንድ ውስጥ ያለ አብዝተው ስለሚጠቀሙበት አየር ማረፊያ መረጃ እንዲሰበስብ ከሩሲያ ኃላፊነት ተሰጥቶታል ብሏል። ግለሰቡ በቁጥጥር ስር የዋለው የዩክሬን የደኅንነት መሥሪያ ቤት ለፖላንድ መንግሥት ጥቆማ ከሰጠ […]

ከአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የተሰጠ መግለጫ

Amhara Prosperity Party /APP/    ·  ከአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የተሰጠ መግለጫ ከትናንት ታሪካዊ ስህተቱ መማር የተሳነው ሕዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ (ህወሓት) የፕሪቶሪያውን ስምምነት ሙሉ በሙሉ በመጣስ ለአራተኛ ዙር ሕዝባችን ላይ ወረራ ፈፅሟል፡፡ ጀንበር ጠልቃ በወጣች ቁጥር ከጦርነት ውጭ ማሰብ የማይችለው የህወሓት ቡድን ከዉጭ እና ከዉስጥ ጠላቶቻችን ጋር ተናቦና ተቀናጅቶ በእርካሽ ፖለቲካዊ ብያኔና ፍረጃ በጊዜያዊ አሥተዳደሩ […]

ማንነቱንና ርስቱን አሳልፎ የሚሰጥ ትውልድ ኖሮም አያውቅም አይኖርምም – የሰብአዊ መብት ድርጅቶች የጋራ መግለጫ

Press Release Posted on 2024-04-15 Author rayaman   “ሆድ ሳያውቅ ዶሮ ማታ” እንዲሉ ወልቃይት ጠገዴ፤ ጠለምት፤ ራያ ያማነው? የሚለው ጥያቄ ጊዜው ያለፈበት ጥያቄ የሚያደርገው መልሱ በሁሉም ዘንድ የታወቀና የተመሰከረለት መሆኑ ብቻ ሳይሆን ዛሬ ህዝባችን ለዘመናት ባደረገው መራራ ትግልና በከፈለው ክቡር መስዋዕትነት ከትህነግ/ወያኔ ወረራ ነፃ የወጣና በልጆቹ እየተስተዳደረ የሚገኝ በመሆኑ ጭምር ነው። ሙሉ መግለጫውን ለማንበብ …