የመንግሥት የወጪ ቅነሳ ፖሊሲ ማኅበራዊ ልማትን ሊጎዳ እንደሚችል ባለሞያዎች ጠቆሙ

May 1, 2024 – VOA Amharic መንግሥት እየተከተለው ያለው የወጪ ቅነሳ ኢኮኖሚያዊ ፖሊሲ፣ ማኅበራዊ ዘርፉን እየጎዳው መኾኑን የምጣኔ ሀብት ባለሞያዎች ይገልጻሉ፡፡ ነዳጅን ጨምሮ አብዛኛውን ማኅበረሰብ በሚጠቅሙ ዘርፎች ላይ ሲደረጉ የቆዩ ድጎማዎች መነሣትንም ለአብነት ይጠቅሳሉ።… … ሙሉውን ለማየት ወይም ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ

ጦርነቱን ተከትሎ በአማራ ክልል ስር የተቋቋሙ አስተዳደሮች እስከ ሰኔ 30 መፍትሔ እንደሚያገኙ ጄነራል ታደሰ ተናገሩ

1 ግንቦት 2024 የትግራይን ጦርነት ተከትሎ በአማራ ክልል ስር ተጠቅለው የተቋቋሙ አስተዳደራዊ መዋቅሮች እስከ ሰኔ 30/ 2016 ዓ.ም መፍትሔ እንደሚያገኙ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ምክትል ፕሬዚዳንት ጄነራል ታደሰ ወረደ ተናገሩ። ጄነራል ታደሰ ባለፉት ሁለት ቀናት የፕሪቶሪያ ግጭትን በዘላቂነት የማቆም ስምምነት አተገባበር በተመለከተ የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ከመከላከያ እና ከፌደራል መንግሥት ባለስልጣናት ጋር ያደረጉትን ውይይት መሰረት በማድረግ […]

በአማራ ሕዝብ ላይ እየተፈጸመ ያለው ጥቃት ‘ስልታዊ የዘር ጭፍጨፋ’ አዝማሚያ እንዳለው የአውሮፓ የፍትሕና ሕግ ማዕከል የተባለ ድርጅት አስታወቀ

ከ 5 ሰአት በፊት የአውሮፓ የፍትሕና ሕግ ማዕከል “ድምጽ አልባው የአማራ ሕዝብ ስቃይ በኢትዮጵያ” በሚል አርዕስት ባወጣው ሪፖርት በክልሉና ከክልሉ ውጭ ከ2010 ዓ.ም. ጀምሮ የተፈጸሙ ጥቃቶችን ዘርዝሯል። በአውሮፓ እና በአለም አቀፍ ደረጃ የሰብዓዊ መብቶች ጥበቃ ላይ የሚሰራው ማዕከሉ የአገሪቱን የረጅም ዘመን ታሪክና የተወሳሰበ የፖለቲካ ስርዓት ቃኝቶ ሪፖርቱን የሚጀምር ሲሆን፤ ባለፉት ጥቂት ዓመታት በኢትዮጵያ ጉልህ የሆነ […]

የአፍሪካ ኅብረት በሕገ ወጥ መንገድ ከንግድ ባንክ አካውንቱ ሊወጣ የነበረው ስድስት ሚሊዮን ዶላር አለመሳካቱን ገለጸ

ከ 5 ሰአት በፊት የአፍሪካ ኅብረት በሕገ ወጥ መንገድ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አካውንቱ ሊወጣ የነበረው ስድስት ሚሊዮን ዶላር መክሸፉን አስታወቀ። የአፍሪካ ኅብረት ሚያዝያ 23 ቀን 2016 ዓ. ም. ባወጣው መግለጫ፣ በአዲስ አበባ ከተማ የአፍሪካ ኅብረት ዋና መሥሪያ ቤት ቅጥር ግቢ ውስጥ ከሚገኘው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፍ ስድስት ሚሊዮን ዶላር በሕገ ወጥ መንገድ ለማውጣት የተደረገው ሙከራ […]

ሩሲያ ከዩክሬን የማረከቻቸውን የጦር መሣሪያዎች ለዕይታ አበቃች

ከ 3 ሰአት በፊት የሶቪየት ህብረት ናዚ ጀርመንን ማሸነፍ አስመልክቶ በሞስኮ ግዙፍ የድሉ መታሰቢያ ፓርክ ይገኛል። ቦታው አሁን አዲስ ኤግዚቢሽን ማዕከል ሆኗል። ኤግዚቢሽኑ ግን ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት ጋር ምንም ግንኙነት የለውም። ለዕይታ የቀረቡት ዩክሬን ውስጥ በሩሲያ ጦር የተያዙ የምዕራባውያን ወታደራዊ መሣሪያዎች ናቸው። መሣሪያዎቹ የጦርነቱ ዋንጫዎቿ ሲሆኑ አደባባይ ላይ ለዕይታ አብቅታ ጡንቻዬን ተመልከቱልን ብላለች። ከተማረኩት መካከል […]

ብዙዎች ‘እንቅልፍ እንዲጥላቸው’ ያደረገውን ድምጽ አልባ ‘አላርም’ እንደሚያስተካክል አፕል ገለጸ

ከ 4 ሰአት በፊት የአንዳንድ አይፎን ስልኮች ከእንቅልፍ መቀስቀሻ ጥሪ (አላርም) ድምጽ አልባ መሆኑ ተጠቃሚዎችን እያማረረ ነው። እንቅልፍ ጥሏቸው እያረፈዱ መሆኑንም ተናግረዋል። አፕል ችግሩን በአፋጣኝ ለመቅረፍ እየሠራሁ ነው ብሏል። አንድ የአይፎን ተጠቃሚ “አምስት ጊዜ አላርም ብሞላም ምንም ድምጽ አላሰማም” ስትል ቲክቶክ ላይ ቅሬታዋን አሰምታለች። አፕል ችግሩ መከሰቱን ቢያውቅም ለምን እንደተከሰተና ተጠቃሚዎች እንዴት ችግሩን መቅረፍ እንደሚችሉ […]

የአፍሪካ የሕዋ ሳይንስ ጎልቶ እንዲታይ እሠራች ያለችው ወጣቷ ሳይንቲስት

ከ 5 ሰአት በፊት ካሜሩናዊቷ ሳይንቲስት ሜሪ ማኩዋቴ ከሳተላይት የሚገኝ መረጃን በመጠቀም በአደጋ ጊዜ ሰዎችን ለማዳን በሚደረገው ሩጫ ቀዳሚ ከሚባሉት አንዷ ናት። ነገር ግን የአፍሪካ አገራት የራሳቸውን የሕዋ ምርምር ጣቢያ ማቋቋም አለባቸው ስትል ትሞግታለች። ባለፈው መስከረም ማዕከላዊ ሞሮኮ በርዕደ-መሬት ስትመታ የ32 ዓመቷ ሳይንቲስት ስልክ በተደጋጋሚ መጥራት ጀመረ። ምንም እንኳ እሷ የምትገኘው ከአደጋው ሥፍራ በሺህ ኪሎ […]

በእርግጥ ቲክ ቶክ ለምዕራቡ ዓለም ስጋት ነው?

ከ 5 ሰአት በፊት በዩናይትድ ስቴትስ ኮንግረስ በኩል የጸደቀው ረቂቅ ሕግ ቲክ ቶክን በአሜሪካ ውስጥ የሚያግድ መሆኑን የተቃወችው ቻይና ውሳኔውንም ፍትሃዊ አይደለም ብላዋለች። ባለፉት ዓመታትም በቻይና ኩባንያ ባለቤትነት የተያዘው መተግበሪያ ከደኅንነት ጋር በተያያዘ የውዝግብ ምክንያት ሲሆን ተደጋግሞ ታይቷል። በብዙ ምዕራባውያን አገራት ያሉ ባለሥልጣናት፣ ፖለቲከኞች እና የደኅንነት ሠራተኞች እና ሌሎችም ቲክ ቶክን ስልካቸው ላይ እንዳይጭኑት ታግደዋል። […]

የሩስያ ወረራ ከሁለተኛው የዓለም ጦርነትም ይብሳል- የ98 ዓመቷ ዩክሬናዊት

ከ 5 ሰአት በፊት ሊዲያ ሎሚኮቭስካ የ98 ዓመት አዛውንት ናቸው። የሩሲያ ወረራ በዓይናቸው ከተመለከቱት ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት የከፋ ሆኖባቸዋል። ደመ ነፍሳቸውን ማመንን ተምረዋል። ለዚህም ነው የሩስያ ጦር በምስራቅ ዩክሬን ውስጥ ወደምትገኘው የትውልድ መንድራቸው ኦቼሬቲን ሲገባ ከቤተሰቦቻቸው ጋር ለመሸሽ የወሰኑት። በከባዱ የተኩስ ልውውጥ ወቅት ሊዲያ ከዘመዶቻቸው ተለያዩ። ነጠላ ጫማቸውን እንደተጫሙ ተስፋ ሳይቆርጡ ወደ ምዕራብ አቅጣጫ ጉዟቸውን […]