በአማራና በትግራይ ክልሎች መካከል የተፈጠረው ውዝግብ ተባብሶ ቀጥሏል

March 31, 2024 – Addis Admas  በአማራ ክልልና በትግራይጊዜያዊ አስተዳደር መካከል የተከሰተው ውዝግብ ተባብሶ ቀጥሏል። ሁለቱም ወገኖች በየፊናቸው ማስጠንቀቂያና መግለጫ እያወጡ ነው፡፡ የአማራ ክልል  ትናንት ባወጣው መግለጫ፤ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ሀገሪቱን ና ሁለቱን ክልሎች ወደ ቀውስ ከሚያስገቡ ተግባራቱ  እንዲቆጠብ አስጠንቅቋል። የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር  ያወጣው መግለጫ ጠብ አጫሪ  እንደሆነም ገልጿል። ክልሉ… … ሙሉውን ለማየት ወይም ለማንበብ እዚህ […]

ንግድ ባንክ በንዝህላልነት እና በግዴለሽነቱ የጠፋበትን ገንዘብ ፍለጋ ወደ ቁማር ቤቶች መዝመቱ ተሰምቷል።

March 31, 2024 – Konjit Sitotaw  ንግድ ባንክ በንዝህላልነት እና በግዴለሽነቱ የጠፋበትን ገንዘብ ፍለጋ ወደ ቁማር ቤቶች መዝመቱ ተሰምቷል። የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ያለ አግባብ የራሳቸው ያለሆነን ገንዘብ ከባንኩ ወስደው ወደ ቤቲንግ ተቋማት ያዘዋወሩ ሰዎች ባንክ በመገኘት ለዚሁ የተዘጋጀውን ቅጽ በመሙላት እንዲያመለክቱ አሳሰበ፡፡ ባንኩ መጋቢት 6 ቀን 2016 ባጋጠመው የሲስተም ችግር ምክንያት ያለአግባብ የገንዘብ ልውውጥ እንደነበር አስታውሷል። በዚህም […]

በምስል፡ የትንሳዔ በዓል በመላው ዓለም እየተከበረ ይገኛል

ከ 4 ሰአት በፊት በክርስትና እምነት ትልቅ ስፍራ የሚሰጠው የትንሳዔ በዓል በመላው ዓለም እየተከበረ ይገኛል። የአውሮፓውያንን የቀን ቀመር በሚከተሉ አገራት የሚገኙ ክርስቲያኖች እየሱስ ክርስቶስ ከሦስት ቀናት በኋላ ከሞት የተነሳበትን ሐይማኖታዊ በዓል እያከበሩ ይገኛሉ።

ፑንትላንድ ለሶማሊያ ፌደራል መንግሥት ዕውቅና መስጠት ማቆሟን አስታወቀች

ከ 1 ሰአት በፊት ከፊል ራስ ገዝ የሆነችው የሶማሊያዋ ግዛት ፑንትላንድ ሞቃዲሾ ለሚገኘው ለሶማሊያ ፌደራል መንግሥት የሰጠችውን ዕውቅና ማንሳቷን ይፋ አደረገች። የፑንትላንድ መንግሥት ካቢኔ ቅዳሜ መጋቢት 21/2016 ዓ.ም. ያካሄደውን አስቸኳይ ስብሰባን ተከትሎ ባወጣው መግለጫ ፑንትላንድ ለፌደራል መንግሥቱ ተቋማት ላይ የነበራትን መተማመን በማጣቷ ትሰጥ የነበረውን ዕውቅና ለማንሳት ወስኗል። ይህ የፑንትላንድ አስተዳደር ውሳኔ የተሰማው የሶማሊያ መንግሥት ፓርላማ […]

ትራምፕ፤ ፕሬዝደንት ባይደን እጅና እግራቸው ተጠፍሮ የሚታዩበት ፎቶ መለጠፋቸውን ተከትሎ ወቀሳ ደረሰባቸው

ከ 6 ሰአት በፊት የጆ ባይደን የምርጫ ቅስቀሳ ቡደን ዶናልድ ትራምፕ በማሕበራዊ ሚድያ ገፃቸው የለጠፉትን ቪድዮ ተከትሎ ትችት እየሰነዘሩ ነው። ትራምፕ ያጋሩት ቪድዮ ፕሬዝደንት ባይደን እጅና እግራቸው ተጠፍሮ የጭነት መኪና ላይ ተጭነው ያሳያል። ትራምፕ ከመጪው ኅዳር ምርጫ በፊት “በተደጋጋሚ ፖለቲካዊ አመፅ ለማስነሳት እየሞከሩ ነው” የሚል ትችት ደርሶባቸዋል። የትራምፕ ምርጫ ቅስቀሳ ቡደን ቃል አቀባይ በበኩላቸው ዲሞክራቶች […]