ከለሊቱ 9:52 በሬክተር ስኬል 5.8 የደረሰ የመሬት መንቀጥቀጥ ዛሬ ለሊት በአፋር ክልል ተከሰተ

January 4, 2025 – Konjit Sitotaw  በሬክተር ስኬል 5.8 የደረሰ የመሬት መንቀጥቀጥ ዛሬ ለሊት በአፋር ክልል ተከሰተ በኢትዮጵያ በሬክተር ስኬል 5.8 የተለካ የመሬት መንቀጥቀጥ፤ ከለሊቱ 9:52 መድረሱን የአሜሪካ የጂኦሎጂካል ሰርቬይ መስሪያ ቤት አስታወቀ። ሰሞኑን ሲከሰቱ ከነበሩት የመሬት መንቀጥቀጦች ዘለግ ላሉ ሰከንዶች የቆየው ርዕደ መሬት፤ ንዝረቱ በአዲስ አበባ የተለያዩ አካባቢዎች ተሰምቷል። የለሊቱ የመሬት መንቀጥቀጥ የተከሰተው በአፋር ክልል መሆኑን […]

በሬክተር ስኬል 5.5 የተመዘገበ እና በቅርብ ቀናት ከነበሩት ከፍተኛው የመሬት መንቀጥቀጥ ተከሰተ

January 4, 2025  በሬክተር ስኬል 5.5 የተመዘገበ እና በቅርብ ቀናት ከነበሩት ከፍተኛው የመሬት መንቀጥቀጥ ተከሰተ (መሠረት ሚድያ)- ምሽት 2:01 ላይ የተከሰተው ይህ ርዕደ መሬት 5.5 ሆኖ በሬክተር ስኬል እንደተመዘገበ የአሜሪካ ጂኦሎጂካል ሰርቬይ አስታውቋል፣ በርካታ የአዲስ አበባ ነዋሪዎችም ንዝረቱ እንደተሰማቸው እየጠቆሙ ይገኛሉ። ይህ በቅርብ ቀናት ውስጥ በአብዛኛው አዋሽ ፈንታሌ አካባቢ ከተከሰቱት ርዕደ መሬቶች በመጠኑ ከፍተኛው ሆኖ […]

በኢትዮጵያ እየተከሰተ ያለው የመሬት መንቀጥቀጥ ለ10 ሺህ ገደማ ሰዎች የእሳተ ገሞራ ፍንዳታ ስጋት እንደሆነ ተጠቆመ

January 4, 2025  በኢትዮጵያ እየተከሰተ ያለው የመሬት መንቀጥቀጥ ለ10 ሺህ ገደማ ሰዎች የእሳተ ገሞራ ፍንዳታ ስጋት እንደሆነ ተጠቆመ (መሠረት ሚድያ)- ‘Gelology Hub’ በሚል የሚታወቀው እሳተ ገሞራዎችን እና የመሬት እንቅስቃሴዎችን በተመለከተ ትንታኔ የሚያቀርበው ድርጅት እንዳለው በአለም ዙርያ ትኩረት የተነፈገው ይህ አደገኛ ክስተት የእሳተ ገሞራ ፍንዳታን ሊያስከትል የመቻል እድሉ ከፍተኛ ነው። በኢትዮጵያ እየተካሄዱ ያሉ ግጭቶች እና ጦርነቶች ይህ […]

በአፋር ክልል፣ ዱለሳ ወረዳ በተከሰት የመሬት መንቀጥቀጥ ሳቢያ በበርካታ ሥፍራዎች ላይ ፍል ውሃዎች እየተፈጠሩ ይገኛሉ።

January 4, 2025 – Konjit Sitotaw  በአፋር ክልል፣ ዱለሳ ወረዳ በተከሰት የመሬት መንቀጥቀጥ ሳቢያ በበርካታ ሥፍራዎች ላይ ፍል ውሃዎች እየተፈጠሩ ይገኛሉ። በወረዳው በሳጋንቶ ቀበሌ የደረሰውን የመሬት መንቀጥቀጥ ተከትሎ በስፍራው በአካል በመገኘት የመስክ ምልከታ ያደረገ የኢቢሲ ሪፖርተር በቀበሌው በበርካታ ሥፍራዎች ላይ ፍል ውሃዎች እየወጡ መሆኑን መታዘቡን ገልጿል። በቀበሌው በተለይ በዶፈን ተራራ ላይ የመሬት መንቀጥቀጡ በመጠኑም በድግግሞሹም ከጊዜ ወደ […]

ኢትዮጵያ በሶማሊያ ከሚሰማራው አዲስ ተልዕኮ ጋራ እንደምትተባበር አስታወቀች

January 4, 2025 – VOA Amharic  በሶማሊያ አዲሱ የአፍሪካ ኅብረት የሰላም ተልዕኮ ከአል ሻባብ ጋራ ለሚያደርገው ፍልሚያ እንደምትተባበር ኢትዮጵያ አስታውቃለች፡፡ በሶማሊያ የአፍሪካ ኅብረት የድጋፍና የማረጋጋት ተልዕኮ በቅርቡ ወደ ሶማሊያ እንደሚሰማራ በመጠበቅ ላይ ነው። ኢትዮጵያ ከሶማሊላንድ ጋራ የፈጸመቸው የባሕር በር አቅርቦትን የተመለከተ የመግባቢያ ስምምነት በፈጠረው ውጥረት ምክንያት፣ የኢትዮጵያ ወታደሮች ተሳተፎ እንደማይ… … ሙሉውን ለማየት ወይም ለማንበብ እዚህ ላይ […]

የኒው ኦርሊንስ  ሽብር ተጠርጣሪ እስላማዊ መንግሥትን መቀላቀሉን ተናግሯል

January 4, 2025 – VOA Amharic  በአውሮፓውያኑ የዘመን መለወጫ፣ ሰዎች በሞቱበት የኒው ኦርሊንሱ ሽብር ጥቃት ተጠርጣሪ፣ ድርጊቱን በእስላማዊ መንግሥት አሸባሪ ቡድን ተነሳስቶ ብቻውን የፈጸመው ይመስላል ሲል፣ ኤፍ ቢ አይ ትላንት ሐሙስ አስታወቀ። ተጠርጣሪው የጦር ሠራዊት አባል ነበር። መርማሪዎች ላስ ቬጋስ ውስጥ በአሜሪካ ወታደር ይሸከረከር ከነበረው ሌላ የተሽከርካሪ ጥቃት ጋራ፣ የጥቃቶቹ መነሻ ምክንያትና ተያያዥ ሊሆኑ ይችላሉ በ… … […]

የዋጋ ግሽበት በባለሙያዎች እና ነዋሪዎች አተያይ

January 4, 2025 – DW Amharic  አስተያየታውን የሰጡን የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች ከአምና አንጻር ከዘይት እስከ ሽንኩርት፣ ከጤፍ እስከ በርካታ የምግብ ፍጆታ እቃ እና የቤት ውስጥ መገልገያዎች ያልጨመረ ነገር የለም ባይ ናቸው፡… … ሙሉውን ለማየት ወይም ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ

ካልፎርኒያ አነስተኛ አውሮፕላን ተከስክሶ ሁለት ሰዎች ሞቱ

January 4, 2025 – VOA Amharic  በአሜሪካ ካልፎርኒያ ግዛት ውስጥ አንድ አነስተኛ አውሮፕላን ትላንት ሐሙስ ተከስክሶ ሁለት ሰዎች ሕይወታቸውን እንዳጡ ፖሊስ አስታውቋል። አውሮፕላኑ ደቡብ ካልፎርኒያ ውስጥ በሚገኘ አንድ የቤት ዕቃዎች ማምረቻ መጋዘን ላይ እንደተከሰከሰም ፖሊስ አስታውቋል። የአውሮፕላኑ መከስከስ እሳት በማስነሳቱም 200 የሚኾኑ ሠራተኞች አካባቢውን ለቀው እንዲወጡ ተደርጓል። ዐስራ አንድ በሚኾኑ ሰዎች ላይ ጉዳ… … ሙሉውን ለማየት ወይም […]

በአክሱም የሚገኙ ሴት ሙስሊም ተማሪዎች ችግር በሦስት ቀናት እንዲፈታ ምክር ቤቱ አሳሰበ

January 4, 2025 – VOA Amharic  ለሦስት ሳምንታት የፀጉር መሸፈኛ ሒጃብ ለብሰው ወደ ትምህርት ቤት እንዳይገቡ ተከልክለዋል፣ የተባሉ ሴት ሙስሊም ተማሪዎች ችግር በሦስት ቀናት ውስጥ እንዲፈታ የትግራይ ክልል እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክርቤት ዛሬ ዐርብ ታኅሣሥ 25 ቀን 2017 ዓ.ም. በሰጠው መግለጫ አስታወቀ። ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ። … … ሙሉውን ለማየት ወይም ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ

የደቡብ ኮሪያ ፕሬዝደንትን ለመያዝ የተደረገው ሙከራ ከሸፈ

ጃንዩወሪ 03, 2025  አስተያየቶችን ይዩ የደቡብ ኮሪያ መርማሪዎች ተከሳሹን የአገሪቱ ፕሬዝደንት ዩን ሶክ ዮል በቁጥጥር ሥር ለማድረግ የነበራቸውን ሙከራ አቁመዋል። መርማሪዎቹ ሙከራውን የተውት ፕሬዝደንቱን ከመኖሪያ ቤታቸው ለመያዝ ያደርጉት ሙከራ በጠባቂዎቻቸው በመገታቱ ነው። የሀገሪቱ ሕግ አውጪ ምክር ቤት ፕሬዝደንቱን ከሥራቸው ያገደ ሲሆን፣ የመያዣ ትዕዛዙ ተግባራዊ የሚደረግ ከሆነ ዩን ሶክ ዮል በደቡብ ኮሪያ ታሪክ የተያዙ የመጀመሪያ ፕሬዝደንት […]